The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

Ethiopia

ዶዘር፣ ግሬደር ኤክስካቫተር፣ ሮለር እና ሎደር

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 17፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ሃዋሣ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደመባ 02/01/2013

መ/ቤታችን የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን በሥሩ ላሉት ዲስትሪክቶች አገልግሎት የሚውሉ የኮንስትራክሽን እና ሲቪል ኢንጅነሪንግ መሣሪያዎች መገልገያ ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር ኤክስካቫተር፣ ሮለር እና ሎደር ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት፣ መንግስት መ/ቤቶች በሚያወጡት የጨረታ ማስታወቂያ ላይ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ በማድረግ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ «ኦርጅናል» እና «ኮፒ» በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የየሎቱን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 8 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው::
  5. አቅራቢዎች ጨረታውን ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8.00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል:: ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 0.5% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስረከቢያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  7. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8.  መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን

አቅ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት

የፖ.ሣ.ቁጥር 688

የስልክ ቁጥር 046-220-55-91/046-220-98-90

ፋክስ 046-220-23-66/046220-29-13

ሃዋሣ ኢትዮጵያ

ደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን

…ኤክስካቫተር በአካፋና በጃክ ሀመር ለመከራየት ይፈልጋል:

Published on:Reporter ( ኅዳር 13፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

 የጨረታ ማስታወቂያ

ናሽናል ሲሚንቶ አማ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::

ተ/ቁየማሽኑ ኣይነትመለኪያሞዴልየሚፈለገው ብዛትየሰዓት ዋጋ ከቫት በፊት
1ኤክስካቫ ተር በአካፋና በጃክ ሀመርበቁጥር 2 

በመሆኑም ተጫራቾች

  • የአካፋ መጠኑ 1.5m3 ወይም ከዛ በላይ እንዲሁም ስሪቱ ከ2016 በኋላ የሆነና የቴክኒክ  ብልሽት ያላጋጠመው::
  • በአካፋም ሆነ በጃክ ሀመር ችሎታ ያለው ኦፕሬተር ማቅረብ የሚችሉ::
  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ::
  • በሠንጠረዡ ላይ የተገለጹትን ማሽነሪዎች የዕዓት ዋጋ በግልጽ በማስቀመጥ ኢትዮ ቻይና ፍሬንድ ሺፕ መንገድ kf ህንጻ 1ኛ ፎቅ ወሎ ሰፈር አአ. ስልክ፡ 0986894464/251 11 4 42 19 28/ ግዢ ክፍል እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ ስልክ ቁጥር 0946-43-93-94/0935-98-50-83 ግዢ ክፍል በታሸገ ፖስታ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ::
  • የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ባሉት 20 የስራ  ቀናት የሚቆይ ሆኖ ማለትም በህዳር 29/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ጨረታው ተዘግቶ  ታህሳስ 2/2013 ዓም ድሬዳዋ በሚገኘው ናሽናል ሲሚንቶ ኤማ ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
  • ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

ማሳሰቢያ፡-

  • ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውሳኔ ይስጥበታል:: መ/ቤቱም የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
  • ድርጅቱ !

Rental of different Construction Machinery

Published on:Reporter ( Nov 22, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

INVITATION FOR BID

BID NO. OBMCSC-02/2013

OBM Construction Share Company invites all interested and eligible bidders for rental of different Construction Machinery and vehicles



Lot No.
DescriptionQuantity
1

Excavator
1
2Bulldozer1
3Wheel loader2
4Dump truck
2
5Water truck1
6Double Cabin pick up1
  1.  Interested bidders can obtain complete bid documents up on payment of non-refundable 100 (one hundred) birr before December 3, 2020 from the address mentioned below.
  2. . Bidders shall deposit or pay 2% bid bond of their offered total price in the form of CPO or bank document.
  3.  Bidders must submit their offers in authenticated sealed envelopes.
  4. . All bidders requested to have renewed business license for the current year, TIN registration certificate.
  5. The bid closing date shall be December 4, 2020 at 4:00 Am local time. Bid shall be opened in the same date at 4:30 AM local time in the presence of bidders or their legal representatives in our head office Meeting room.
  6.  OBM Construction Share Company reserves the right to reject any part or all bids.
  • OBM CONSTRUCTION SHARE COMPANY, Lideta Sub City, Biftu Building 5th Floor, In front of Addis Abeba Commercial School. I
  • Tel. 0118362024, 0118362025, 0118362029

ዶዘር፣ ሎቤድ፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ እሰካባተር ፤እናደምትራክ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 13፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

[

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በጅማ ዞን የመንቶ ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት የንግድ ድርጅቶች እና ጥቃቅንና አነስተኞችን በግልፅ ጨረታ አወዳድር የመንገድ ሥራ ማሽኖችን (ዶዘር፣ ሎቤድ፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ እሰካባተር ፤እናደምትራክ) ለመከራየት ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት የመወዳደሪያ መሥፈርቶች፡

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ::
  2. የዘመኑ ግብር የከፈለበትን ማስረ ጃ ማቅረብ የሚች
  3. በንግድና ከተማ ልማት ጽ/ቤት በስነስርዓት ጉድለት ያልተከሠሡ።
  4. የግብር መለያ ቁጥር (TN NO ) ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የፌዴራል እና የፋይናንስ ግዢ ስርዓት አስተዳደር የሚያከብር፡፡
  6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ vAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  7. . ተወዳዳሪዎች የአቅራቢት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው
  8. ተወዳዳሪው በሰነዱ ላይ ትክክለኛአድራሻ፣ ስም እና ፊርማ ማሳረፍ አለባቸው
  9. . የጨረታው ማስከበሪያ ማረጋገጫ የሚሆን 15000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ።
  10. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ህጉ በሚፈቅደው መሠት 2% (ሁለት ፐርሰንት) የመክፈል ግዴታ አለበት።
  11. ጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ከሙስና እና ከመሰል ነገሮች ነጻ መሆን አለባቸው
  12. . ጨረታው የሚከናወነው ሰነዱ በወጣበትቋንቋ መሠረት ይሆናል።
  13. ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ሰነድ እንድም ገጽ ሳያጎሉ ጎልተው መመለስ አለባቸው፡፡
  14. የመንገድ ሥራ ማሽኖችን ( ዶዘር ሎቤድ፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ እስካቫተር እና ደምትራክ) በጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ ማቅረብ የሚችል ::
  15. . ተወዳዳሪዎች ለማሽኑ የሚያስፈልገውን ነዳጅ ማቅረብ የሚችል (የነዳጅ ዋጋይጨምራል
  16. የንብረቱ ባለቤትነት ፡ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ የሚችል።
  17. አገልግሎት ዘመን (207-2020 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር) ያልበለጠ መሆን አለበት።

የጨረታው ሰነድ ሳጥን የሚዘጋው 2/4/2013 ዓም 4፡00 ሰዓት ሆኖ የሚከፈተው2/4/2013 ዓም 4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ከላይ 1-17 የተዘረዘሩት ነጥቦችን ማሟላት የምትችሉ ከመንቾ ወረዳ ሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር ቀርባችሁ የማይመለስ የኢትዮጵያ 200 (ሁለት መቶ) ብር ከፍላችሁ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀን ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ።

የጨረታው መከፈቻ ቅዳሜና እሁ፡ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0913254666/0917069994

በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ

ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት

ግሬዴር/Grader 140H/K-model 2014 -2018፤ኢስካቫተር /Excavator/140H/K model 2014-2018 ና ደብል ፒካ አፕ /Double pick up (Model 2016 and above)እና ለጭነት ግሬደር፤ እስካቫተርና ባወጣነው እስፔስፊኬሽን መሰረት ደርሶና መልስ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 13፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጮመን ጉዱሩ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጮመን ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለ2013 ዓ.ም በግልጽ ጨረታ የሚከራይ የሥራ ፕሮጀክት ማሽን ለሚሳተፉ ተጫራቾች የተዘጋጀ የተወዳዳሪዎች መመሪያ፡፡

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጮመን የጉዱሩ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለጮመን ጉዱሩ ወረዳ የመንገዶች ባለስልጣን ሥራ ፕሮጀክት የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ማሽኖች፤ የግሬዴር/Grader 140H/K-model 2014 -2018፤ኢስካቫተር /Excavator/140H/K model 2014-2018 ና ደብል ፒካ አፕ /Double pick up (Model 2016 and above)እና ለጭነት ግሬደር፤ እስካቫተርና ባወጣነው እስፔስፊኬሽን መሰረት ደርሶና መልስ ማቅረብ የሚችል ፍላጎት ያለው ተጫራች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማቅረብ የሚፈልግ ::

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች 

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለቸው፡፡
  2. የ2013 ዓ.ም.ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ፡፡
  4. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማሽኖች በአንድ ላይ ጠቅልሎ ማቅረብ የሚችል ሲሆን ለያይቶ ወይም ነጣጥሎ ማቅረብ አይችልም::
  5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ (supply list) የተመዘገቡና ማስረጃ ያለቸው፡፡
  6. የአሸነፈበትን ማሽን እስከ ጮመን ጉዱሩ ወረዳ መንገዶች በለስልጣን ጽ/ቤት የስራ ቦታ ድረስ በራሱ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ማንኛውን ተጫራቾች የማሽኖች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ከነዳጅ ፍጆታ ጋር ብቻ መሆን አለበት፡፡ (All Rental cost Machine with fuel only)
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ( Bid Bond) የሚመለስ ገንዘብ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ (CPO)20,000 (ሃያ ሺህ ብር ) ቀጥታ ለጮማን ጉዱሩ ወረዳ መንገደች ባለ ሥልጣን መፃፍ ያለበት ከጨረታው ሰነዱ ጋር ጨረታ ከመዘጋቱ በፊት ማሰያዝ ይኖርበቻዋል፡፡
  9.  የጨረታ ሰነዱ ሰርዝ ድልዝ ቢኖረው ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bank Grant 10% የዋስትና አያይዞ ማቅረብ አለበት::
  11.  ሰነዱን የፋይናንስ እና ቴክኒካል ፕሮፖዛል ላይ ኮፒ እና ኦርጂናል ብቻ ለብቻው በተለያየ ፖስታ ታሽጎ በአንድ ፖስታ አብሮ መቅርብ አለበት፡፡
  12. ይህ ማስታቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጮመን ጉዱሩ ወረዳ መንገዶች ባለስልጣን ጽ/ቤት በመቅረብ ዋጋ ማቅረቢያዎችን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  13. የጨረታ ሰነዱን ተጫራቾች ጮመን ጉዱሩ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር ቀርበው ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
  14. የጨረታ ሳጥኑ 15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡
  15. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  16. አሸናፍው ድርጅት የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ እና የውል ስምምነት መፈረም አለበት፡፡
  17. አሸናፊው ድርጅት ግሬደር እና እስካቫተር ማሽን በስራ ቦታ ማቅረብ የሚችል፡፡
  18. የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ይሆናል፡፡
  19. ተጫራቾች ከሚከተሉት አንዱን ሳያሟሉ ቢቀሩ ከውድድሩ ይሠረዛሉ፡፡
  20. የሥራ ፕሮጀክት ማሽን ዋጋ የምንከፍለው አሸናፊው ድርጅት አሸንፎ ውል የገባባቸውን የሥራ ፕሮጀክት ማሽን ሙሉ በሙሉ በፕሮጀክቱ ቦታው (on site) ታይቶ ካስረከቡ በኋላ 20% ይከፈላል።
  21. ግልጽ ያልሆነ ሊታይ ወይም ሊነበብ የማይችል ንግድ ፍቃድና ሌሎች አብረው የሚቀርቡ ማስረጃዎች ካላቀራቡ ውድቅ ይሆናል፡፡
  22.  መ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ መሠረዝና የሚወስዳቸው አግልግሎት በ20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 20 42 47 54 ደወሉ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የጮመን ጉዱሩ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

ኤክስካቫተር ካት ሞዴል16፣ ግሬደር ካት ሞዴል 16፣ሩሎ ካት ሞዴል 16፣ ሻወር ትራክ፣ ዳምትራክ፣

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 12፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ጅማ ዞን የዴዶ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በጅማ ዞን በዴቻ ወረዳ ገ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት ለመንገድ ግንባታ ስራ የሚውሉ ማሽኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ኤክስካቫተር ካት ሞዴል16፣ ግሬደር ካት ሞዴል 16፣ሩሎ ካት ሞዴል 16፣ ሻወር ትራክ፣ ዳምትራክ፣ በሰዓትና በቢያጆ የነዳጅ ወጪን ጨምሮ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት የመወዳደሪያ መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፡፡
  2. የዘመኑ ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  3. 3በንግድና ከተማ ልማት ጽ/ቤት በስነስርዓት ጉድለት ያልተከለሰ፡፡
  4. የግብር መለያ ቁጥር (TIN NO) ማቅረብ የሚችል፡፡
  5. የፌዴራል እና የፋይናንስ ግዥ ስርዓት አስተዳደር የሚያከብር፡፡
  6. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ተወዳዳሪዎች የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ተወዳዳሪው በሰነዱ ላይ ትክክለኛ አድራሻ ስም እና ፊርማ ማሳረፍ የሚችል፡
  9. የጨረታው ማስከበሪያ ማረጋገጫ የሚሆን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚችል፣
  10. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ህጉ በሚያዘው መሰረት 2% (ሁለት ፐርሰንት) የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
  11. ጨረታው ላይ የምትሳተፉ ተጫራቾች ከሙስና እና ከመሰል ነገሮች ነጻመሆን አለባችሁ፡፡
  12. ጨረታው የሚከናወነው ሰነዱ በወጣበት ቋንቋ መሠረት ይሆናል፡፡
  13. ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ሰነድ አንድም ገጽ ሳያጎሉ ሞልተው መመለስ አለባቸው፡፡
  14. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ኤክስካቫተር ካት ሞዴል 16፣ ግሬደር ካት ሞዴል 16፣ ሩሎ ካት ሞዴል 16፣ የግል የባለቤትነት ማረጋገጫ (ሊብሬ) ማቅረብ የሚችል፡፡
  15. የኤክስካቫተር ካት ሞዴል 16፣ ግሬደር ካት ሞዴል16፣ሩሎ ካት ሞዴል 16፣አገልግሎት 2017-2020 (እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር) የሆነ፡፡
  16. ተወዳዳሪዎች ከ3 በላይ ወረዳ ከዚያ በላይ ቦታዎች የሰራበትን በጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  17. የጨረታው ሰነድ ከ12/3/2013 እስከ 21/3/2013 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ በዴዶ ወረዳ ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 7 ቀርባችሁ የማይመለስ የኢትዮጵያ 200 (ሁለት መቶ ብር) ከፍላችሁ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
  18. የጨረታው ሰነድ ሣጥን በ21/3/2013 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት በዴዶ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር … ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካይ ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0917 87 8961/0913 50 6829/0945 03 4139

በጅማ ዞን የዴዶ ወረዳ ገ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት

ዶዘር D8R cater pilar :ግሬደር 180 HP CAT pillar :እስካቫተር Hitachi (Catter Pillar)

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 11፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለገጠር መንገድ ስራ የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎች እስከ ሥራ ቦታ ማለትም ከላላ ቱሉ ጫሊ ትምህርት ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የማሽኑ ዓይነት፡-

  1. ዶዘር D8R cater pilar የተመረተበት ጊዜ እ.አ.አ.ከ 2014 ወደዚህ የተመረተና 300 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. ግሬደር 180 HP CAT pillar የተመረተበት ጊዜ እ.አ.አ 2014 ወደዚህ የተመረተና 180 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል :
  3. እስካቫተር Hitachi (Catter Pillar) HD 255 የተመረተበት ጊዜ እ.አ.አ.ከ 2014 ወደዚህ የተመረተና 255 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

የመወዳደሪያ መስፈር፡-

  1. የ2013 ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው።
  2. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፤ ቲን ነምበር ያላቸው ፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው ፤ እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት (supplier List) ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የማሽኑን ዝርዝር የሚገልፅ ዶክሜንት (Specification of Machineries ) የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ የጨረታ ዶክሜንት ከ12/3/2013 እስከ 28/3/2013 ዓ.ም ከጉደያ ቢላ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ቀርበው በመውሰድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም የታሸገ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሁሉም ማሽኖች ከታወቀ በባንክ የተደገፈ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ሥም ፣ አድራሻ፣ ማሕተም እና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራች ግብር መከፈሉን የሚገልፅ ከገቢዎች ባለስልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ::
  7. ጨረታው በ 28/3/2013 ዓም እስከ 3:30 ሰዓት ቆይቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ባለ ጉዳዩም ሆነ ህጋዊ ተወካይ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም ።
  8. ማንኛውም ተጫራች ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ከታወቀ በባንክ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት::
  9. ጨረታውን ያሸነፈ የቅድመ ክፍያ (Advance Payment) ለመውሰድ ከታወቀ ባንክ (Unconditional bond) ማቅረብ አለበት።
  10. ማንኛውም ተጫራች የማሽኑን ሊብሬ ማቅረብ አለበት ወይም ህጋዊ ውከልና ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  11. ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሠረት ማሽኖችን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  12. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ቅድመ ክፍያ የሚከናወነው ማሽኑን ወረዳ እንደደረሰ ይሆናል።
  13. ማንኛውም ተጫራች ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
  14. ጨረታ ያሸነፈ with holding tax 2% መቁረጥ ግዴታ አለበት።
  15. ማንኛውም ተጫራች የማሽኑን መግለጫ (Spesfication) ማቅረብ አለበት
  16. ጨረታውን ያሸነፈ አካል እስከ 5 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  17. ለነዳጅና ሠራተኛ ማመላለሻ የሚሆን የግሉ (የራሱ) የሆነ ተሽከርካሪ እስከ ሥራ ቦታ ማለትም ከላላ ቱሉ ጫሊ ት/ቤት ድረስ ማመላለስ የሚችል፣ ለማሸኖች ሁሉ ነዳጅ የሚያቀርበው የጨረታ አሸናፊ ይሆናል።
  18.  መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
  • ስልክ ቁጥር፡- 0936008854 / 0913163779

የጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

ሎደር : ግሪደር : ቼን ኤክስካቫተር…

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 11፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2013

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ቢ/ኮ አገልግሎት ጽ/ቤት በከተማ አስተዳደሩ በ3ቱም ቀበሌዎች ውስጥ ለሚሰራው የኮብል ስቶን መንገድ የመሬት ዝግጅት እና የጠጠር መንገድ ሥራ ለመስራት ያመች ዘንድ በማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡

ስለሆነም:-

  1. በዘርፉ የወጣ ንግድ ፈቃድና በዘመኑ የታደሰ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ፣
  2. መለያ ቁጥር /ቲን/ ፣ ሊብሬ፣ የቫት ተመዝጋቢነት የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የምትችሉ፣
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩት ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የማሽን ኪራይ አቅርቦቱ የማሽኑ የማጓጓዣ ወጪ፣ የጥበቃ፣ ሥራውን ሲሰራ የሚጠቀመው ነዳጅ በማሽን አቅራቢው የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  5.  ለሥራው የሚያስፈልገው ሎደር እና ግሪደር ከ200 ሰዓት በላይ፣ ሮሎ ባለ 16 ቶን 120 ሰዓት በላይ እና ቼን ኤክስካቫተር ከ70 ሰዓት በላይ የሚፈጅ ሲሆን ሥራውን ሙሉ ለሙሉ በተፈለገው መጠንና ዓይነት ሰርቶ ለማስረከብ ሁሉንም ማሽኖች በወቅቱ የማቅረብ ግዴታ ይኖርበታል፣
  6. ተጫራቶች በቀረበው ዝርዝር መሠረት የምታቀርቡበትን ከጥቅል ዋጋው ላይ 1% CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በአጣ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ጽ/ቤት ግቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ፣
  7. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 150 ብር በመከፈል ከአጣ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የካላንደር ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:30 ሰዓት ከአጣ ከ/አስ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
  9. ጨረታ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዚህ ዕለት ከሰዓት በኋላ 8፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
  10. ጨረታው በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ አይችሉም፡፡
  12. መ/ቤቱ ግዥውን በ20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
  13. በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ለጽ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል የመፈረም ግዴታ ያለበት መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- 

  • መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 033 661 0688 ወይም በፋክስ 0336610234 ላይ ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ::
  • ጨረታውን የምናወዳድረው በጥቅል ስለሆነ በዝርዝሩ ውስጥ ላሉ የማሽን ዓይነት በሙሉ ዋጋ መሞሳትና ማቅረብ መቻል አለበት፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን ያስጣዊ ከተማ አስተዳደር

ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

ኤክስካቫተር

Published on:Place of Bid Competitions:ሀዋሳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይ/ኢ/ል/ መምሪያ ጨረታ ቁጥር ኮ/001/13

የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2013 በጀት ዓመት በከተማው የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ለማሰራትና ሬዳሽ ለማምረት ሥራ ኤክስካቫተር ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡በዚህም መሠረት በጨረታው ስመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

  1.  ኤክስካቫተር ቼን ባኬት ከነ ጃከ ሐመር ከ180-350 የፈረስ ጉልበትና እ.ኤ.አ ከ2014 ወዲህ የተመረተ::
  2. በዘርፉ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለ2013 ዓ.ም ስለመታደሱ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በሀገር ውስጥ ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታዎችን የተወጡና በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን ማረጋገጫ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ አስተሻሸግ በተመለከተ የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ኦሪጅናልና ፋይናሻል ሁለት ኮፒ ለየብቻ በፖስታ ከታሸገ በኋላ እንደገና በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
  5. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ልማት መምሪያ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  6.  የጨረታው ሳጥን በ15ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነባልተገኙበት በፋ/ኢ/ልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 (ግዥ ክፍል )ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ሲፒኦ (CPO) እና ሰንድ የገዙብት ደረሰኝ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  8.  ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚገባችው ተጨማሪሰነዶች፡8.1 የኦፕሬተር ፕሮፋይል ፣ አምስት ዓመት እና ከዚያ በላይበተወዳደረው ማሽን የስራ ልምድ ያስውና የሥራ ግብርየተከፈስበት የሥራ ልምድ ማስረጃ : ከግብር ሰብሳቢመ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አስበት፡፡8.2 ያማሽን ኦፕሬተሩ ከተጫራች ድርጅት ጋር የተፈራረመበት የቅጥር ውል፡፡ 8.3. በሚወዳደረው ማሽነሪ ዓይነት የባስቤትነት ማረጋገጫደብተር /ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ስስበት::8.4. እስከ 2012 የማሽነሪና አድሳት ስስማድረጉ ፣ ቦሱአና የታደ ሙሉ ኢንሹራሽ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት::
  9. ከላይ በተ.ቁ 8 ላይ የተገስጹ ማስረጃዎችን አሟልቶ አያይዞየማያቀርብ ተጫራች በጨረታ ግምገማ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  10. አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  11. የጨረታ ዋጋ ስታስገቡ ድልዥ ስርዝ ወይም የማይነበብ ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  12. መምሪያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

 መረጃ ስልክ 046212 1334

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይ/ኢ/ል/መምሪያ

ዶዘር (Dozer)…

Published on:Reporter ( ኅዳር 6፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የማሽን ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ታይዎን ኮንስትራክሽን ለጅግጅጋ – ሀርሙካሌ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ለስራው አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሽኖች  አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ የነዳጅ እና የሎቤድ ወጪ ድርጅታችን የሚሸፍን ይሆናል፡፡

ተ.ቁየማሽን አይነትብዛትመለኪያማሽኑ የተሰራበት ዓ.ም.የኮንትራት ጊዜመግለጫ
1ዶዘር (Dozer)1በሰዓት2012 እ.ኤ.አ እና ከዚያ በላይለ 1 ዓመት 
2ግሬደር (Grader 140H 14OK)2,,,,  
3ኤክስካቫተር (Excavator)2,,,,  
4ሎደር (Loader)2,,,,,  
5ሩሎ (Roller 16Ton)2,,,,  
6ገልባጭ የጭነት መኪና (Sinotruck)8በወር,,  
7ወተር ትራክ (Water Truck)2,,,,  
8የነዳጅ ትራክ (Fuel Truck >= 10,000 L )1,,,,  
9ሎቤድ (Lowbed)5በኪ.ሜ,,ለ1 ጉዞከአ.አ-ጅግጅጋ

በመሆኑም ይህንን ማቅረብ የሚችሉ፡-

  1. አንድ ተጫራች ከላይ የተጠቀሱ የማሽን አይነቶች ላይ በከፊልም ሆነ በሙሉ መሳተፍ ይችላል፡፡
  2. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. ተጫራቾች ዋናውን እና ቅጂውን ቴክኒካልና (ሊብሬ) ፋይናንሻል ፕሮፖዛል  ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የራሳቸውን ዋጋ ማቅረቢያ ፎርም በመጠቀም ዋጋቸውን  ሞልተው ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘውትር በስራ ሰዓት  እስከ ህዳር 18 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ 10፡00 ሰዓት በማሽነሪ አስተዳደር ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በመቅረብ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  5. ለአሽናፊ ተጫራች የ 200 ስዓት ቅድመ ክፍያ (Advance Payment) እንፈጽማለን፡፡
  6. አሽናፊ ተጫራች የሚያቀርበው ማሽን ቴክኒካል አቅሙ በባለሙያ ተፈትሾ የሚወሰን ይሆናል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ፍሬሽ  ኮርነር የሚገኝበት ህንጻ ላይ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206::

ስልክ ቁጥር: 0973370070/0116479396/0910918106 ኢሜል፡ Hiwoncon@gmail.com.

ታይዎን ኮንስትራክሽን 

ትምህርት ቤት ግንባታ፣… የዶዘር ኪራይ ፣…

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 2፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የቡግና ወረዳ 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር የቡግና ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለቡ/ወ/ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ግንባታዎችንና የማሽን ኪራዮችን በግልጽ ጨረታ በሎቲንግ ሲስተም፤ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በአዲሱ የንግድ አዋጅ መሰረት በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የቲን/ተመዝጋቢ የሆነ።
  3. ግዢ ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  4. ከውሃ ምንጭ ግንባታ ዉጭ ላሉት ሌሎች የግንባታ ዘርፍ ደረጃ 9 እና በላይ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ::
  5. ተጫራቾች በጨረታለመሳተፍ ከላይ በተራቁጥር ከ1-4 የተጠቀሱትንና  የሚመለከታቸውን ፎቶ ኮፒ ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ /ማስገባት አለባቸው።
  6. የሚገዙ እቃዎች ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የተከፋፈለ ሲሆን
  • ሎት 1፡- የFTC ግንባታ ፣
  • ሎት 2፡- የእንስሳት ክሊኒክ ግንባታ
  • ሎት 3 ፦ ትምህርት ቤት ግንባታ፣
  • ሎት 4፡ የትምህርት ቤት አጥር ግንባታ፣
  • ሎት 5 : የሽድ ግንባታ፣
  • ሎት 6፡የመንገድ ፎርድ ግንባታ፣
  • ሎት 7 : የዶዘር ኪራይ ፣
  • ሎት8 የኤክስካቫተር ኪራይ
  • ሎት 9፣ የውሃ ምንጭ ግንባታ ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ድረስ ያሉትን ለእያንዳዳቸው 100 ብር /አንድ መቶ ብር/ በመከፈል እንዲሁም ሎት 9፡- 30 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥና ን/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር1 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን የግልፅ ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የኤክስካቫተር እና ዶዘር ኪራይን እስከ 15 ኛው ቀን ድረስ ግንባታን የግልፅ ጨረታው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ኛውቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡግና ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አ/ቡ/ቢሮ ቁጥር 14 የኤክስካቫተር እና ዶዘር ኪራይን ጨረታው የወጣበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በ16ኛው ቀን ግንባታዎችን የግልፅ ጨረታው እየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀም 22 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 ይከፈታል፡፡ የተጠቀሰው ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል።

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ሱ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በእካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0913143820 ወይም 0921264455 በመደወል ግኘት ይችላሉ፡፡

የቡ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ዓይና

ግሬደር፣ዶዘር፣ሎደር፣ሮሎ፣ሻወር ትራክ፣ኤክስካቫተር እና ገልባጭ መኪኖችን

Published on:Be’kur ( ጥቅምት 30፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአብክመ ገ.ኢ.ት ቢሮ በምዕ.ጎ.ዞን ገ.ኢ.ት.መምሪያ የወምበርማ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check It!

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ገ.ኢ.ት ቢሮ በምዕ.ጎ.ዞን ገ.ኢ.ት.መምሪያ የወምበርማ ወረዳ ገ.ኢ.ትብብር ፅ.ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ስራዎችን/እቃዎችን ማለትም

  • ሎት 1፡- ከኮኪ ጇምቢ የመንገድ ጥገና የማሽን ኪራይ ማለትም፡-ግሌደር፣ዶዘር፣ሎደር፣ሮሎ፣ሻወር ትራክ፣ኤክስካቫተር እና ገልባጭ መኪኖችን መከራየት እና ማስጠገን ፣
  • ሎት 2፡-የውሀ የግንባታ እቃዎች ማለትም አፍሪዲፕ ፓምፕ ፣ፌሮ ብረት እና እስታፋ ፣
  • ሎት 3 ፡-የህትመት ውጤቶች፣
  • ሎት 4፡-የፅዳት እቃዎችን ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
  1.  በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
  3. የግዥው የብር መጠኑ በየሎቱ 200 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀን እስከ 11፡30 ድረስ አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ተጫራች ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ በማያያዝ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 የማይመለስ ብር በሎት 50/ሃምሳ/ብር በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት እና መጫረት ይችላሉ
  6. ተጫራቾች የግዥውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1፡- ብር 15,000/አስራ አምስት ሺህ/ ፣ለሎት 2፡- ብር 4000/አራት ሺህ/፣ለሎት 3 ፡- ብር 500/አምስት መቶ/ ብር/፣ለሎት 4፡-ብር 500/አምስት መቶ/ ብር ለወም/ወ/ ገ/ኢ/ትብብር ፅ/ቤት በማለት ይህን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ኦሪጂናሉን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ መሙያውን በጥንቃቄ በመሙላት በሞሉት ዋጋ ላይ የድርጅታቸውን ስም፣ፊርማ እና ማህተም በማድረግ በአንድ ወይንም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በተለያዬ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦውን /ጥሬ ገንዘብ ገቢ የተደረገበትን ኮፒ በአንድ ፖስታ በማድረግ እነዚህን ሶስት ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በፖስታው ላይ የመስሪያቤቱን እና የአቅራቢውን ስም እና አድረሻ በመፃፍ የተጫራቹን ማህተም፣ፊርማ እና አድራሻ በመፃፍወም ወ.ገ.ኢ.ት.ጽ. ቤት ግዥ .ን.አስ.ቡድን ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ሎት 1 በ4፡30 ፣ ሎት 2 በ5፡00፣ ሎት3 በ5፡30 ፣ ሎት 4 በ6፡00 ሎት ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የማያግደን ከመሆኑም በተጨማሪ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡የጨረታው መክፈቻ ቀን የመንግስት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀ ከ5/አምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የሎት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10 በመቶ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ትዕዛዝ/በሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ በማሰራት ውል መያዝ አለበት፡፡
  11. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን የሎት እቃዎች በየመ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  12. . በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ወም/ወ/ገ/ኢ/ትብብር ፅ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳድር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0584490215 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዋጋ ሲሞሉ ግልፅ እና ተነባቢ መሆን አለበት፡፡
  14. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች/አገልግሎቶች/ ሙሉ በሙሉ በውሉ መሰረት ካላስረከበ የውል ማስከበሪያው ሙሉ በሙሉ ይወረሳል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የወምበርማ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት

ሮሎ ፣ ግሪደር እና ኤክስካቫተር ኪራይ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 1፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check It!

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 02/2013

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምሥ/ጎጃም ዞን የሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን በወረዳው ለሚገኙት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • ሎት1፡- የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
  • ሎት2፡-የስፖርት አልባሳት
  • ሎት3፡- የመኪና ጎማ
  • ሎት4፡- የማሽን ኪራይ ማለትም ሮሎ ፣ ግሪደር እና ኤክስካቫተር ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ለማስራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. የተሰጣቸው የንግድ ፈቃድ 1 ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፥ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው ፣ የቲን ነምበር /የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ተመዝጋቢ የሆነ የቫት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ሁሉም የእቃ አቅርቦት ተወዳዳሪዎች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን በመያዝ ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ማቅረብ የሚችሉ የእቃ አቅርቦት ስራውን ሙሉ በሙሉ በራሱ አቅርቦት መስራት/ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች በጥንቃቄ አሽገውና ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የሚፈለገው ፖስታ በሁለት ቅጅ ከሆነ በፖስታው ላይ ዋናውንና በጽሁፍ ዋናና ቅጅ በማለት ለይተው ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን በሚሞሉት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ፓራፍ ማድረግ አለባቸው፡፡
  5. እያንዳንዱ ተጫራች ሰነዱን የሚያሟሉት በነጻ ገበያ ዋጋ ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡ለሞሉትም ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ
    • ለሎት 1፡-20000.00/ሃያ ሺህ ብር/
    • ሎት 2፡- 2000.00/ሁለት ሺህ ብር/
    • ለሎት3፡6500.00/ስድስት ሺህ አምስት መቶ ብር/
    • ለሎት4፡-30000.00 / ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከማጠቃለያ ፖስታው ጋር ለብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቹ ከላይ በተጠቀሰው ስራ የፅሁፍ ማመልከቻ በማቅረብ ከሎት 1-4 150.00/አንድ መቶ ሃምሳ ብርየማይመለስ ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 06 የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ይህ ማስታወቂያ በውስን ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለእቃ አቅርቦት 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ 16ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን 400 ሠዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ዕለቱ የበዓል ቀን/ዝግ/ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ሳይገኙ ሲቀሩ የጨረታውን መከፈት የማያስቀር መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  8. አቅርቦቱን ለማቅረብ /ለመስራት/ ከተፈራረምንበት ቀን ጀምሮ በገቡት ውል መሰረት ማጠናቀቅ/አገልግሎት መስጠት ይኖርበታል።ሆኖም ከአሸነፉበት ዋጋ የዋጋ ልዩነት ሲኖር ምንም አይነት ጭማሪ የማናደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. ተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም አይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም::
  10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  11. የተጫራቾች የመጫረቻ ድጋፍ ስነዶቻቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማርኛ መሆን አለበት፡፡
  12. አሸናፊው አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ ለውል ማስከበሪያ የሚሆን 10% ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ እና ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  13. ማሳሰቢያ ለሁለም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ዋጋ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ለእቃ አቅርቦት /ለአገልግሎት 40/አርባ ቀናት/ መሆኑን መገንዘብ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-0582470509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ሸበል በረንታ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

የግዢ ቡድን የዕድ ውኃ

ዌል እስካቫተር ባለ ጎማ : ኮምፓክተር : ሎደር

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 1፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዳማ ከተማ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check It!

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዳማ ከተማ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በከተማው የተለያዩ ስራዎችን ለማሰራት የተለያዩ ማሽነሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ 

  1. ለተጠየቀው የማሽነሪ ኪራይ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Ta Payer registration No) ያላቸው 
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በጽ/ቤቱ ስም የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000000184369 ላይ ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጽ/ቤቱ የግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናተው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ሰነድ ላይ በተሰጠው ስፔሳ ራኪሽን መሰረት ብቻ ሳይጨምር ወይም ሳይቀንስ ዋጋውን መሙላት ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 6፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾቶ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  6. ማንኛውም ተወዳዳሪ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ካሸነፈ ማትረብ የሚጠበትበት
  • 1 ዌል እስካቫተር ባለ ጎማ (1)
  • 2. ኮምፓክተር -3
  • 3 ሎደር (1) ሲሆን

8. ማንኛውም ተጫራች ለሚያቀርባቸው ማሽነሪዎች ቦሎ ያስደረገበትን ማቅረብ አለበት፡፡

9 ማንኛውም ተጫራች የነዳጅ ዋጋ እና የተለያዩ ጥገናዎችን በራሱ ወጪ የሚሸፍን መሆን አለበት፡፡

10. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው ማሽነሪዎች አሮጌ ከሆኑ ተቀባይነት አይኖረውም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጪ ወይም የበዓላት ቀን ሆነ በሚከተለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡

12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

13. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር በአስተማማኝ ሁኔታ ስራውን ማከናወን ይኖርበታል፡፡

14 ማንኛውም ተጫራች ለውድድር የሚቀርበው ቫት ተጠቃሚ መሆን አለበት፡፡

15. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 022-211-14-42 ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአዳማ ከተማ መስተዳድር የአዳማ ከተማ

ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት

Excavator : Roller : Pick up


Published on:Reporter ( Nov 8, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Abeba 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check It!

INVITATION FOR BID

RE-BID NO. OBMCSC-01/2013

OBM Construction Share Company invites all interested and eligible bidders for the supply of different Construction Machinery and vehicles.

Lot No.DescriptionQuantity 
1Excavator2
2Roller2
3Pick up2

BIDDERS CAN BID FOR LOT/LOTS OF THEIR PREFERENCE:

  1. Interested bidders can obtain complete bid documents upon payment of non-refundable 200 (two hundred) birr before November 23, 2020, from the address mentioned below.
  2. Bidders shall deposit or pay a 2% bid bond of their offered total price in the form of a CPO or bank document.
  3. Bidders must submit their offers in authenticated sealed envelopes.
  4. All bidders requested to have a renewed business license for the current year, TIN registration certificate.
  5. The bid closing date shall be November 24, 2020, at 5:00 Am local time. The bid shall be opened in the same date at 5:30 AM local time in the presence of bidders or their legal representatives in our head office Meeting room.
  6. 6. OBM Construction Share Company reserves the right to reject any part or all bids.

OBM CONSTRUCTION SHARE COMPANY,

 Lideta Sub City, Biftu Building

5th Floor, In front of Addis Abeba Commercial School.

Tel. 0118362024, 0118362025, 0118362029

ግሬደር : ኤክስካቫተር ከነ ጃክሃመሩ (ቼይን) : ዶዘር : ሮለር


Published on:Reporter ( ጥቅምት 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check It!

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/mach/168/2020

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጣርማ በር መለያያ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማሽኖች ኢንተርፕራይዛችን ባስቀመጠው ቁጥር ዋጋ (Fixed price) ለመስራት ፍላጎት አቅራቢዎች በቅደም ተከተል መዝግቦ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል::

ስለሆነም፡

NoDescriptionየማሽኑ / የተሽከርካሪው አቅምብዛት ሞዴል/ስሪት ቁርጥ ዋጋ በሰዓት ከዛት በፊት ነዳጅ ሳያካትት
1ግሬደር140-200 HP ካት፣ ሳኒ፣ ቮልቮ ወይም ከነዚህ ጋር ተመጣጣኝ1,200.00 
2ኤክስካቫተር ከነ ጃክሃመሩ (ቼይን)150-250 HP4ካት፣ሳኒ፣ኮማትሉ ወይም ከነዚህ ጋር ተመጣጣኝ1,250.00
3ዶዘር 300-350 HP 04 ካት፣ሌበረር ወይም ከነዚህ ጋር ተመጣጣኝ1,600.00 
4ሮለር ከ16 ቶን በላይ 2ማንኛውም450.00 

1. ተጫራቾተ በመስኩ /ህጋዊ/ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

2. አከራይ ለሚያከራየው ማሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ማቅረብ አለበት::

3. ተጫራቾች እስከ ህዳር 16 ቀን 2013 .ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መ/ቤት የግኝዥ የሥራ ሂደት ቢሮ በመምጣት መመዝገብ ይችላሉ::

4. የማሽኖቹ የቴክኒክ ብቃት በባለሙያ ተፈትሾ ተቀባይነት ማግኘት ይኖርበታል::

5. ጐል የሚታሰረው የማሽኑ ቴክኒካል ብቃት በኢንተርፕራይዙ ሲረጋገጥ ብቻ ነው::

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

E-MAIL አድራሻ info@dce-et.com  የድህረ ገፅ አድራሻ WWW.dce-et.com

ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.0114-40-04-71/0114-42-07-46

ኤክስካቫተር፣ግሬደር፣ሮሎ፣የውሃ ቦ፣ቲሲኖ ትራክ እና ሎቤድ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አማራ ክልል
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check It!

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ በመራኛ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2013 በጀት አመት በከተማዋ ውስጥ ለሚሰራው የውስጥ ለውስጥ መሰረተ ልማት ስራዎች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን

  • 1ኛ ኤክስካቫተር፣
  • 2ኛ. ግሬደር፣
  • 3ኛ. ሮሎ፣
  • 4ኛ. የውሃ ቦቲ
  • 5ኛ. ሲኖ ትራክ እያንዳንዳቸው ከ2011 እ.ኤ.አ ወዲህ የገባ እና ሎቤድ   በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመከራየት ወይም ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1. በበጀት ዓመቱ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (ቲን) እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውያን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ  ዘወትር በስራ ሰዓት ለተከታታይ 15 ቀን እስከ 15/3/2013 ዓም ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመራኛ ከተማ መሪ ማዘ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ሰነዱን መግዛት ችላሉ።
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የገጠላና የጠቅላላ ዋጋ በዝርዝር ሞልተው ኮፒና እርጅናል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ባንኮ የሚሰጥ 1% ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የንግድ ስራ መሰጫ መደቦችና የተሰማሩት የንግድ ስራ ፍቃድ መስጫ ኮድ ቁጥር የንግድ ስራ ፈቃድ መስጫ መደብ እና የተሰማሩበት የስራ መስኮች በተገለፀው ትንታኔ ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የእቃውን ዋጋ በዝርዝርና በጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ስም ፊርማና ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከ26/2/2013 ዓ.ም ቀን እስከ 10/3/2013 ዓም 11፡30 ሰዓት ድረስ በመረጃ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው ተጫራቾች በአካልም ሆነ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም  ባልተገኙበት 11/3/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በመራኛ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  7. ሌሎች ለስራው የሚያስፈልጉ አጠቃላይ ማቴሪያሎችን ነዳጅ፣ ቅባትና ሰርቪስ ጨምሮ ራሱ መሸፈን ወይም መቻል አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች ለተቀመጠላቸው ከፍት ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በትክክል የነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ጨማሪ ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ስፔስፊኬሽን እና የማሽኑን አይነት የስራ ሰዓትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ለበለጠ  መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0111170081/894/0931 63 31 43/0980630520 ደውለው ይጠይቁ

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ

ወረዳ የመራኛ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

ዶዘር : ኤክስካቫተር : ግሬደር…

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 19፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአብክመ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን የመቅደስ ወረዳ
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን የመቅደላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለመቅደላ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በሚገኙ 07 ቀበሌ ምንጋሽ እና 026 ቀበሌ ደፈር ለሚያሰራው መንገድ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 የዶዘር ኪራይ በሰአት ሎቤድን ችሎ (የማድረሻ እና የመመለሻን )
  • ሎት 2 የኤክስካቫተር ኪራይ በሰአት ሎቤድን ችሎ (የማድረሻ እና የመመለሻን )
  • ለት 3 የግሬደር ኪራይ በሰአት ድን ችሎ (የማድረሻ እና የመመለሻን )
  • ሎት 4 ለመንገድ የሚሆን ጥራት ያለው ገረጋንቲ ማምረት እና ማጓጓዝ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶችማሟላት አለባቸው፡፡
  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. ዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ከለት1 -4 የተዘረዘሩትን ተጫራቶች ጨረታ ሰነዱንየማይመለስ ብር 150/ አንድ መቶ ሃምሳ ብር/በመክፈል የመቅደላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ጥሬ ገንዘብ ወይም የዕቃውን ጠቅላላዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በእንድ ወይም እንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅበማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመቅደላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግዥና ን/እስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከሎት 1-4 የተዘረዘሩትን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ እስከ 3:30 ሰዓት ድረስ በማስገባትይታሽጋል ፡፡ በዚሁ እለት ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅደም ተከተል በስራ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ን/አስ/ደ/ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀንካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  7. በጨረታው ለመጫረት የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ስፈለጉ ከጨረታ ሰነዱ ወይም 0334500222 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 334500273 በመላክ ማግኘት ይቻላል::
  8. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጎልም ፡፡
  9. አሸናፊው ድርጅትበለአትለማከራየትየሚያስገባቸውን ማሽነሪዎች ግዥ ፈጻሚ መስሪያቤትለስራከሚፈልግበትቀበሌ የማድረስ ግዴታ አለበት፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአብክመ በደቡብ ወሎ መስተዳድር ዞን የመቅደስ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዊል ሉደር (2008 ስሪት) እና ኤክስካቫተር ለመሽጥ ይፈልጋል::

Published on:Reporter ( ጥቅምት 18፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

የሐራጅ ማስታወቂያ

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሠረት ቀጥሱ ያቀረቡትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁየተበዳሪ ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪ ቅርንጫፍየመያዣ አይነትየሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥር/ሴሪያል ቁጥርየሞተር ቁጥርየጨረታ መነሻ ዋጋ በብርጨረታው የሚከናወንበት ቀንና ሰዓትጨረታው የወጣው
1በርሞግ ኮንስትራክሽን ኃ/የተግ/ማህበርተበዳሪኢምፔሪያል ዊል ሉደር (2008 ስሪት)ሥክ- L D-0845 N1A02463 C7C12932 900,000.00 ሕዳር 03 ቀን 2013 ከሰዓት በኋላ 8፡009፡00ለመጀመሪያ ጊዜ
2አቶ ቴዎድሮስ አበራ ኦዳተበዳሪገርጂ ኤክስካቫተርEX-0794 HHKHZ703JC000023726483560 4,300,000.00 ሕዳር 03 ቀን 2013ከጠዋቱ 4፡00 -5፡00ለመጀመሪያ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች፣

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ:: አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈሰትን ቀሪ ገንዘብ በአሥራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃልሉ መክፈል አለበት:: ካልከፈሉ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቅርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ:: ላላሽነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
  2. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው::
  3. ጨረታው የሚከናወነው በተራ ቁጥር 1 ላይ የተመለከተው በባ……… ሲሆን ፤ ተራ ቁጥር 2 ላይ የተመለከተው ደግሞ በትግራዊ ብሔራዊ ክልል፤ አክሱም ከተማ በሚገኘው በባንኩ አክሱም ቅርንጫፍ ነው::
  4. የተጫራቾች ምዝገባ ከአያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
  5. የስም ማዛወሪያ ክፍያ፤ ዓመታዊ የቦሎ ክፍያና እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል::
  6. ለጨረታ የቀረሱት ንብረቶች ቀረጥ ያልተከፈለባቸው ስለሆነ ገዢ ከቀረጥ ነፃ መብት ያለው መሆን ይኖርበታል፤ ካልሆነ ደግሞ ቀረጡን እና ተጨማሪ እሴት ታክስ መክፈል የሚጠበቅበት ይሆናል::
  7. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  8. ለሐራጅ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት በተራ ቁጥር 2 ላይ የተገለፀውን በተመለከተ አክሱም ቅርንጫፍ (0342757717) በመቅረብ ለመጎብኘት ይችላሉ::
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር በስልክ ቁጥር 011-1-58-08-63/0111-26-36-09 (ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት) ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ

Excavator, Wheel loader & Truck mount crane ለመግዛት ስለሚፈልግ…

Published on:
Reporter
 ( ጥቅምት 18፣ 2013 )
Place of Bid Competitions:መቐለ
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ኩባንያ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መኪና እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ብቃት ያላችሁ እ ከዚህ ከታች የተዘረዘሩ መስፈርት የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች ኩባንያችን ይጋብዛል፡፡

ዝርዝር የሚገዛ ንብረት

ተ.ቁየዕቃውን ዓይነትመለኪያብዛት ማብራሪያ
1Pickup double  cabin 4WD ABS /airbags power output 100ccበቁጥር06በስፔሲፊሽን መሰረት
2Hydraulic drive excavator Diesel engine T/charged  net power 200-232kwበቁጥር01በስፔሲፊሽን መሰረት
3Wheel loader Diesel Engine T/charged net power 146-160 kwበቁጥር01በስፔሲፊሽን መሰረት
4Truck mount crane max. lifting capacity 10-120 Tonበቁጥር01በስፔሲፊሽን መሰረት
5Telescopic Crane Max. Lifting capacity 10-12 Tonበቁጥር01በስፔሲፊሽን መሰረት
  1. ተጫራቾች የ2013 የታደሰ ንግድ ፈቃድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ  የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የታደሰ ንግድ ፈቃድና የታክስ ከፋይ ምዘዝገባ ምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታው ሰነድ 28/10/2020 እስከ 10/11/2020 እ.ኤ.አ ከ መቐለ ኮርፖሬት ሳፕላይ ቸይን ወይም አዲስ አበባ ላይዘን ቢሮ መውሰድ ይቻላል፡፡
  3. ጨረታው በ11/11/2020 እ.ኤ.አ ከሰአት በኋላ ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በ11/111/2020 እኤ.አ ከሰአት በኋላ ከቀኑ 8:30 አት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ መስፍን ዋና መ/ቤት በሚገኝ ኮርፖሬት ሳፕላይ ቼይን አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ተጫራቾች ባይገኙም የጨረታ ሰነዱ ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ዋናውና ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11/11/2020 እ.ኤ.አ ከሰኣት በኋላ ከቀኑ 8:00 መቐለ ዋና መሥሪያ ቤት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ ክፍያ ማዘጋዣ (CPO) ብር 200,000.00 (ብር ሁለት መቶ ሺ) በስም ታሸገ ፖስታ ከጨረታው ጋር ማስገባት አለባቸው:: በፖስታ ያልታሸገ ሲፒኦ እንዲሁም ሌላ አይነት የጨረታ ማስከበርያ ተቀባይነት የለውም::
  6. ተጫራቾች የሚያስገቡት የእቃው ዋጋ ታክስና ቫት ( VAT ) የትራንስፖርት ክፍያ ለየብቻው አስልቶ ማስገባት አለባቸው:: እንዲሁም ማስረከቢያው ቦታው መቐለ መስፍን ኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ ግቢ ውስጥ በመሆኑ በመጓጓዝ ሒደት የሚያጋጥም ብልሽትና ጉድለት15. ተጫራቾች ሙሉ ሃላፍነት ይኖርባቸዋል።
  7.  ጨረታው በ11/11/2020 እ.ኤ.አ ከሰአት በኋላ ከቀኑ 8:00 ተዘግቶ በ11/11/2020 አ.ኤ. ከሰአት በኋላ ከቀኑ 8:30 ሰኣት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት መቐለ መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ኃላ.የተ. የግል ኩባንያ ዋና መ/ቤት በሚገኝ ኮርፖሬት ሳፕላይ ቼይን አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን ሰነዳቸው የተሟላ ከሆነ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
  8.  የጨረታ አሸናፊ የሚሆኑ ተጨራቾች የጨረታ ዋስትና (Performance Guarantee) ቢያንስ ለ3 ወር የሚቆይ የኮንትራቱን ጠቅላላ ዋጋ 10% በCPO ወይም በቅድም ሁኔታ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና unconditional Bank Guarantee ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
  9. ተጨራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5(አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ (ቅዳሜ ጨምሮ) በሥራ ሰዓት የጨረታውን 10% የውል ማስከበሪያ ( Performance Guarantee) ወይም በሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ውል ማሰር ይጠበቅባቸዋል:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::
  10. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ተመስርተው ዋጋ ማስገባት አይፈቀድም፡፡
  11. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ካሸነፉ ለሌላ ሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት አይችሉም።
  12. ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉት ዕቃ ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ በ20 የሥራ ቀናት ውስጥ መቐለ ዋና መሥሪያ ቤት አጓጉዞ ማስረከብ አለባቸው:: ይህ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ብር ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ይወስዳል::
  13. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ

መቐለ                                            አዲስ አበባ

ስልከ +251-344402017                ስልክ +251-114709501

ፋክስ +251-344406225                ፋክስ +251-114709636

መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ኃላ.የተወ.የግል ኩባንያ

You cannot copy content of this page