The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ዶዘር D8R cater pilar :ግሬደር 180 HP CAT pillar :እስካቫተር Hitachi (Catter Pillar)

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 11፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የምሥራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለገጠር መንገድ ስራ የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሽነሪዎች እስከ ሥራ ቦታ ማለትም ከላላ ቱሉ ጫሊ ትምህርት ቤት ድረስ ማቅረብ የሚችል ህጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።

የማሽኑ ዓይነት፡-

  1. ዶዘር D8R cater pilar የተመረተበት ጊዜ እ.አ.አ.ከ 2014 ወደዚህ የተመረተና 300 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  2. ግሬደር 180 HP CAT pillar የተመረተበት ጊዜ እ.አ.አ 2014 ወደዚህ የተመረተና 180 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል :
  3. እስካቫተር Hitachi (Catter Pillar) HD 255 የተመረተበት ጊዜ እ.አ.አ.ከ 2014 ወደዚህ የተመረተና 255 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

የመወዳደሪያ መስፈር፡-

  1. የ2013 ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው።
  2. ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ፤ ቲን ነምበር ያላቸው ፣ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው ፤ እና የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት (supplier List) ያላቸው።
  3. ተጫራቾች የማሽኑን ዝርዝር የሚገልፅ ዶክሜንት (Specification of Machineries ) የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ከፍሎ የጨረታ ዶክሜንት ከ12/3/2013 እስከ 28/3/2013 ዓ.ም ከጉደያ ቢላ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ቅርንጫፍ ቀርበው በመውሰድ ዋና እና ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም የታሸገ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ለሁሉም ማሽኖች ከታወቀ በባንክ የተደገፈ CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ሥም ፣ አድራሻ፣ ማሕተም እና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራች ግብር መከፈሉን የሚገልፅ ከገቢዎች ባለስልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ::
  7. ጨረታው በ 28/3/2013 ዓም እስከ 3:30 ሰዓት ቆይቶ በዚያው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን ባለ ጉዳዩም ሆነ ህጋዊ ተወካይ ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግድም ።
  8. ማንኛውም ተጫራች ማሸነፉ ከተረጋገጠ በኋላ ለውል ማስከበሪያ ከታወቀ በባንክ 10% የማስያዝ ግዴታ አለበት::
  9. ጨረታውን ያሸነፈ የቅድመ ክፍያ (Advance Payment) ለመውሰድ ከታወቀ ባንክ (Unconditional bond) ማቅረብ አለበት።
  10. ማንኛውም ተጫራች የማሽኑን ሊብሬ ማቅረብ አለበት ወይም ህጋዊ ውከልና ያለው ስለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
  11. ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሠረት ማሽኖችን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  12. ጨረታውን ያሸነፈው አካል ቅድመ ክፍያ የሚከናወነው ማሽኑን ወረዳ እንደደረሰ ይሆናል።
  13. ማንኛውም ተጫራች ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል።
  14. ጨረታ ያሸነፈ with holding tax 2% መቁረጥ ግዴታ አለበት።
  15. ማንኛውም ተጫራች የማሽኑን መግለጫ (Spesfication) ማቅረብ አለበት
  16. ጨረታውን ያሸነፈ አካል እስከ 5 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  17. ለነዳጅና ሠራተኛ ማመላለሻ የሚሆን የግሉ (የራሱ) የሆነ ተሽከርካሪ እስከ ሥራ ቦታ ማለትም ከላላ ቱሉ ጫሊ ት/ቤት ድረስ ማመላለስ የሚችል፣ ለማሸኖች ሁሉ ነዳጅ የሚያቀርበው የጨረታ አሸናፊ ይሆናል።
  18.  መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
  • ስልክ ቁጥር፡- 0936008854 / 0913163779

የጉደያ ቢላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page