| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ጎንደር |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግንባታ ስራዎች የጨረታ ማስታወቂያ
በጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በ2013 ዓ.ም UIIDP ማለትም በአለም ባንክ፣ በክልሉና በከተማው በጀት ድጋፍ
- ኮብል ስቴዲየም ጀርባ 0.5 ኪሎ ሜትር የውሃ ማፋሰሻ ቦይ ስራ የመኪና ማቋረጫ ጨምሮ በሎት 3 እስከ ደረጃ 8
- ፋሲል ከፍለ ከተማ 0.6 ኪሎ ሜትር የውሃ ማፋሰሻ ቦይ ስራ በሎት 5 እስከ ደረጃ 8
- አብየ እግዚ ቀበሌ አራጋው ቤት አካባቢ፤ ሞላ ቤት ኣካባቢ፣ ቁስቋም አካባቢ ዮሃንስ ቤት ጀርባ 0.2 ኪሎ ሜትር የሆነ የድጋፍ ግንብ ስራ እስከ ደረጃ 8
- ፒያሳ የወጣቶች ሴንተር ላይ የመናፈሻ ልማት ስራ በፌዝ 2 እስከ ደረጃ 7
- የአውቶብስ የማቆሚያ እና ለተጓገfች መቆያ የሚሆን የሸድ ግንባታ ስራ እስከ ደረጃ 7
- ማረሚያ ቤት መውረጃና ማራኪ ኳስ ሜዳ አካባቢ 0.5 ኪሎ ሜትር የሆነ የድጋፍ ግንብ ስራ በሎት እስከ ደረጃ 7
- ፈንጠር አካባቢ በቁጥር የአንድ) ድልድይ የግንባታ ስራ እስከ ደረጃ 7
- መናሃሪያ በለሳ መውጫ፣ ማዘጋጃ አቦ፣ ኮሌጅ ኮንዶሚነየም አካባቢ እና ከፒያሳ እስከ ቅዳሜ ገበያ አካባቢ 5 ኪሎ ሜትር የመንገድ መብራት መልሶ የመገንባት ስራ (Street light rehabilitation)
- ሎዛ ጤና ጣቢያ እና ከማህበራት እስከ ቆላድባ አስፓልት ድረስ እና እየር ጤና ቤተከርስቲን መግቢያ እካባቢ 7 ኪሎ ሜትር ደረጃ የጠበቀ የጠጠር መንገድ እስከ ደረጃ 5
- መካከለኛ ድልድዮችን የሚያገናኝ 7 ኪሎ ሜትር ደረጃ የጠበቀ የጠጠር መንገድ ስራ እስከ ደረጃ 5 ከላይ የተዘረዘሩትን የግንባታ ስራዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከተማ አስተዳደሩ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶች በሙሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- 1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው፣
- 3 የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፣
- 4 ተጫራቶች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- 5 የሚሰሩ ሥራዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል ፣
- 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስ/ድጋፍ የስራ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ከ27/03/2013 ዓ.ም እስከ 19/04/2013 ዓ.ም ማግኘት ይቻላል
- 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ከላይ ለተዘረዘሩት ስራዎች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 8 ላሉት ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት 80,000 /ሰማኒያ ሺህ ብር/ማስያዝ ሲኖርባቸው በተራ ቁጥር 9 እና 10 ላሉት ደግሞ በእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት 300,000 /ሶስት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኣንድ ኦርጅናልና ኣንድ ፎቶ ኮፒ የቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክሜንት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽንመምሪያ የግዥ ፋይናንስና ንብረት እስ/ድጋፍ የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 10 /አዳራሹ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 20/04/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከመምሪያ አዳራሽ በ20/04/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ20/04/20፡3 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምክንያት ባይገኝ በሚወሰነው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል
- 10, መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- 11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው: ገዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 111 06 24 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 111 64 60/111 41 71 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር