The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

GC-4

G+1 ህንጻ ግንባታ እድሳት ሥራ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ሆሳዕና
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በሀድያ ዞን የሆሳዕና ደም ባንክ ለሚያሰራው የG+1 ህንጻ ግንባታ እድሳት ሥራ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከደም ባንኩ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስከ 20ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም 60,000/ስልሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር ፓስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቶች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊከ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕርፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴከኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም የቴከኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል። የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል። ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ Bidder Certification of Compliance) ተፈርሞና ታሽጉ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  4. ጨረታው በ21ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት በደም ባንኩ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ደም ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ማሳሰቢያ፡- አዲሱ የተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል:: በዞኑ ውስጥ ሶስትና ከዚያ በላይ ስራ ያላቸው ተቋራጮች መሳተፍ አይችሉም::
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 046-555-46-18 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ደም ባንክ

ሆሳዕና

የመጸዳጃ ቤት ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ከአዲስ አበባ 130 ኪ.ሜ ርቀት ወደ ደብረብርሃን 80 ኪ.ሜ ርቀት
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/13

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሀ/ማ/ከ/ወ ገ/ኢ/ት/ ፅ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ለ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፤

  1. የጽህፈት መሳሪያዎች ለሁለተኛ ጊዜ
  2. ቋሚ አላቂ እቃ ለሁለተኛ ጊዜ
  3. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለሁለተኛ ጊዜ
  4. የተዘጋጁ ደንብ ልብስ ፣ብትን ጨርቅ፣ ጫማዎችና ልብስ ስፌት ለሁለተኛ ጊዜ
  5. ፈርኒቸር ለመጀመሪያ ጊዜ
  6. የእንስሳት መድሀኒት ለሁለተኛ ጊዜ
  7. የመጸዳጃ ቤት ግንባታ ለመጀመሪያ ጊዜ

ስለዚህ:

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የአቅራቢነት ማስረጃ ያላቸው
  3. የግዥው መጠን ብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክርነት ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
  5. የሚገዙ እቃዎችን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊክሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/ሀምሳ ብር/ብቻ በመክፈል ከግዥ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 ማግኘት ይችላሉ
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሀ/ማ/ከ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግዥ ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥ የን/ አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 8 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቹ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ ከሁለት ቀን በፊት ናሙና ማቅረብ መቻል አለበት፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን እንዳዋጭነቱ በተናጠል ወይም በጥቅል ሊሰጥ ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0116190146/148 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻ ፣ከአዲስ አበባ 130 ኪ.ሜ ርቀት ወደ ደብረብርሃን 80 ኪ.ሜ ርቀት በሚወስደው አስፋልት ከሸኖ ከተማ አለፍ ብሎ ወደ ምስራቅ 39 ኪ.ሜ ገባ ብሎ እንገኛለን፡

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የሀገረማርያም ከሰም ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

ሾላ -ገበያ

ቢሮ ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መንግስት በጉራጌ ዞን ሰገ/ጉ/ወ/ወረዳ 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር GGWW/004/2013

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መንግስት በጉራጌ ዞን ሰገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋኢል ጽ/ቤት በ2013 ዓም መደበኛ በጀት ለገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመጀመሪ ደረጃ ሆስፒታል የደንበኞች መቀበያ እና ለፍ/ቤት የተዘዋዋሪ ችሎት ቢሮ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ተጫራቾች

  1. የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC8 ደረጃ ስምንት እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች
  3. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ወከልና ይወ መምጣት አለባቸው
  4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋኤል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋኤልዕ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው፡፡
  6.  ተጫራቾች የጨረታውን ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዶከመንት ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለለፋይናንሻል ዶከመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከፋይናንሻል ኦርጅናል ዶከመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 8፡00 መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋኢል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታው ሰነድ በ15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. በአፈፃፀም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም ።
  2. ተጫራቾች ተጫርተው ካሸነፉ በኋላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜውን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን ::
  3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  4. ሁለት እና ከዛ በላይ የሆነ ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም፡፡
  • ለበለጠ መረጃ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋሲል ጽ/ቤት ቢር ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ

በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ

ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

የፓርቲሽን ሥራ፣ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች ሥራ እና የጥበቃ ቤት ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 05/2013

በኢፌዴሪ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡፡

  • ሎት1. የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና አገልግሎት ግዥ
  • ሎት2. የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት3. የጅምናዚየም ዕቃዎች ግዥ
  • ሎት4. የፓርቲሽን ሥራ፣ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶች ሥራ እና የጥበቃ ቤት ግንባታ የአገልግሎት ግዥ
  • ሎት5. የሊፍት አሳንሰር ግዥ
  • ሎት6. የአይቲ ቪዲዮ ኮንፍራንስ ክፍል ሙሉ ሥራ መገጣጠምና ማሰልጠንን ጨምሮ ግዥ
  • ሎት7. የመኪና ዕቃዎች (tools) ግዥ
  • ሎት8. የቀላል መኪና ጥገናና የመኪና ማጠቢያ ጋራዥ (የተሽከርካሪ አነስተኛ ጋራዥ) ግንባታ
  • ሎት9. የተሽከርካሪ ጥገና

በዚህ በጨረታው መወዳደር የምትችሉት:

  1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃዳቸውንና የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀውና አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፣ ግብር የመከፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ጨረታ ለመሳተፍ ሕጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለሚጫረቱበት የማይመለስ በብር 100 (መቶበመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15/ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት አዲስ አበባ እስታዲየም መንገድ ትራንስፖርት ያለበት ተመሳሳይ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ግዥና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 2ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ::
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ስም ለሚጫረቱበት ሲፒኦ 2,000 ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ፖስታቸውን በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
  5. ከአሸናፊው ተጫራች ጋር ውል ከመፈረሙ በፊት በጨረታ ሰነዱ ከተገለፀው አቅርቦት መጠን በላይ መጨመር ወይም መቀነስ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በአሸናፊው ተጫራች የቀረበው ውድድሩ የተገኘው ዋጋ ሳይቀየር እስከ 25% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚቻል፣
  6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት ጠዋት 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመፈቻ ቀኑ ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ከተጠቀሰው ቀን ዘይግቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ዋጋ አይኖረውም፣
  7. መስሪያ ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116146699 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

አድራሻችን፡- አዲስ አበባ እስታዲየም መንገድ ትራንስፖርት ያለበት ተመሳሳይ ሕንፃ ላይ

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት

የግድብ መሰረት ግራውንቲንግ (Dam Foundation Grouting) ስራን በንዑስ ተቋራጭ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ባህር ዳር 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

አገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር NCB AWWCE 04/2013 ዓ.ም

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባው ለአጅማ ጫጫ መስኖ ፕሮጀክት ግድብ አገልግሎት የሚውል የግድብ መሰረት ግራውንቲንግ (Dam Foundation Grouting) ስራን በንዑስ ተቋራጭ ለማሰራት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊው ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም አርፎበት በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀን እና ፀንቶ የሚቆይ 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር) በድርጅታችን ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡ አሸናፊ ከተለየ እና ከአሸናፊው ጋር ውል ከተያዘ በኋላ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቶች ስራውን ሰርተው የሚያጠናቅቁበት ጊዜ | Construction time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ስራውን ሰርቶ የሚያጠናቅቅበትን ጊዜ ገደብ በግልፅ በሰነዱ ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (ኢውስኮድ) ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ 21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ይከፈታል፡፡ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መከፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ባይገኙም ጨረታው በግዥ ኮሚቴ አማካኝነት ስለሚከፈት ተጫራቾች ከውድድሩ አይታገዱም፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ለሚወሰዱ ማንኛውም ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ ወይም የድርጅቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንከ ቢድ ጋራንቲ በማሰራት ማስያዝ እና በአካል ቀርቦ ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መያዝ አለበት፡፡ ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው:: የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮአችን 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻበመክፈል መግዛት ይችላሉ:: የሚሰሩ ዝርዝር የግድብ መሰረት ግራውንቲንግ (Dam Foundation Grouting) ስራን አይነት በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል፤ ለወደፊቱም ድርጅታችን በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  9. የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀናት በታች የሰጠ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  11. ተጫራቶች ተወዳድረው ያሸነፉበትን የስራ ዝርዝር ሰነድ አቅርበው እና በአማካሪው ተቀባይነት ሲያገኝ ወደ ስራው እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 058 222 14 79 መደወል ይችላሉ::

አድራሻ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት

አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን

ድርጅት (ኢው.ስ.ኮ.ድ.)

የዘመናዊ ቄራ ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር-003/2013

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለወልቂጤ ከተማ አገልግሎት የሚውል ማለትም፡- የዘመናዊ ቄራ ግንባታ ግዢ ለመፈጸም በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ  ባላቸው ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

 ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ  ተቋራጮች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

  • 1ኛ/ የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን  የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  • 2ኛ/ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችልና የዘመኑ የሥራ ግብር  የከፈሉ፣ ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማቅረብ የምትችሉ፡፡
  • 3ኛ/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ  21 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዛው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ዶክመንት ይከፈታል፡፡
  • 4ኛ/ ተወዳዳሪዎች የጨረታው ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር ብቻ/ አዲስ ክ/ከተማ ሚገኘው የገቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮ በመከፈልና ሪሲቱን በመያዝ ከወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰአት መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  • 5ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶከመንት ሲያቀርቡ ከስር በተገለጸው መሰረት ይሆናል

ሀ/ለቴከኒካል ዶከመንት ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ የ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር በማድረግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ቴከኒካል በሚል ስመለየት እና ፋይናንሽያል ዶክመንት ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ለየብቻቸው በማሸግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት በ22ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ወልቂጤ ከተማ ፋ/ኢ/ል /ፅ/ቤት-ግ/ን/አስ/ዋና/ስ/ሂደት ክፍል ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን የሚገባ ሲሆን የቴክኒካል ዶክመንት ጨረታው 4:30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6ኛ/ ከቴከኒካል ግምገማ ወደ ፋይናንሽያል ያለፉተወዳዳሪዎች ፋይናንሽያል  ዶክመንት የሚከፈትበት ቀነ ቀጠሮ በተቋሙ በማስታወቂያ ቦርድ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

7ኛ) በBC(ቢሲ) /GC(ጂሲ) ደረጃ 4 እና ከዚህ በላይ ፈቃድ ያላቸው ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑ፡፡

8ኛ/ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ህጋዊ ውክልና  ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

9ኛ/መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ  በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11/ ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • 1/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴ  ጨረታውን ሊከፍት ይችላል፡፡
  • 2/ በአፈጻጸም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም።
  • 3/ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  • 4/ በጨረታው ሂደት ውስጥ በየትኛውም ግምገማ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ ግዢ መመርያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

ለበለጠ  መረጃ አድራሻ፡- በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት ብሩክ ህንጻ ፊት ስፌት ቴሌ አጠገብ ከተሠራው አዲሱ የወልቂጤ  ከተማ አስተዳደር ህንጻ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወ/ከ/ፋ/ኢ/ ል/ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113658187  ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡

በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር

የፋ/ኢ/ል/ዋ/ጽ/ቤት

የጠጠር መንገድ ግንባታ : የእግረኛ መንገድ ግንባታና የከብት በረት አጥር ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአብክመ የደጀን ከተማ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

በደጀን ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በአለም ባንክ በክልሉና በከተማው በጀት ድጋፍ በከተማው ውስጥ

  • 1ኛ. የጠጠር መንገድ ግንባታ ከወንድሙ ምንውየ እስከ ሀይማኖት ካሳ መ/ቤት ፓኬጅ ቁጥር Dejen UllDP CW/04/20/21 LOT 2
  • 2ኛ. የእግረኛ መንገድ ግንባታ ከአህመድ ጀማል ሱቅ እስከ ኬላ በሁለቱም ሳይድ ፓኬጅ ቁጥር DEJEN ULlDP/CIP/CW/05/20/21  ሎት 1፡
  • 3ኛ የከብት በረት አጥር ግንባታ ፓኬጅ ቁጥር Dejen UIIDP/ CW/08/20/21 LOT3 ለመስራት ተጫራችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከተማ አስተዳደሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በመሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ  VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. GC/RC ደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ ለተቁ 1 GC ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ እንዲሁም RC ደረጃ 7 እና ከዚያ በላይ ለተቁ 2 እና GC/BC ደረጃ 9  እና ከዚያ በላይ ለተቁ 3
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ፡ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና  የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸ  ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የስራው ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  7. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከደጀን ተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 16 ይህ ጨረታ በአዲስ  ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ21 ቀናት ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ በእያንዳንዱ ሎት ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ለተራ ቁጥር 1 23000/ሀያ ሶስት ሺህ ብር/ለተራ ቁጥር 2.65460/ስልሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ብር ለተራ ቁጥር 3 20,000/ሀያ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በግዥ መመሪያው መሰረት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
  10. የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ የቴክኒካልና  ፋይናንሻል ዶክሜንት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደጀን ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፅ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 18  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በቢሮ  ቁጥር 18 በ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ  በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ  ቢሮ ቁጥር 18 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058-776-00-24 /058776 10 09 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በአብክመ የደጀን ከተማ

አስተዳደር ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

Construction works (Expression of interest (EOI)

Published on:Fortune ( Dec 6, 2020 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

Request for expression of interest (EOI)

Meta Abo Brewery S.C. Invites interested companies/consultants to express their interest on the following:

Summary of the proposal:

Meta Abo Brewery Share Company is interested to engage potential suppliers that can supply/provide the below service/goods respectively in Ethiopia. The EOI and accompanying documents must be sent by email: MetaAboBreweryprocurement@diageo.com  or received in a sealed envelope clearly labeled “Description of services, no later than 30/12/2021),

Interested entities shall express their intention of the following goods/services;

  • Construction Materials
  • Laboratory materials and consumables
  • Buta Gas
  • Electromechanical works
  • Borehole and water work
  • Construction works
  • Constructions Materials
  • Local spares MRO, RHS, SHS
  • Bearing and seal provider
  • Crane services,
  • Generator services and maintenance

Outputs:

By this invitation, it is the interest of the Meta Abo brewery to shortlist & consider financially capable and interested vendors for future possible business transaction.

Eligibility criteria

In order to be considered for further Appraisal

Vendors must:

  1. Have adequate financial resource to perform the proposed contract
  2. Comply with the required or proposed delivery or performance schedule;
  3. Have a satisfactory past and current performance record
  4. Have the necessary organization, experience, and accounting/operational controls and technical skills
  5. Have the necessary production, construction and technical equipment and facilities
  6. Qualify to receive an award under applicable Diageo regulations, code of business conduct (COBC) and other Diageo’s Polices.
  7. Be able to work as to Diageo Payment term policy (60 days)
  8. Have two client references available for contact during this process.
  9. Declare any form of conflict of interest at the time of document submission if any.

Only short-listed entity shall be considered for the bid solicitation.

Submission details

All interested firms shall provide the following documents

  1. Company profile not more than seven pages
  2. Legal documents
  • Valid Business license and Principal registration certificate that will allow them to work Sebeta and Addis Ababa
  • VAT registration certificate
  • TIN Certificate
  • Article & Memorandum of Association (for Registered Companies)

3. Any other documents that demonstrate entities are capable and motivated i.e., CV, Financial statement, Balance sheet and Income statement, Reference letter for successful performance, etc…)

– Expression of interest and statements of qualification must be delivered to the address below latest by 30/1/2021.

  1. By email: MetaAboBreweryprocurement@diageo.com
  2. Meta Abo Brewery on the road Salet Mihret Church to Jackross Compound, at the Reception office. Tel: 0116670160 or Sebeta procurement office, Samson Habte 251 935998628

Interested entities must provide information indicating that they are qualified to supply the services and/or goods and provide the required items (brochure, description of similar assignments, experience in similar conditions, availability of appropriate skills/expertise in manpower, volume capacity, etc…). Entity(s) will be selected in accordance with the procedures set out in the Diageo Polices.

Meta Abo Brewery S. C. is not bound to accept any quotation, nor award a contract and/or Purchase Order, nor be responsible for any costs associated with a Supplier’s preparation and submission of the Expression of interest (EOI), regardless of the  outcome or the manner of conducting the selection process.

Meta Abo Brewery reserves the right to accept or reject any or all EOI without incurring any obligation to inform involved applicant/s regarding the progress and/or the results.

This Expression of Interest shall not be considered or interpreted as a commitment of Meta to enter into a supply contract for goods and/or services with your company including anyone of your agents and/or subsidiaries. Such decision will be taken at the full discretion of Meta regardless of fulfilling the requirements herein.

ግንባታ

Published on:Be’kur ( ኅዳር 28፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ባህር ዳር
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የግንባታ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ የክልሉን ህዝብና የልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና የስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሃገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡

አማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ከግሊመር ጋር በመተባበር በሊቦ ከምከም ወረዳ 9 ቀበሌዎች ሦስተኛ ዓመት እቅድ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ኘሮጀክትን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ደረጃ 5 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ይህንን ስራ ለመስራት የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶችን አጫርቶ ውለታ ኮንትራት በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተቋራጮች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በማየት አንድ ብቻ መግዛትና መሳተፍ የሚችል ሲሆን የጨረታ መሳተፊያ የታደሰ ክሪላንስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡

ስለሆነም፡- ሎት አንድ አንጐት ቀበሌ፣ ሎት ሁለት ሽና ጽዩን እና ቡራ ቀበሌ፣ ሎት ሦስት ግናዛና ይፋግ /ከተማ/ ቀበሌ፣ ሎት አራት ጣራ ገዳም ቀበሌ፣ ሎት አምስት አገላ ቀበሌ፣ ሎት ስድስት ደሪጣ ቀበሌ ሲሆን

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
  2. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በዘርፉ በተመሳሳይ ሥራ ስራውን መስራታቸውን የሚገልጽ የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ባህር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከቢሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የስራውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ./ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
  7. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን ቴክኒካል ሰነድ ለብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ለብቻ በማዘጋጀት ያለምንም ስርዝ ድልዝ መረጃውን በትክክል በመሙላት ማለትም ሁለቱንም ሰነዶች እያንዳንዳቸው ለየብቻ በኢንቨሎኘ በማሸግ በግልጽ ጽሑፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመጻፍ ማስገባት አለባቸው፣
  8. ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ ሁሉንም የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነዶች ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎኘ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፅሁፍ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር /አልማ/ ዋናው መ/ቤት ባህር ዳር ቢሮ ቁጥር 100 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ15ኛው ቀን 8፡00 ላይ ይታሸጋል በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
  9. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
  10.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 410 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582266364 /0583207360 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር /አልማ/

…ባለ 1 ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ማስገንባት ይፈልጋል፡

Published on:Be’kur ( ኅዳር 28፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካይነት ከአልማ በተገኘ በጀት የምስ/ደ/ወ/ትምርህት ጽ/ቤት ባለ 1 ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ቆላድባ ከፍ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ እንዲገነባላቸው በቁጥር ትም- 4/1887/13/35 ዓ/ም በቀን 14/03/2013 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ስለተጠየቀ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. . የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  5. . የግንባታው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚቻል ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
  6. ተጫቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ሠነዱን መግዛት የሚፈልጉ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከ28/03/2013 ዓ/ም እስከ 18/04/2013 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 18/04/2013 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. . ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 19/04/2013 ዓ/ም 3፡30 ተዘግቶ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን በ4፡00 ይከፈታል
  11.  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟለት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
  12. . በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ ነው፡፡
  13. አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በባንክ ጋራቲ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. . ማንኛዉም ተጫራቾች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት የግንባታውን ቦታ ርክክብ በመፈፀም ግንባታውን መስራት ይኖርበታል፡፡
  16. በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918739006/0583350601 በመደወል ማግኘት ይችላሉ
  17. ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም

የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

Construction of Debele rural small scale Irrigation Project

Published on:Published on:
Addis Zemen ( Dec 6, 2020 )
Place of Bid Competitions:Dire Dawa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

INVITATION FOR BIDS

Dire Dawa Administration Water, Mine & Energy Office

The Employer, Dire Dawa Agriculture Water, Mines & Energy Office, has received a budget from Dire Dawa City Administration towards the cost of Rural water supply system Development and intends to apply part of the budge for payments of Construction of Debele rural small scale Irrigation Project located in Dire Dawa Rural kebele of asseliso Cluster

BID Ref. No.DDAWMED/Con/020/ 2013 Construction of:-civil work for Debele kebele small scale Irrigation Dire Dawa water, Mines & Energy Office now invites sealed bids from eligible bidders having Grade GC/ WWC-6 & above for construction of SSI as described below

  1. Bidding will be conducted through NCB procedures and is open to all eligible bidders
  2.  Interested eligible bidders may obtain further information from the address below and obtain the bidding documents during office hours 08:00 AM to 05:00 PM
  3. Bidders shall meet the following minimum qualifying criteria to qualify for the award of the contract.
  4. A complete set of bidding documents in English may purchase by interested eligible bidders upon payment of a non-refundable fee of ETB 300 (Three Hundred Birr) in cash.
  5. Bids must be delivered to the address below on or before 30th Dec 2020, 9:30 AM Electronic bidding will not be permitted and late bids will be rejected.
  6. Bids will be publicly opened at the address mentioned below on 30th Dec 2020, 9:30 AM
  7. All bids must be accompanied by a Bid Security of ETB 50,000.00 in the form of an unconditional Bank Guarantee or СРО.
  8. Bids shall be valid for a period of Ninety (90) days after the Bid opening date.

The address referred to above is:

Dire Dawa Administrative Agriculture, Water Mine & Energy

Bureau Procurement, finance and property administration directorate

1st floor, Room Number – 1

Telephone number:- +251251 113558

Dire Dawa Administration Water, Mine & Energy Office

Construction of Debele rural small scale Irrigation Project

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Dire Dawa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

INVITATION FOR BIDS

Dire Dawa Administration Water, Mine & Energy Office The Employer, Dire Dawa Agriculture Water, Mines & Energy Office, has received a budget from Dire Dawa City Administration towards the cost of Rural water supply system Development and intends to apply part of the budge for payments of Construction of Debele rural small scale Irrigation Project located in Dire Dawa Rural kebele of Jeldessa Cluster

BID Ref. No.DD4WMEO/Con/020/2013 Construction of:- civil work for Debele kebele small scale Irrigation

Dire Dawa Water, Mines & Energy Office now invites sealed bids from eligible bidders having Grade GC/WWC-6 & above for construction of SSI as described below,

  1. Bidding will be conducted through NCB procedures and is open to all eligible bidder
  2.  Interested eligible bidders may obtain further information from the address below and obtain the bidding documents during office hours 08:00 AM TO 05:00 PM.
  3. Bidders shall meet the following minimum qualifying criteria to qualify for award of the
  4. A complete set of bidding documents in English maybe purchased by interested eligible bidders upon payment of a non-refundable fee of ETB 300 (Three Hundred Birr) on cash
  5. Bids must be delivered to the address below on or before 30% Dec 2020, 9:30 AM Electronic bidding Het Le permitted and late bids will be rejected
  6. Bids will be publicly opened at the address mentioned below on 30 Dec 2020, 9:30 AM
  7. All bits must be accompanied by a Bid Security of ETB 50,000.00 in the form of unconditional Bank Guarantee, or CPO.
  8. Bids shall be valid for a period of Ninety (90) days after Bid opening date.

The address referred to above is

Dine Dawa Administration Agriculture, Water Mine & Energy Bureau Procurement, finance and property administration directorate 1st Floor, Room Number 1

Telephone Number: +251251113558

Dire Dawa Administration Water, Mine & Energy Office

ዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት (Construction)

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም ተጀምረው ሳይጠናቀቅ የተቋረጠውን የፍርድ ቤት ግንባታ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በተገለጸው መሰረት በ2013 የበጀት ዓመት ለማስገንባት ፦ በግንባታ መስክ የተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ የግዢ ዘዴ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁየግንባታው ዓይነትየግንባታው ቦታየተጫራች ደረጃየጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን በ CPO ብቻ
1ዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤትኦሞራቴጂሲ/ቢሲ ደረጃ ሰባትና ከዚያ በላይ10,000 / አስር ሺህ / ብር 

በዚህም መሠረት፡- 

  1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር፤ በክልሉ ወይም ስልጣን በተሰጠው አካል ተመዝግቦ ለ 2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከላይ በሠንጠረዥ በተጠቀሰው ደረጃ መሠረት የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ያለው፡፡
  2. በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው እና ለ 2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፤
  4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
  5. የግብር ግዴታን በመወጣት ስልጣን ካለው አካል ወይም ገቢዎች ባለስልጣን ለበጀት ዓመቱ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችለውን የታደሰ የታክስ ኪሊራንስ ሠርተፍኬት የያዘ Malid tax clearance certificate 
  6. በፌዴራል ወይም በክልሉ የግዢ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ስልጣን ከተሰጠው የሚመለከተው አካል በዘርፉ በአቅራቢነት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ / Registered in PPPA or PPA Suppliers List /
  7. ከዚህ ቀደም የወሰዳቸውን የግንባታ ሥራ ውሎች በጥራትና በወቅቱ ገንብቶ የሚያስረከብ ለመሆኑ፤ የግንባታ ጥራት ማጓደል ማዘግየት፣ ውል ማቋረጥ ወዘተ የውል አስተዳደርና አፈፃፀም ችግር የሌለበት ስለመሆኑ ስልጣን ከተሰጠው ከሚመለከተው የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ማንኛውም የመንግስት አካል ማስረጃ ያለው በመሆኑም ከዚህ ቀደም የግንባታ ፕሮጀክት ወስዶ በግንባታው ወይም በፕሮጀከቱ የውል ስፔስፍኬሽን እና ማጠናቀቂያ ቀናት በሚፈለገው ጥራትና የማጠናቀቂያ ቀናት በማጠናቀቅ ለአሰሪው ባለ በጀት መ/ቤት በወቅቱ ያላስረከበ ፤ ውል ያቋረጠ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡ ለዚህም ማስረጃ ከቀረበ ከጨረታው ውድድር በቀጥታ ውጭ ይደረጋል ወይም ይሰረዛል፡፡
  8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች ህጋዊ የፅሁፍ ማመልከቻ ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን ይህ ጨረታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 30 /ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት ግዢ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ከፍል የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን በመውሰድ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ከታወቀ ባንከ በሲፒኦ ብቻ በማዘጋጀት ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግ ከጨረታው ቴክኒካል ኦርጂናል ዶከመንት ጋር በማስገባት ማስያዝ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች የተገዛውን የጨረታ ሠነድ በመሙላት እና በማዘጋጀት አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን አቀራረቡም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ እና ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴከኒካሉ ላይ ቴክኒካል ኦርጂናል እና ቴክኒካል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ፋይናንሻሉ ላይ ፋይናንሻል ኦርጂናል እና ፋይናንሻል ኮፒ በማለት በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በሰላሳ አንደኛው /31ኛው ቀን (የሥራ ቀን) ከሆነ ብቻ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡25 ሰዓት ድረስ መግባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 6፡30 ሰዓት ታሽጎ ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በሰም አሽገው በሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ ካኪ ፖስታ ላይ በጥንቃቄ አስፈላጊውን መረጃ መግለፅ አለባቸው፡፡ የጨረታው አከፋፈት በሁለት መንገድ ሆኖ ቴክኒካሉ በመጀመሪያ ደረጃ ተከፍቶ ከተገመገመ በኋላ ፋይናንሽያል ዶከመንት ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ፤

  • መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0909198826 ወይም 0916779112 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ በደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር

የዳሰነች ወረዳ ፍርድ ቤት

ኦሞራ

አጥር ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ በ2013 ዓ.ም ለሚያሰራው የጥቁር አንበሳ ዋና መ/ቤት አጥር ግንባታ በዘርፋ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውን የሥራ ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ.አድራሻደረጃቸውየማጠናቀቂያ ጊዜ የመቁጠሪያ ቀናትቢድ ቦንድ በሲፒኦ ቼክ እና ካሽ
1አጥር ግንባታጂሲ/ቢሲ 7 እና ከዛ በላይ የሆኑለ 90 ቀናት 
  • ኤጀንሲያችን ይህን ግንባታ የሚፈፀመው በማስታቂውና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ከሚያሟሉት መሀከል የቴክኒክ መስፈርት ያሟላና ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች በመምረጥ ይሆናል፡፡
  • ተጫራቹ የሥራ ብቃታቸውንና ውጤታማነታቸውን ባለፋት 3 ዓመታት ያለምንም እንከን የተወጡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና ከአሰሪው መስሪያ ቤት እና ከሌሎች መንግስታዊ ቢሮዎች የሥራ ማስጠንቀቂያ ያልደረሳቸው መሆን ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቹ በውጭ ኦዲተር የተረጋገጠ የፋይናንስ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል/ ይኖርበታል።
  • ተጫራቾች ካለፉት 10 ዓመት ውስጥ የሥራ አፈፃፀም ማስረጃቸውን 2013 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ፈቃዳቸውን እንዲሁም ከገቢዎች ባለስልጣን መ/ቤት ጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ፣ ታክስ ክሊራንስ) ተ.እ.ታ የተመዘገበበት ሰርተፊኬት እና ከከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር የሚሰጠውን የምዝገባ የምስክት ወረቀት 2013 ዓ.ም የታደሰ ዋናውን በማቅረብ በግዥ ኤጀንሲ ዌብ ሳይት ላይ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ ከሚገኘው መ/ቤታችን ከግዥ ኬዝ ቲም ሰነዳቸውን ከተረጋገጠ በኋላ የማይመለስ ብር 200 ከፍሎ መውሰድ ይችላል።
  • አንድ ተጫራች ከአንደ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም::
  • አንድ ተቋራጭ ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ እንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
  • ተቋራጮች የዋጋ ማቅረቢያውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለጽ በጨረታው የስራ ዝርዝር ላይ በተገለጸው መሰረት ለሚያሠራቸው ስራዎች ፣ እቃ፣ ሠራተኛ መሣሪያ አጠናቆ ለመስራት የሚሰጡትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል መጻፍ አለባቸው:: በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ በግልጽ በሚነበብ መልክ መፃፍ አለበት፡፡
  • ተቋራጮች የጨረታ ሰነዶችን ሞልተው ቴክኒካልና ፋይናሽያል ኦሪጅናል እና ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ፎቶ ኮፒዎችን ሁሉንም ለየብቻ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስገባት ኤንቨሎፖች ላይ በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማረጋገጥ በተጨማሪ ሙሉ አድራሻቸውን በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አጠገብ በሚገኘው መ/ቤታችን ግዥ ከፍል እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
  • ጨረታው ታህሳስ 20 ቀን2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በመ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  • ማንኛውንም ተጫራች ከውድድር በፊት የስራ ሳይቱን አይቶ ማርጋገጥ አለበት::
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  • ማሳሰቢያ፡ በገዙት ኦርጅናል ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው ፈርመው ማህተም በማድርግ ሰነዱን ይመልሱ፡፡
  • ፖ.ሳ.ቁ. 1090 ስልክ ቁጥር 011 551 22 99 ወይም 011 558 63 13 አዲስ አበባ

ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ

የመናፈሻ ልማት ስራ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ጎንደር
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የግንባታ ስራዎች የጨረታ ማስታወቂያ

ንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2013 ዓ.ም UIIDP ማለትም በአለም ባንክ፣ በክልሉና በከተማው በጀት ድጋፍ

  1. ኮብል ስቴዲየም ጀርባ 0.5 ኪሎ ሜትር የውሃ ማፋሰሻ ቦይ ስራ የመኪና ማቋረጫ ጨምሮ በሎት 3 እስከ ደረጃ 8
  2. ፋሲል ከፍለ ከተማ 0.6 ኪሎ ሜትር የውሃ ማፋሰሻ ቦይ ስራ በሎት 5 እስከ ደረጃ 8
  3. አብየ እግዚ ቀበሌ አራጋው ቤት አካባቢ፤ ሞላ ቤት ኣካባቢ፣ ቁስቋም አካባቢ ዮሃንስ ቤት ጀርባ 0.2 ኪሎ ሜትር የሆነ የድጋፍ ግንብ ስራ እስከ ደረጃ 8
  4. ፒያሳ የወጣቶች ሴንተር ላይ የመናፈሻ ልማት ስራ በፌዝ 2 እስከ ደረጃ 7
  5. የአውቶብስ የማቆሚያ እና ለተጓገfች መቆያ የሚሆን የሸድ ግንባታ ስራ እስከ ደረጃ 7
  6. ማረሚያ ቤት መውረጃና ማራኪ ኳስ ሜዳ አካባቢ 0.5 ኪሎ ሜትር የሆነ የድጋፍ ግንብ ስራ በሎት እስከ ደረጃ 7
  7. ፈንጠር አካባቢ በቁጥር የአንድ) ድልድይ የግንባታ ስራ እስከ ደረጃ 7
  8. መናሃሪያ በለሳ መውጫ፣ ማዘጋጃ አቦ፣ ኮሌጅ ኮንዶሚነየም አካባቢ እና ከፒያሳ እስከ ቅዳሜ ገበያ አካባቢ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብራት መልሶ የመገንባት ስራ (Street light rehabilitation)
  9. ሎዛ ጤና ጣቢያ እና ከማህበራት እስከ ቆላድባ አስፓልት ድረስ እና እየር ጤና ቤተከርስቲን መግቢያ እካባቢ 7 ኪሎ ሜትር ደረጃ የጠበቀ የጠጠር መንገድ እስከ ደረጃ 5
  10. መካከለኛ ድልድዮችን የሚያገናኝ 7 ኪሎ ሜትር ደረጃ የጠበቀ የጠጠር መንገድ ስራ እስከ ደረጃ 5 ከላይ የተዘረዘሩትን የግንባታ ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከተማ አስተዳደሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
  • 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  • 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
  • 3 የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
  • 4 ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • 5 የሚሰሩ ሥራዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል ፣
  • 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስ/ድጋፍ የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ከ27/03/2013 ዓ.ም እስከ 19/04/2013 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል 
  • 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ከላይ ለተዘረዘሩት ስራዎች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 8 ላሉት ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት 80,000 /ሰማኒያ ሺህ ብር/ማስያዝ ሲኖርባቸው በተራ ቁጥር 9 እና 10 ላሉት ደግሞ በእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  • 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኣንድ ኦርጅናልና ኣንድ ፎቶ ኮፒ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክሜንት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽንመምሪያ የግዥ ፋይናንስና ንብረት እስ/ድጋፍ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 10 /አዳራሹ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 20/04/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • 9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከመምሪያ አዳራሽ በ20/04/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ20/04/20፡3 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምክንያት ባይገኝ በሚወሰነው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል
  • 10, መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • 11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው: ገዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 111 06 24 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 64 60/111 41 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር

ድልድይ ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት 2013 በጀት አመት ለአገታ ኤጀሬ ድልድይ ግንባታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።

ስለሆነም ደረጃ-9 ማህበራት ማሰራት ይፈልጋል።

  • የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ
  • የንግድ ፍቃድ እና የስራ ፍቃድ የ2013 በጀት አመት የታደሰ ማቅረብ የሚችል
  •  የጨረታ ዋስትና 5000 (አምስት ሺ ብር) በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ

ከላይ የተገለፁትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ማንኛውም ማህበር ሰነዱን ከአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ 150 ብር /አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈልና በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን ፋይናሻል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናልና ሁለት ኮፒ፤ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ጨረታው የሚከፈተው 21ኛው ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 630 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባልተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡

  • ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ካቀረቡት ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
  • የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጠውም።
  • ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡0913345126 ወይም 0910036412/0916690356

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በስልጤ ዞን

የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት

የውሃ ምንጭ ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ/ በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ብ/ብ/ህ/ከ/መ/ በካፋ ዞን ጌሻ ወረዳ በውሃ ሀብት ጽ/ቤት በ2013 ዓ. ም በጀት በተለያዩ ቀበሌዎች የውሃ ግንባታ በመደበኛ እና በRLLP በጀት በቡድን በመከፋፈል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ 2013 ዓ.ም የሚገነቡ፡- ምንጭ ግንባታና እጅ ፓምፕ ቡድን አከፋፈል

ተ.ቁቀበሌጎጥየግንባታ አይነትየበጀት ምንጭቡድንምርመራ 
1ወዲቲያጋየእጅ ፓምፕRLLP 1
2ከጮወረባምንጭ ጥገናመደበኛ
3መሻሚጭብያምንጭ ግንባታRLLP
1አንድራቻኢታ መታያምንጭ ግንባታRLLP2 
2ደኒቲዉሺምንጭ ጥገናመደበኛ
3ጋዌቻጨለ ጎቺምንጭ ጥገናመደበኛ
1አንድራቻእታ ብድራምንጭ ግንባታRLLP3 
2ተችቲሾቦእጅ ፓምፕRLLP
3ይድፋኡጋናምንጭ ጥገናመደበኛ
1የርከጭቲዓመቶምንጭ ጥገናመደበኛ4 
2መሻሚሹንጋምንጭ ግንባታRLLP
3ድርበዶአከራምንጭ ጥገናRLLP
1ጋዌቲመጫምንጭ ግንባታRLLP5 
2አበታባያኒእጅ ፓምፕRLLP
3ነችቲያለፋምንጭ ግንባታRLLP
1ጋዌቲመልጋዊእጅ ፓምፕRLLP6 
2እመሮ አጣጋሄ ቅቲምንጭ ግንባታመደበኛ
3የሺቶ የሪዋንድራእጅ ፓምፕRLLP
1ተችቲሾቦምንጭ ግንባታRLLP7 
2ተችቲገሪምንጭ ግንባታRLLP

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

  • ደረጃ ዘጠኝና( 9 ) ከዚያ በላይ የሆነ / WC ወይም GC/ ህጋዊ የግንባታ ፍቃድ ያለው፡፡
  • የዘመኑን ግብር የከፈለና በወቅቱ የንግድ ፍቃድ ያሳደስ ፣
  • የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
  • ቫት ተመዝጋቢ የሆነ ለመንግስት 2 በመቶ ታክስ ከሚያገኘው ገቢ ለመከፈል ፍቃደኛ የሆነ፣

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ ሀያ /20/ ቀናት ውስጥ ጌሻ ወረዳ ገቢዎች ቅ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 34 ክፍል ተጫራቾች ለአንድ ቡድን የማይመለስ 50 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ በመግዛት የቡድኑን ቁጥር ሰነድ ላይ በመፃፍ አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል መረጃ ከነሲፒኦ ለብቻ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል ለየብቻ የግንባታውን ቦታና ቡድን በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ስም፣ ማህተምና ስልክ ቁጥር በመጻፍ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛ ተከታታይ ቀናት እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ በጌሻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ስራ ሂደት የቢሮ ቁጥር 03 በመቅረብ ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ ፣

  • ተጫራቹ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ሲገቡ የውል ማስከበሪያ 10% ለማስያዝ ፈቃደኛ የሆነ
  • አንድ ተጫራች ከላይ በቡድን ከተከፋፈሉት የውሃ ግንባታ ስራዎች መካከል መወዳደር የሚችለው በአንድ ቡድን ውስጥ የሚገኙትን የውሃ ግንባታ ስራዎች ብቻ እንጂ ከአንድ ቡድን ውጭ መወዳደር አይችሉም።
  • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናንስ አስ/ር ስራ ሂደት ቢሮ በ21ኛው ቀን 3፡05 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን አያስተጓጉልም ::
  • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በሰንበት ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ተላልፎ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ግንባታ ብር ጠቅላላ ዋጋ 2000 በካሽ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ስልክ 047-774-0329/047-774-0201

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/በካፋ ዞን የጌሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

በጎደሬ ወረዳ ገለሻ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት በጾታ የተለዩ የወንዶችና ሴቶች የመጻዳጃ ቤትና የሴቶች የወር አበባ መፀዳጃ ክፍል…

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ጋምቤላ 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጋምቤሳ ሕ/ብ/ክ/መ/ትም/ ቢሮ

በዋን ዋሽ ብሔራዊ ፕሮግራም በተገኘ በጀት ድጋፍ

  1. በጎደሬ ወረዳ ገለሻ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት በጾታ የተለዩ የወንዶችና ሴቶች የመጻዳጃ ቤትና የሴቶች የወር አበባ መፀዳጃ ክፍል
  2. ጋምቤላ ወረዳ ጎራ ኝካዎ 1ኛ ደረጃ ትም/ቤት የወንዶችና የሴቶች የመጻዳጃ ቤትእና የወር አበባ መፀዳጃ ክፍል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡

  1. የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
  2. የምዝገባ ሰሪትፊኬት ማቅረብ የሚችል
  3. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  4. ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝገቢ የሆነ
  5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 ሦስት መቶ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21/ ሃያ አንድ ተከታታይ የሥራ ቀናት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ትም/ቢሮ ቢሮ ቁጥር 19 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
  6. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው የሥራ ቀን ሲሆን ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 3፡30 ሰዓት ላይ ያስገባሉ፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0475510136/ 0475511236

የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ

ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

ቀሪ ስራዎችና የግቢ ማስዋብ ሥራ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 )Place of Bid Competitions:በሀድያ ዞን ሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

 የጨረታ ማስታወቂያ

በሀድያ ዞን የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዲሞኔስስትሬሽን ክፍል ቀሪ ስራዎችና የግቢ ማስዋብ ሥራ ለማሰራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letterከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው
  3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በስም አሽጐና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ  ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝናበፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ተሞልቶ ተፈርሞና ታሽጐ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  4. ጨረታ በ21ኛው በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡- አዲሱ የተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል ።

በዞኑ ውስጥ ሶስትና ከዚያ በላይ ስራ ያላቸው ተቋራጮች መሳተፍ አይችሉም ::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-555-3988 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

በሀድያ ዞን ሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ

ሆሣዕናCompany Info

Construction of fence, guardhouse, dry latrine & Shelter

Published on:Addis Zemen ( Dec 6, 2020 )Place of Bid Competitions:Bahir Dar
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

Invitation to National Competitive Bid for the procurement of fence, guardhouse, dry latrine,

  • Shelter to bid Tender No. (RFQ No. 4041071) at different sites of NWR
  • Floating Date: December 9, 2020, at 08:30 AM
  • Ethio Telecom North West Region (NWR) invites interested and eligible local bidders in this bid for the procurement of fence, guardhouse, dry latrine, Shelter to bid Tender No. (RFQ No. 4046838, 4046819, 4046831, 4046832, 4046830, 4046827, 4046823, 4046824, 4046817, 4046793, 4046774, 4046786, 4046796, 4046818, 4046820, 4046821, 4046822, 4046825, 4046826, 4046828, 4046829) at different sites of NWRFloating Date: December 9, 2020, at 08:30 AM
  • Closing Date: December 23, 2020, at 05:00 PM
  • Opening Date: December 24, 2020, at 10:00 AM

Bid documents can be obtained from ethio telecom’s NWR (Bahir Dar), 1st-floor room No. 108 during office hours (Monday to Friday) upon payment of a non-refundable fee of Birr 100.00 (Birr one hundred only).

  1.  All Bids must be accompanied by bid security as specified in the bid document.

1.1. The bid bond shall be furnished in the format specified in the bid document. Ethie Telecom North West Region Sourcing and Supply Section 1st floor, Room No. 108 In front of Tana Haik School Tel: +251582200049 P. O. Box 01, Bahir Dar, Ethiopia.

2. Bidders are seriously advised to read and comply with the instructions provided in the bidding document.

3.Ethio telecom reserves the right to reject all or parts of this bid.

4. No one is allowed to duplicate or transfer the bidding document that she/he acquired to participate under this invitation. Legally authorized agents shall collect the bidding documents for each principal they are representing.

Ethio telecom

You cannot copy content of this page