The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

BC-6

የ3,300 ሜትር ካሬ ውሃ ስርገት መከላከል (water proofing) ሰራ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 24፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Submission Date:ጨረታው ህዳር 8 ቀን 2013 ዓም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ8፡30  ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

 የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር፡- NCB/GOV/N-CS004/2013

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን የዋናውን መ/ቤት ህንፃ የ3,300 ሜትር ካሬ ውሃ ስርገት መከላከል (water proofing) አገልግሎት ግዥ  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችን  በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት መገናኛ ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ምድር ቢሮ ቁጥር 113 በመገኘት ከላይ ለተጠቀሰው ግዥ የተዘጋጀውን  የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡
  2. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት የግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ  በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ በድረ-ገፅ የተመዘገበ፣ ለዘመኑ ሕጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ግብር የመክፈል ግዴታቸውን  የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ በመወዳደሪያ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  3. ጨረታውን ለመሳተፍ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ  ማስከበሪያ የሚሆን ቢያንስ ለ60 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህንኑም እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ከዋናው ሠነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን በአንድ ፖስታ (One envelope) /የቴክኒክ እና የዋጋ በአንድ ላይ የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው::
  5. አሸናፊው ተጫራች ላሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10%  ከውል በኋላ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ ለ60/ስልሣ/ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ  መሆን አለበት፡፡ ከዚህ ያነሰ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ያቀረበ  ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
  7. የጨረታ ሠነዱን በሰሙ አስመዝግቦ ያልገዛ ማንኛውም ተወዳዳሪ  በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡
  8. ጨረታው ህዳር 8 ቀን 2013 ዓም ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ8፡30  ሰዓት 4ኛ ፎቅ በመ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓትና ቀን ዘግይቶ የሚመጣ ማንኛውም የመወዳደሪያ ሠነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. የሚቀርበው ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስን ያካተተ መሆን አለመሆኑን  በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ አለበት፡፡ ይህንን ያልገለፀ ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን እንዳካተተ ተደርጐ ይቆጠራል፡፡
  10.  ገዥው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠቀሱትን አገልግሎት በ20%  የመጨመር ወይም በ20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. የባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- መገናኛ ከሚገኘው በተለምዶ 24 ቀበሌ የገቢዎች ሚኒስቴር  አጠገብ ያለው የዋ/መ/ቤት ህንጻ ምድር ቢሮ ቁጥር113 ስልክ ቁጥር፡- 011 663 08 57 ፋክስ ቁጥር፡- 0116-623924

የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን

Dormiteries Painting, Toilet Maintenance and Roof Maintenance works

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 24፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ወሎ ዩኒቨርሲቲ
Submission Date:ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ፡ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው)  በተገኙበት በኮምቦልቻ  በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር  302 የሚከፈት ይሆናል ፡፡

 የጨረታ ማስታወቂያ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ :-

  • ሎት- 1 Electrical Workshop Renovation and Miscellaneous works
  • ሎት – 2 Dormiteries Painting, Toilet Maintenance and Roof Maintenance works

በመሆኑም:-

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች  ከሎት1 እስከ ሎት 2 ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመከፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት ያህል ሰነዱን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ  ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 302 በሚገኘው መውሰድ/መግዛት የሚችሉና ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ፖስታውን ከአንድ ኮፒ ጋር እንዲሁም ለየብቻ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:::
  2. ተጫራቾች ለሎት-1 እና ሎት-2 (በG.C6 ወይንም በ BC ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ያለው መሆን አለባቸው::
  3. ከሎት1- እስከ ሎት-2 ላሉት የግንባታ ስራዎች ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት በአንዱ ላይ ብቻ ነው:: ወይንም ሰነድ መግዛትና መወዳደር  የሚችሉት አንድ ሎት ላይ ብቻ ነው::
  4. ተጫራቾች ሊሰራ ከሚፈለገው ስራ ጋር በዘርፉ ቀጥተኛ ወይንም ተዛማጅ እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የታደሰ የሙያ ብቃት  ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር  ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ክሊራንስ የግብር (ጨረታ እንዲጫረቱ የሚል) የግብር ከፋይ መለያ  ቁጥር እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ በስራ ዘርፉ ተመዝጋቢ መሆን  አለባቸው::
  5. ተጫራቾች ዋጋ መውላት ያለባቸው ዩኒቨርሲቲው ባቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ነው:: እንዲሁም ስርዝ ድልዝዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
  6. ተወዳዳሪው (ተጫራቹ) ከሎት-1 እስከ ሎት-2 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ የስራ ዋስትና ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ  ሃምሳ ሺህ ብር) ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ጋራንቲ ብር 250,000.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ ) የ90 ቀናት ያህል ሊቆይ የሚችል  የስራ ዋስትና ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ለሁሉም ሎት ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ በጨረታው ለተሸነፈ ድርጅት አሸናፊው ድርጅት ከአዋርድ ከተደረገ በኋላ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
  8. ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ወይንም bill of quantity መሠረት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  9. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10. ከሎት-1 እስከ ሎት-2 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ፡ ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው)  በተገኙበት በኮምቦልቻ  በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር  302 የሚከፈት ይሆናል ፡፡
  11. ለሁሉም የጨረታ ሎት( ከሎት-1 እስከ ሎት-2) የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን ባለው የስራ ቀን በተራቁጥር 10 ላይ በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
  12. ስርዝ ድልዝ ያለው የዋጋመሙያሰነድ ተቀባይነት የለውም
  13. የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ደረስ ጨረታውን አያስተጓጉልም፡፡
  14. ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ  ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ተጫራቾች ከዚህ የጨረታ ማስታወቂያ በተጨማሪ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘውን  የተጫራቾች መመሪያ ባለማንበብ እና ባለመገንዘብ (ባለመረዳት) ለሚከሰተው ችግር ዩኒቨርሲቲው ተጠያቂ አይሆንም ፡፡
  16. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው 60 ቀናት ያህል ብቻ ነው፡፡
  17. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም

በስልክ  ቁጥር፡-033 851 41 20/03 38 51 90 42 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ወሎ ዩኒቨርሲቲ

ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ

ኢንስቲትዩት

የግንባታ ማጠናቀቅ ስራ (aluminum window and aluminum door work )

Published on:Addis Zemen ( Nov 3, 2020 )Place of Bid Competitions:Amara 
Submission Date:Floating period of bid is 10 working days starting from the announcement of this bid on Addis Zemen Newspaper. Bids will be closed at 2:00 Pm 

Invitation for Bids

Bid No, ORDA/NCB/PW/02/2020

  1. The Organization for Rehabilitation and Development in Amhara (ORDA) has a plan to aluminum window, aluminum door and aluminum hand rail and baluster Work purchase including the supply of all necessary materials based on the attached design and specification in the bid document, the work place is at Bahirdar city Hidasie kebele ORDA garage building.
  2. The Organization for Rehabilitation and Development in Amhara (ORDA) invites eligible bidders for the aluminum window and aluminum door work purchase including the supply of all necessary materials.
  3. Bidders submit appropriate documentary evidence demonstrating its compliance, which shall include:
    • Valid and renewed trade license (የግንባታ ማጠናቀቅ ተቋራጭነት ስራ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች ብቻ) )
    • VAT registration certificate issued by the tax authority,
    • Trade registration certificate and other necessary legal documents
  4. Bid must be delivered to the Address in a sealed envelope within 10 working days below at 7(b) at the end of 10 working days before 2:00 pm
  5. All bids must be accompanied by a bid security of 2% from the total amount of bid price in the form of CPO or Unconditional Bank guarantee only.
  6. Floating period of bid is 10 working days starting from the announcement of this bid on Addis Zemen Newspaper. Bids will be closed at 2:00 Pm and opened in the presence of the bidders’ or representatives who choose to attend at the address below at 7 (b) or without opening ceremony flowers we can open the bid at the end of 10 working days at 2:30 pm.
    •  (a) Documents will be obtained Bahir Dar City at Organization for Rehabilitation and Development in Amhara (ORDA) head office, block No 1, room No. 106 Telephone 058-226- 63- 57 Fax. 058 226 43 74 P.O. Box – 132 and Addis Ababa Branch office near to Bole Printing press Telephone 011-550-44- 55
    • (b) Bids must be delivered to, and will be opened Bahir Dar City at Organization for Rehabilitation and Development in Amhara (ORDA) head office, Room No. 106
  7. ORDA reserves the right to cancel the bid fully or partially.

Organization for Rehabilitation and Development in Amara (ORDA)

ለዝብቲት የመ/ደ/ት/ቤት አገልግሎት የሚውል አንድ ብሎክ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ ብሎክ የሴቶች መፀዳጃ ቤት እና አንድ ብሎክ የሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ክፍል እና ለእኔሣ የመ/ደ/ት/ቤት አንድ ብሎክ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ ብሎክ የሴቶች መፀዳጃ ቤት እና አንድ ብሎክ የሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ክፍል

Published on:Be’kur ( ጥቅምት 23፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ
Remaining Time for Bid Submission (Check it)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ት/ጽ/ቤት ለዝብቲት የመ/ደ/ት/ቤት አገልግሎት የሚውል አንድ ብሎክ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ ብሎክ የሴቶች መፀዳጃ ቤት እና አንድ ብሎክ የሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ክፍል እና ለእኔሣ የመ/ደ/ት/ቤት አንድ ብሎክ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ ብሎክ የሴቶች መፀዳጃ ቤት እና አንድ ብሎክ የሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ ክፍል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት ተጫራቾች፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፡፡
  6. ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የማይመለስ ብር 50.00 ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 7/3/2013 ዓ.ም 3፡00 ድረስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተጫራቾች መመሪያ ጋር የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ በማካተት በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱን ስም፣ አድራሻ ፣ ፊርማ ፣ ማህተም በማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ረታውን በ8/3/2013 ዓ.ም በ16ኛው ቀን እስከ 3፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ታሽጎ በ3፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዮ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ 1 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ በስልክም ሆነ በአካል አቤቱታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ አይነት የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 1.5 በመቶ እና በላይ ሆኖ የቫት ተመዝጋቢ ተወዳዳሪዎች ከሆኑ የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከነቫቱ መሆኑን እና እንደ ተጫራቾች ምርጫ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒዮ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይንም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ የሚያሲዙ ከሆነ በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ ጥሬ ገንዘቡን በመሂ/1 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0586660003 /0586660414/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር

የግንባታ የአጥር ስራ

Published on:Be’kur ( ጥቅምት 16፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በሰሜን ሸዋ በሞጃና ወደራ ወረዳ
Submission Date:ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ እና ንብረት አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ እና ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል በ16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ሸዋ በሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው የጋውና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ2013 በጀት ዓመት ለተለያዩ የግንባታ አይነቶች የሚውሉ

  • የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን፣
  • የግንባታ የአጥር ስራ
  • የቢሮ እቃ የጽዳት ፣
  • የህትመት
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች
  • የተሽከርካሪ መለዋወጫ
  • የጀኔሬተር ጥገና የሞተር ጥገና ለድጋፍ ሰጭ እና
  • ለባለሙያተኞች የደንብ ልብስ በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የም ትችሉ ሲሆን፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠን ብር 50 ሺህ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እና ይጠቅማኛል የሚሉትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4.  በግንባታ ዘርፍ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ከደረጃ /6/ በላይ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የእቃዎችን እና የግንባታ አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር ብቻ በመክፈል ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ስር ደጋፊ የስራ ሂደት ከዋና ገንዘብ ያዝ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩብት ብር ወይም የእቃውን ወይም የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋው 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ እና ንብረት አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ እና ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል በ16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. በጥንቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
  10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 033 89 94 860 ወይም 09 20 86 72 19 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  13. አድራሻ በአብክመ የሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 100 ኪ.ሜ ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማ በር ዋሻ ወደ ም ዕራብ በ40 ኪ.ሜ ገባ ብሎ፡፡

በሰሜን ሸዋ በሞጃና ወደራ ወረዳ

የቆቦ አጠ/ከፍ/መሰ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ

Published on:Be’kur ( ጥቅምት 23፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ 
Submission Date:ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን 13/03/2013 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በ22ኛው ቀን 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን በቆቦ ከተማ አስተዳደር ትም/ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የቆቦ አጠ/ከፍ/መሰ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2013 ዓ/ም በተያዘው በጀት ዓመት የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ ኩንታራክተሮችን በጋዜጣ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት/ማስገባት/ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናቶች ማለትም ከ23/02/2013 ዓ/ም እስከ 13/03/2013 ዓ/ም ድረስ የምትጫረቱ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ዋጋ መሙላያ ዝርዝር ከት/ቤቱ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ 100 ብር ገዝቶ በመውሰድ ሞልቶ በስም በታሸገ ፖስታ ለት/ቤቱ በማስገባት የምትጫረቱ መሆኑን እያሣወቅን፡፡

ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን 13/03/2013 ዓ/ም ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ በ22ኛው ቀን 3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

የጨረታ አይነት የአስተዳደር ህንፃ ግንባታ የተጫራቾች መመሪያ

  1. ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ስራ ግብር የከፈሉ መሆን አለበት፡፡
  2.  የምዝገባ ሰርተፊኬት/ቲን/ ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የቫት ተመዝጋ መሆን አለባቸው፡፡
  4. የግምባታ ፈቃዳቸው ከደረጃ 9 እና በላይ ያሉትን ይጋብዛል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የዋስትና ማስከበሪያ 10 በመቶ እና የቅድሚያ ክፍያ ማስከበሪያ 30 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  7.  አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  8. የጨረታ ዋጋው ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዳይኖረው በጥንቃቄ መሞላት አለበት፡፡
  9. የሚሰሩ የግንባታ ስራ ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከዋጋ ማቅረቢያው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. ሙሉ በሙሉ የግንባታ ወጭውን በራሱ ወጭ አጠናቆ በመስራት ማስረከብ የሚችል፡፡

ማሣሰቢያ፡- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡  ተጫራቾች እኩል ከወጡ አሸናፊውን በድርድር የሚለይ ይሆናል፡፡

የበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0920315258 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

የቆቦ ከተማ አስተዳደር ትም/ት/ጽ/ቤት

የግንባታ ፣ የአጥር ስራ፣…

Published on:Be’kur ( ጥቅምት 23፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአክብመ የሰሜን ሸዋ ዞን
Submission Date:ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታለስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል 16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ በሚገኘው የጋውና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለ2013 በጀት አመት

  • ለተለያዩ የግንባታ አይነቶች የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን፣
  • የግንባታ የአጥር ስራ፣ የቢሮ እቃ፣
  • የጽዳት፣ የህትመት፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • የኤሌክትሪክ መለዋወጫ እቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣
  • የጀኔሬተር ጥገና ፣የሞተር ጥገና ለድጋፍ ሰጭ እና ለባለሙያተኞች የደንብ ልብስ በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር

የምትችሉ ሲሆን፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው
  2. የግዥ መጠን 50000/ሃምሳ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን እናይጠቅመኛል የሚሉትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. በግንባታ ዘርፍ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ከደረጃ /6/ በላይ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የእቃዎችን እና የግንባታ አይነት ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50 ብር በመክፈል ግዥ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ከዋና ገንዘብ ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ወይም የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታለስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 16 ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ክፍል 16ኛው ቀን በ4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. በጥንቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ድጋፍይደረግላቸዋል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ 033 89948 60/09 20 86 72 19 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  • አድራሻ፡- በአክብመ የሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን 100 ኪ.ሜ ወደ ደሴ መስመርከሚወስደው መንገድ ጣርማ በር ዋሻ ወደ ምዕራብ በ40 ኪ.ሜ ገባ ብሎ ነው፡፡
  • የጋውና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ

የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ በአለም ባንክ በጀት and የማሽነሪ ኪራይ

Published on:Be’kur ( ጥቅምት 16፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ወልዲያ ከተማ 
Remaining Time for Bid Submission (Check it)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልል በሰ/ወሎ/ ዞን የወልዲያ ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት በአለም ባንክ፤ በመደበኛ በጀትና በሮድ ፈንድ በጀት ለሚያሰራው የመሰረተ ልማት ስራዎችና የእቃ ግዥና የማሽነሪ ኪራይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ለዚህ ጨረታው መሳተፍ ለምትፈልጉ ሁሉ ለግንባታ ስራ በደረጃ 9 እና በላይ ሙያ ባላቸው የስራ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • 6 ሳይት የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ በአለም ባንክ በጀት
  • ሎት 1. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ በአለም ባንክ በጀት
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ግዥ በአለም ባንክ በጀት
  • 1 ሳይት የውሃ ተፋሰስ ጥገና በመደበኛ በጀት
  • 1 ሳይት ሪቴንግ ወል በአለም ባንክ በጀት

የተለያዩ ደረጃዎች ባላቸው የስራ ተቋራጮችና አቅራቢዎች አስፈላጊ የሆኑትን የግንባታ ማቴሪያሎትና የእጅ ዋጋ ችለው ለሚሰሩ ተወዳዳሪዎችና የእቃ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተቋራጮችና አቅራቢዎች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡ ስለዚህ

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ አለበት፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ አለበት፡፡
  3. የግዥው መጠን ለግንባታ 50 ሺህ ብር ለዕቃና አገልግሎት ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ቫት ተመዝጋቢ መሆን አለበት፡፡
  4. ማንኛውም የስራ ተቋራጭ የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ከአማራ ክልል ውጭ የሚመጡ ተጫራቾች በሚንስተር መ/ቤቱ የኮንስትራክሸንና ኢንዱስትሪ ልማት ቁጥጥር ባለስልጣን የምዝገባ ሰርትፈኬት ወይም አጭር ምዝገባ ማቅረብ አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ/ ገቢ ሆኖ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ ኮፒ አድርጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርበታል
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰ/ወሎ ዞን ወልዲያ ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
  • 6 ሳይት የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ ለእያንዳንዱ ሰነድ 50 ብር
  • ሎት 1. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሰነድ 100 ብር
  • ሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ሰነድ 50 ብር
  • 1 ሳይት የውሃ ተፋሰስ ጥገና ስራ ሰነድ 50 ብር
  • 1 ሳይት ሪቴንግ ወል ሰነድ 50 ብር
  • ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝቶ መጫረት /መወዳደር/ የሚችለው የመረጡትን የግንባታ ስራ 2/ሁለት/ ሳይት ብቻ መርጦ መግዛትና መወዳደር ይችላል፡፡ ከዚህ ውጭ ወይም ከተፈቀደው ሰነድ በላይ ገዝቶ የተገኘ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፤ለግንባታ ስራው ተወዳዳሪዎች አሸናፊ ከሆኑ የማቴሪያል ቴስት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  1. በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ለተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማሰያዝ አለብዎት፡፡
  2. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤና የመልካም ስራ አፈጻጸም ወቅታዊ የሆነ መረጃ በሃላፊ የተፈረመ ማቅረብ አለበት፡፡
  3. በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ እና 10 በመቶ አስይዘው ወደ ስራ መግባትዎ ሲረጋገጥ እንደየፕሮጀክቱ ዓይነት እስከ 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ይሰጣል፡፡
  4. ማንኛውም የግዥ ወይም የግንባታ ስራዎች የጨረታ ሰነዱን ዋጋ መሙሊያ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝና በፍሉድ የጠፋ እንዲሁም የማይነበብ ተደጋግሞ የተጻፈ እንዲሁም የማይነበብ የማስረጃ ፎቶ ኮፒ አያይዞ የቀረቡ ተወዳዳሪዎች /ተጫራቾች/ ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. 5የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናልና በኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ የሚወዳደሩበትን ሳይት እና እቃ በፖስታው ላይ በመጻፍና በማዘጋጀት የድርጅቱን ማህተምና ፈርማ ሙሉ አድራሻ በመግለጽ በተለያየ ፓሰታ አሽጎ በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ማሰገባት ይኖረባቸዋል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 12 የተዘረዘሩት መስፈርቶች ለሁሉም ተጫራቾች (ተወዳዳሪዎች) ገዥ ይሆናል፡፡

1. ለውሃ ተፋሰስ ግንባታ ቁጥር  1 የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ ቁጥር 1

በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎት ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በአለም ባንክ በጀት ለሚያሰራው የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ ከወርቂት አያሌዉ ቤት እስከ ፈንታየ ቤት ድረስ 73 ሜትር ኮድ woldia – CW- DR- UIIDP-03—03–2020/2021 እና ጎማጣ ከስለሽ ቤት እስከ ነባሩ ተፋስስ ድረስ 110 ሜትር ኮድ woldia- CW- DR- UIIDP-03-02–2020/2021 ያሉትን የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ በደረጃ 9ና በላይ ሙያ ባላቸው የስራ ተቋራጮች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ለተፋሰሶች ግንባታ የሚያስፈልጉ ማንኛውንም የግንባታ ማቴሪያሎችና የእጅ ዋጋ ችሎ ወይም አቅርቦ ለመስራት ለሚፈልጉ ሁሉ በተዘጋጀው ፕላንና የሰራ ዝርዝር መሰረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/03/2013 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሰራ ሰአት የጨረታ ሰነዱን በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማሰገባት አለበት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 16/03/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

ከነባሩ ተፋሰስ እስከ ፈንታየ እሸቱ ቤት ድረስ በአለም ባንክ በጀት ለሚሰራው 100 ሜትር የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ ኮድ woldia- CW–DR -UIIDP–04-01–2020/2021 ለተፋሰስ ግንባታ ስራ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 16/03/2013 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 16/03/2013 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

2. ለውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ ቁጥር 2

በ ወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በአለም ባንክ በጀት ለሚያሠራው የውሃ ተፋሰስ ግንባታ ስራ ከጽሀይሰገድ ቤት እስከ ንግስት ቤት ድረስ 185 ሜትር ኮድ woldia- CW—DRUIIDP-05-01-2020/2021 እና መምህር አራጌ ቤት አካባቢ 54 ሜትር ኮድ woldia- CW–DR—UIIDP-05-02-2020/2021 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/2/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 17/3/2013 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ፖስታውን ከጠዋቱ 3፡00 ማስገባት አለበዎት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 17/03/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

ቲንፋዝ ቀበሌ ከነባሩ ተፋሰስ እስከ ጎረጅ ድረስ 70 ሜትር ኮድ woldia- CW–DR-UIIDP-05-03-2020/2021 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 17/03/2013 ዓ/ም የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለበት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 17/03/2013 ዓ/ም 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

3. ሪቲንግ ወል

በወ/ከ/አስ/ኢን/ል/ከተማ አገልግሎ ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በአለም ባንክ በጀት ለሚያሰራው ሪቲንግ ወል ግንባታ ስራ ከዘይንያ ሱቅ፤ሰናይት ቤት እና ወረቅዉሃ ቤት ድረስ 75 ሜትር ኮድ- woldia-CW-RWUIIDP- 07-01-2020/2021 ይህ ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን 16/2/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2013 ዓ.ም የጨረታ ፖስታውን ከጠዋቱ 3፡00 ማስገባት አለበዎት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 18/03/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡ ኪ/ምህረት ቤተክርስቲያን እስከ ሸሌ ድረስ 100 ሜትር በመደበኛ በጀት የዉሀ ተፋሰስ ጥገና ስራ ኮድ woldia-CW-CIP-DM-03-01–2020/2021 ዓ/ም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 18/03/2013 ዓ/ም የጨረታ ፖስታውን ከሰዓት 8፡00 ማስገባት አለበት፡፡ የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 18/03/2013 ዓ/ም ከሰዓት 8፡00 ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 8፡30 የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡

  • 1. ሎት1 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት2 ጽ/መሳሪያ የወ/ከ/አስ/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት በአለም ባንክ በጀት በ2013 ዓ/ም የኤሌክትሮኒክ ዕቃዎችና የጽ/መሳሪያ በየሎቱ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቱን አሟልተው መጫረት ለምትፈልጉ

ሁሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን 16/02/2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 01/03/2013 ዓ/ም የጨረታ ፖስታውን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ማስገባት አለበዎት የጨረታ ሳጥኑም በዚሁ ቀን 01/03/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡ በጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ያሸነፉበትን ንብረት በራስዎ ወጭ አጓጉዘው ወ/ከ/አገ/ንብረት ክፍል ገቢ ያደረጋሉ፡፡ ካሸነፉት ንብረት ውስጥ ትክክለኛውን እቃ ካላቀረቡ በራስዎ ወጭ መልሰው ትክክለኛውን እቃ ያቀርባሉ፡፡ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ሁሉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 03 33 31 03 22 እና 03 33 31 18 61 ወይም 03 33 31 13 31 በመደወል መረጃ ማገኘት ይቻላል፡፡

  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የመከፈቻ ቀኖች ከላይ በተገለጹት ሲሆን በብዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

የወልዲያ ከተማ አስ/ር/ኢ/ል/ከ/አገ/ጽ/ቤት

Lot-I Guna Begemdir Construction Projects

Published on:Addis Zemen ( Nov 1, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Submission Date:Addis Ababa Office on submission of the tender document the 10th day from the first publication on Addis Zemen newspaper at or before 2:00 PM (bid closing time) Bid Requirements

Invitation for Bids

Issued By ActionAid Ethiopia

Bid Category Construction: Lot-1 Guna Begemdir Construction Projects ActionAid Ethiopia (AAE) is a gender justice, good governance, and poverty eradication organization. It envisions a country where all enjoys their rights equally and live a decent life. Its heart lies on gender equality where it designs its frameworks and operations on women’s and girls’ empowerment and abolishing root causes of violence against women and girls. Its interventions are guided by the Human Rights Based Approach, Transformative Femimst Leadership, and Intersectional Feminist Analysis tools. AAE has been implementing programs in Ethiopia under both humanitarian and development contexts for more than 30 years

ActionAid Ethiopia believes that Gender equality and poverty eradication are achieved through purposeful individual and collective action to bring socio-economic changes from household level to local, national, and international levels. Empowerment of people living in poverty and women leadership with the support of their allies is crucial to driving change that will ensure equality and

  • Lot-I Guna Begemdir Construction Projects

ActionAid Ethiopia invites all eligible contractors with GC or BC Grade 6 and above who have a license valid for the current year and a Registration certificate for VAT & trade.

Bids shall be valid for a period of 120 days after Bed opening and must be accompanied by Bid security of ETB 20,000 (Twenty Thousand) CPO only and shall be delivered to ActionAid Ethiopia

Addis Ababa Office on submission of the tender document the 10th day from the first publication on Addis Zemen newspaper at or before 2:00 PM (bid closing time) Bid Requirements

  1. ActionAid Ethiopia (hereafter referred to as “the Organization”) now invites wax-sealed bids from interested eligible bidders for Guna Begemdir Lot! projects, construction of Library and Dry Pit latrine blocks located at Guna Begemdir Woreda, Atekana Kebele.
  2. Complete sets of the bidding documents may be accessed at ActionAid Ethiopia Addis Ababa Office Debre Zeit road, inside CCRDA compound (Kality, in front of Kality drivers training center) upon request starting from Ist day of the announcement.
  3. Bidders are eligible to collect bid document only for one Lot and must indicate clearly on which Lot they are Competing.
  4. The bidders should attach their VAT registration -TIN Number registration certificate.
  5. The date for submission of tender document is on 10th date at or before 2:00 PM (bid closing time).
  6. The bidder must provide complete set of technical document and financial documents separately.
  7. Bid opening date will be on the same day of bid closing at 2:30 P.M in the presence of bidders or their legal representatives at the ActionAid Ethiopia Addis Ababa office. If there is public holiday on this date the closing and opening of the bid will take place on the next working date at the same time and venue.
  8. Bidders may obtain further information and inspect the bidding document at ActionAid Ethiopia, Tel.0114654671.
  9. The Employer reserves the right to reject any or all bids.

ActionAid Ethiopian

Addis Ababa, Ethiopia

Construct the Clinic and raw material weigh bridge area’s toilet septic tank within a completion period of 90 calendar days.

Published on:Reporter ( Nov 1, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission (Check it)

Bids will be delivered to the address below on or before 10:00 PM of the following 10 Calendar days starting from the day of invitation to bid posted on newspaper.

INVITATION FOR BID

Bid No.02C& RMWST/2020

HABESHA CEMENT SHARE COMPANY

RENOVATION AND CONSTRUCTION OF CLINIC

AND SEPTIC TANK FOR RAW MATERIAL WEIGH

BRIDGE AREA TOILET.

Habesha Cement Share Company invites sealed bids under National Competitive Bid (NCB) for eligible firms to construct the Clinic and raw material weigh bridge area’s toilet septic tank within a completion period of 90 calendar days.

  1. Contractor must be duly registered by the Ministry of Urban Development and Housing /Construction with BC 7/ GC 8 and above with valid license for the year 2020
  2. Interested eligible bidders may obtain further information from and inspect the bidding document of the office of Habehsa Cement located at Wollo Sefer ( Kasma building 8th floor), from the Department of Procurement and Civil Engineering Division 8:30 am to 12:30 pm and 1:30 pm to 5:30 pm Monday to Friday during working days.
  3. A complete set of bidding documents can be purchased with payment of a non-refundable fee of ETB 300.
  4. The method of payment will be in cash against receipt
  5. The provisions in the Instructions to Bidders and in the General Conditions of Contract are the provisions of the PPA Standard Bidding Documents: Procurements of works 2011.
  6. Bids will be delivered to the address below on or before 10:00 PM of the following 10 Calendar days starting from the day of invitation to bid posted on newspaper.
  7. Bids will be opened in the presence of bidders’ representatives who choose to attend at Habesha Cement Share Company on the same day at 10:30. AM.
  8. The address referred to above is: Habesha Cement Share Company, Addis Ababa, EthioChina Friendly Street, Kasma Building, 8th Floor, Tel No: 0930034293, 0930034298, 0904033975, Fax No: 0114667044, P.O.Box 3317
  9. Tenders shall be valid for a period of 60 days after bid opening.
  10. Habesha Cement Share Company reserves the right to reject all or part of the bid.

Habesha Cement Share Company

Construction of fence and Leveling of the Compound in UNHCR Aysaita residence-

Published on:The Reporter ( Oct 31, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa 
Remaining Time for Bid Submission (Check it)

TENDER NOTICE

The Representation Office of the United Nations High Commissioner for Refugees (UNHCR) in Ethiopia, Addis Ababa invites competent, reputable and registered companies(international) to participate in the below tender:

  • REQUEST FOR PROPOSAL-Construction of fence and Levelling of the Compound in UNHCR Aysaita residence-RFP/HCR/AA/2020/005

The closing date is 09 November 2020- 16H00- Ethiopian time Details of the above-mentioned bid document should only be requested through email, by sending your request to ETHADSMS@unhcr.org.

Working hours: Monday to Thursday from 09:00-12:00 and 14:00-16:00 Friday from 09:00-14:00

Tender documents can be requested effective from 26 October to 07th November 2020.

The tender submission should comply with requirements raised in the request for proposal document and must be type-written/computer-generated/PDF.

Closing date for receipt of tender documents is 09 November 2020- 16H00 Ethiopian Time . No submission after this deadline shall be accepted.

UNHCR Representation

Addis Ababa Ethiopia

Supply Management Services

በአፋር ክልል የግንባታ ስራዎች

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 21፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አፋር ክልል ገቢረሱ ዞን
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

 ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአፋር ክልል በገቢረሱ ዞን አሚባራ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማት ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት ለሚያከናውናቸው የግንባታ ስራዎች ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

በጨረታ የሚሰሩ ስራዎች የሚከተሉት ይሆናሉ፡-

  1. የተስኩቲ ማዕከል የውሃ መስመር ዝርጋታ
  2. ከላይቶ ት/ት ቤት ጥገና
  3. ባድሃሞ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ባለ ሁለት ክፍል ላብራቶሪ እና ላይብረሪ ግንባታ
  4. ኩስራ ጤና ኬላ ጥገና
  5. ሲደሃፋጌ ጤና ጣቢያ የሴፕቲክ ታንከር ግንባታ
  6. ተስኩቲ ማዕከል የጽ/ቤት ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡-

  • ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ፍቃዳቸውም በ2013 ዓ.ም የታደሠና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የጨረታውን ሰነድ በአሚሰራ ወረ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ብር 100 የማይመለስ ስመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ ቀናት የሰነድ ሽያጭ ይከናወናል፡፡

በአፋር ክልል ገቢረሱ ዞን

አሚባራ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ልማት

ጽ/ቤት

Construction of :- Supply and laying Borehole collector & transmission main pipe work, water conveyance system, masonry Reservoirs, water points, break pressure tank, cattle trough and guard house etc

Published on:Ethiopian Herald ( Oct 29, 2020 )Place of Bid Competitions:Dire Dawa
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

INVITATION FOR BIDS

FEDERAL DEMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA ONE

WASH NATIONAL PROGRAM

  1. The Federal Democratic Republic of Ethiopia has received financing from the Consolidated WaSH Accounts (CWA) toward the cost of the project implementation of One Wash National Program II, and intends to apply part of the proceeds toward payments under the contract for Construction of Civil Works for Jeldessa woreda, Ayale gumgum Qabele Multi-village Rural Water Supply System
  2. The Dire Dawa Water, Mines & Energy Office now invites sealed bids from eligible bidders for construction of Civil Works for Jeldessa woreda, Ayale gumgum Qabele Multi-village Rural Water Supply System. Project ID P167794No.BID Ref. No.Description of Works1ET-Dire Dawa WB199523-CWRFBConstruction of :- Supply and laying Borehole collector & transmission main pipe work, water conveyance system, masonry Reservoirs, water points, break pressure tank, cattle trough and guard house etc
  3. Bidding will be conducted through the National Competitive Bidding (NCB) procedures and is open to all eligible bidders.
  4. Interested eligible bidders may obtain further information from the address below and obtain the bidding documents during office hours 09:00AM to 05:00 PM.
  5. Bidder shall meet the following minimum qualifying criteria to qualify for award of the contract, 
  • a. Minimum average annual construction turnover of ETB 26,250,000.00 calculated as total certified payment received for contracts in progress or completed within the last 3 years.
  • b. The bidder must demonstrate access to, or available of financial resources such as liquid assets, lines of credit and other financial means, other than any contractual advance payments to meet the construction cash flow requirement estimated as ETB 4,000,000.00
  • c. Experience under construction contracts in the role of prime contractor, subcontractor, or management contractor for at least the last 5(live) years, starting from 8th July 2015,

6. A complete set of bidding documents in English may be purchased by interested eligible bidders upon the submission of a written application to the address below and upon payment of a nonrefundable fee of ETB 300 (Three Hundred Birr). The method of payment will be Cash against receipt

7. Bids must be delivered to the address below on or before 25th November 2020, 9:30AM Electronic bidding will not be permitted. Late bids will be rejected. Bids will be publicly opened in the presence of the bidders’ designated representatives and anyone who choose to attend at the address below on 25 November 2020,10:00AM.

8. All bids must be accompanied by a Bid Security of ETB 400,000(four hundred Thousand) in freely convertible Currency.

9. The address referred to above is:

Dire Dawa Water, Mines & Energy Office

Address: Via number one road in front of Dire Dawa

Administration Federal Prison

P.O.box 18, Dire Dawa; Ethiopia Tel. +251-25-111-3358, Fax +251-25-111-11-32

URRAP Bridge Construction Projects with approach Roads

Published on:Ethiopian Herald ( Oct 29, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

NOTICE OF INVITATION FOR BID

Procurement Reference Number: ORA/NCB/RFP/CP-04/2013

NOTICE OF INVITATION FOR BID

Procurement Reference Number: ORA/NCB/RFP/CP-04/2013

1.The National Regional State of Oromia has allocated budget towards the cost of URRAP Bridge Construction Projects with approach Roads and intends to apply part of this budget to payments for the under listed projects. The Bridge Name, Location, Span Length, Amount of bid security, Minimum Annual construction turnover (ACT), and the total period of construction including the required mobilization time, for each Bridge project, is indicated in the table below;

No Bridge River NameSpan Length(M) Zone Aana  (Woreda) Bid Bond AmountDuration of the works including 45 days Mobilization Period (Cal.Days) Peak Annual Construction Turnover (ACT) 
1Muka Arba 40West Wellega M/Sibu115,400.00 54815,000,000.00 
2Birbir52West Wellega S/Nole155,000.00 54820,700,000.00 
3Suchi24West Wellega Ayira64,600.00 45610,300,000.00 
4Suphe24Kellam WellegaJ/Horo100,400.00 45616,100,000.00 
5Qobi24Kellam WellegaJ/Horo98,800.00 45615,800,000.00 
6Gerba Guracha32West ArsiNansebo109,900.00 54814,600,000.00 
7Unke39ArsiShanan Kolo130,900.00 54817,500,000.00 
8Gogesa (with 1.6km Approach Road)88North ShoaDara298,400.00 73029,800,000.00 
9Balal60BorenaTaltale140,700.00 73014,100,000.00 
10Iyya (with 4.5 km Approach road)32BaleM/Welabu472,400.00 54863,000,000.00 

2. The Oromia Roads Authority (ORA) now invites eligible bidders to submit sealed bids for providing the necessary labor, material, and equipment for construction works of the above Bridge projects.

3. Interested bidders shall submit the following evidence:

The bidders shall have a certificate of competency from Oromiya Construction Authority or Ministry of Federal Construction with Category; As the table below for each Bridge project, renewed for the bidding period and other appropriate documentary evidence demonstrating the bidder’s compliance, which shall include:

i. Trading /Business License renewed for bid period and Commercial Registration Certificate from authorized bodies.

ii. VAT & Tax payer Identification Certificate issued by the tax authority,

iii. Tax Clearance certificate issued from the Tax Authority (Inland Revenue Authority) which allows the bidder to participate in public tenders at the date of the deadline for bid submission.

iv. Evidence of/Being/ Registered at Ethiopian Public Procurement and Property Administration Agency(PPAA) Supplier list.

NoBridge Name Span Length (M) Category 
1Muka Arba 40GC-6/RC-6/BC-6 & Above 
2Birbir52GC-6/RC-6/BC-6 & Above 
3Suchi24GC-6/RC-6/BC-6 & Above 
4Suphe24GC-6/RC-6/BC-6 & Above 
5Qobi24GC-6/RC-6/BC-6 & Above 
6Gerba Guracha32GC-6/RC-6/BC-6 & Above 
7Unke39GC-6/RC-6/BC-5 & Above 
8Gogesa (with 1.6km Approach Road)88GC-5/RC-5/BC-4 & Above 
9Balal60GC-5/RC-5/BC-4 & Above
10Iyya (with 4.5 km Approach road)32GC-5/RC-5/BC-4 & Above

4. Bidding will be conducted through the National Competitive Bidding (NCB) procedures and is open to all eligible domestic bidders as specified and defined in the bidding document.

5. Interested eligible bidders may obtain further information and inspect the bidding documents, including a complete set of Engineering Drawings which is necessary for bidding purpose, at the address given below at office working hours. A complete set of bidding documents prepared in English language may be purchased by interested bidders on the submission of a written application to the address below and a non refundable fee of ETB 500.00 (Five Hundred Birr only) for each Bridge Project, effective from the first date of announcement up to deadline. The method of payment shall be in cash to the ORA’s Head Office Cashier.

6. Bidders can apply for one or for all or for any number of Bridges projects from the above listed Bridge projects and shall submit their bid separately for each Bridges project, they are interested to apply for.

7. Bidders shall submit One Original and two photocopies for both Technical proposals and financial offer. Technical proposal will be sealed in such a way that one original and one photocopy to be sealed in one envelope while the second photocopy will be sealed in another envelope separately and labeled as “One ORIGINAL & One PHOTOCOPY” and “Second PHOTOCOPY” respectively, then placed in another outer envelope along with bid security as indicated in the above table, in an acceptable form as indicated in bidding document. Financial proposal will be sealed in such a way that one original and one photocopy to be sealed in one envelope while the second photocopy will be sealed in another envelope separately and labeled as “One ORIGINAL & One PHOTOCOPY” and “Second PHOTOCOPY” respectively, then placed in another outer envelope. Finally the whole documents shall be placed in a single wax-sealed envelope whose outer cover containing all necessary information about the firm & Employer including project information.

8. Bids must be delivered to the address below on or before November 30, 2020 at 10:00 A.M. All bids must be accompanied by a bid security indicated in the above table. Late bids will be rejected. Qualification Application, Financial offers, and Bid security of the bidders will be opened by the Oromia Roads Authority in the presence of bidders’ representatives who choose to attend at the address below on the final date and 30 minutes after bid submission as stated above.

9. Evaluation is to be carried out in two stages, Qualification Information First and Financial Bids of Qualified bidders next. Financial Proposal of qualified bidders will be opened at the same address given below on the date that is to be declared by the Authority’s Bid Endorsing Committee after completion of the evaluation of Technical Proposals. Unqualified Bidders’ Financial Proposal will be returned unopened to the Bidder.

10. The Bid validity period shall be: 118 Calendar days after the latest date for submission of bid.

11. Oromiya Roads Authority reserves the right to reject any bid and to annul the bidding process and reject all bids at any time, without thereby incurring any liability to Bidders.

Oromiya Regional Government Sectorial Office A building at Sarbet.

Office of Oromia Roads Authority,

3rd Floor, Procurement Directorate

Email: info@oromiaroadsauthority.org

Website:www.oromiaroadsauthority.org

P. O. B. 42937

Finfinne, Ethiopia

Oromia Roads Authority

የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በክልሉ የተሰሩት የስድስት የማቀነባበርያ ፋብሪካ የአጥር (ሲቲ፣ ፋፈም፣ ጀረር፣ ቆረሄ እና ኤረር ዞን) ሥራ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 19፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ጅጅጋ ሶማሌ ክልል
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር SRS-BDB/FFW/18/2013

የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በክልሉ የተሰሩት የስድስት የማቀነባበርያ ፋብሪካ የአጥር (ሲቲ፣ ፋፈም፣ ጀረር፣ ቆረሄ እና ኤረር ዞን) ሥራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ አና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሱ በጨረታው አንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጅጅጋ ከሚገኘው የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በመገኘት የስራውን ዝርዝርና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመከፈል መግዛት ይቻላሉ፡፡
  4. በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ስራ ላይ የሰሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በስምንተኛው የስራ ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት ጅጅጋ ይከፈታል፡፡
  6. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር +251 25 77 53 595/96

ፋክስ ቁጥር +251 25 7753 598

ጅጅጋ ሶማሌ ክልል

የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ

ልማት ቢሮ

Sub Contract Cutting, Bending and Fixing in position Reinforcement Bar ለፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ 4+B+21 የቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 19፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ፡ECWCL/NCB/-PW/36/2013

  1. Sub Contract Cutting, Bending and Fixing in position Reinforcement Bar ለፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ 4+B+21 የቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት ለማሰራት ብቁ የሆኑ ንዑስ ተቋራጮችን በሃገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋ 1% ( በመቶ) ነገር ግን ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) የማይበልጥ በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው::
  4. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፣ ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር ተዛማጅ የሆነ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከአገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት እና ቅዳሜ እስከ 6፡30 በግዢ መምሪያ (የህንጻ ቴክኖሎጂ እና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ግዢ ቡድን ) በመቅረብ ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበትቀን ጀምሮ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ህዳር2 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ሲሆንጨረታው ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ህዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ጊቢ በሚገኘው የግዥ መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7.  ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ከመገናኛ ወደ አያትበሚወስደው መንገድ በግራ በኩል ጉርድ ሾላ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንጻ 200 ሜትር ገባ ብሎአንድነት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር +251 118 72 30 86

Fax +251 6 67 60 90

Pobox 21 952/1000 አዲስ አባባ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን

Duct and Manhole Construction at Bahirdar Industry Park

Published on:Addis Zemen ( Oct 29, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

Invitation to National Bid for the

procurement of Duct and Manhole Construction at Bahirdar Industry Park (LOT 4)

  • Floating Date: As of October 30, 2020
  • RFQ No: 4041065
  • Closing date: November 20, 2020

Ethio Telecom invites interested and eligible bidders in this bid for the procurement of Duct and Manhole Construction at Bahirdar Industry Park (LOT 4).

  • Bid Remains under floating starting from October 30, 2020 Submission deadline: November 20, 2020 (until 05:00 PM)
  •  Opening date: November 21, 2020 (at 10:00AM)
  • Bid documents can be obtained from ethio telecom’s HeadOffice, Room No. 201 during office hours (Monday to Friday) upon payment of a non-refundable fee of Birr 100.00(Birr one hundred only).
  1.  All Bids must be accompanied by a bid security in the amount of Birr 162,000.00 (One hundred sixty-two Thousand Birr only).

1.1. The bid bond shall be furnished in the format specified in the bid document.

Ethio Telecom’s Head QuarterSupply Chain Division2nd floor, Room No. 211BChurchill Road

P. O. Box 1047, Addis Ababa, Ethiopia.

2. Bidders are seriously advised to read and comply with the instructions provided in the bidding document and can obtain detailed information on the Ethio telecom web address.

3. Ethio telecom reserves the right to reject all or parts of this bid.

4. No one is allowed to duplicate or transfer the bidding document that she/he acquired to participate under this invitation. Legally authorized agents shall collect the bidding documents for each principal they are representing.

  • NB: – bid documents are available only on softcopy. Thus, bidders should come up with flash/CD.
  • For more information, please visit ethio telecom official web
  • site: – www.ethiotelecom.et 

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዊል ሉደር (2008 ስሪት) እና ኤክስካቫተር ለመሽጥ ይፈልጋል::

Published on:Reporter ( ጥቅምት 18፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሱ ያቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁየተበዳሪ ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪ ቅርንጫፍየመያዣ አይነትየሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥር/ሴሪያል ቁጥርየሞተር ቁጥርየጨረታ መነሻ ዋጋ በብርጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓትጨረታው የወጣው
1በርሞግ ኮንስትራክሽን ኃ/የተግ/ማህበርተበዳሪኢምፔሪያል ዊል ሉደር (2008 ስሪት)ሥክ- L D-0845 N1A02463 C7C12932 900,000.00 ሕዳር 03 ቀን 2013 ከሰዓት በኋላ 8፡009፡00ለመጀመሪያ ጊዜ
2አቶ ቴዎድሮስ አበራ ኦዳተበዳሪገርጂ ኤክስካቫተርEX-0794 HHKHZ703JC000023726483560 4,300,000.00 ሕዳር 03 ቀን 2013ከጠዋቱ 4፡00 -5፡00ለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች፣

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ:: አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈሰትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሉ መክፈል አለበት:: ካልከፈሉ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቅርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ:: ላላሽነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
  2. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው::
  3. ጨረታው የሚከናወነው በተራ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተው በባ……… ሲሆን ፤ ተራ ቁጥር 2 ላይ የተመለከተው ደግሞ በትግራዊ ብሔራዊ ክልል፤ አክሱም ከተማ በሚገኘው በባንኩ አክሱም ቅርንጫፍ ነው::
  4. የተጫራቾች ምዝገባ ከአያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
  5. የስም ማዛወሪያ ክፍያ፤ ዓመታዊ የቦሎ ክፍያና እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል::
  6. ለጨረታ የቀረሱት ንብረቶች ቀረጥ ያልተከፈለባቸው ስለሆነ ገዢ ከቀረጥ ነፃ መብት ያለው መሆን ይኖርበታል፤ ካልሆነ ደግሞ ቀረጡን እና ተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል የሚጠበቅበት ይሆናል::
  7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለፀውን በተመለከተ አክሱም ቅርንጫፍ (0342757717) በመቅረብ ለመጎብኘት ይችላሉ::
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 011-1-58-08-63/0111-26-36-09 (ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በዋናው መ/ቤት የሕንፃ ግራውንድ ውስጥ የሚጠራቀመውን ፍሳሽ ለማስወገድ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 18፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር ብ/ግ/ጨ /01/2013

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን በዋናው መ/ቤት የሕንፃ ግራውንድ ውስጥ የሚጠራቀመውን ፍሳሽ ለማስወገድ በዘርፉ የተሰማሩትን በደረጃ 7 እና ከዚያ በላ በGC፤ WC እና BC የሆናችሁትን በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚህ ጨረታ ላይ በመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች

የሚከተሉትን ማሟላት አስባችሁ፡-

  1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፡፡
  2. የታክስ እና የግብር ግዴታቸውን የተወጡና የቲኢቲ ከፋይ፡፡
  3. የምዝገባ ሰርትፍኬት፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም ጋራንቲ 300,000.00 (ሦስት ሺህ ብር)፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከባለስልጣን መ/ቤቱ 9ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 903 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ላይ ከዋለ የጨረታ መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ስዓት ይከፈታል፡፡
  7. ባለስልጣን መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ

ባለስልጣን

የከፍተኛ ፍ/ቤት አጥር እና የግቢ መግቢያ በር ስራ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 18፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን 
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2013 ዓም የበጀት ዘመን ሊያሰራ ላቀደው የከፍተኛ ፍ/ቤት አጥር እና የግቢ መግቢያ በር ስራ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 6/GC-6/ BC-6/ እና ከዚያ በላይ፡፡

  1. ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግሉ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ምስክር ወረቀት ኦርጅናሉን ይዞ በመቅረብ በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስተዳደር የቢሮ ቁጥር 9 የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300 ብር በመከፈል ሙግዛት ይጠበቅባችኋል፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ፣ የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ፣የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ የምስክር ወረቀት በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
  4. 5. ተጫራቾች የገዙት ሰነድ /ፋይናንሻል እና ቴክኒካል/ ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱ ለየብቻ በሰም በታሸገ እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም በመምታት፣ ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናል ኮፒ የሚል ፅሁፍ መፃፍ አለበት፡፡
  6. ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
  7. እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፣ የተቋራጩ አድራሻና የተወካዩን ስልክ ቁጥር በሙግለፅ መፃፍ አለበት፡፡
  8. ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ አስተዳደር የቢሮ ቁጥር 9 ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ስማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/ አስተዳደር የቢሮ ቁጥር 9 ከጠዋቱ 4፡30 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  • ለበለጠ መረጃ ፦ በስልክ ቁጥር 0473351027/0473351278/0473350090

የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት

ሚዛን አማን

You cannot copy content of this page