| Published on:Be’kur ( ኅዳር 28፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አማካይነት ከአልማ በተገኘ በጀት የምስ/ደ/ወ/ትምርህት ጽ/ቤት ባለ 1 ብሎክ ባለ 4 መማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ቆላድባ ከፍ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ እንዲገነባላቸው በቁጥር ትም- 4/1887/13/35 ዓ/ም በቀን 14/03/2013 ዓ/ም በተፃፈ ደብዳቤ ስለተጠየቀ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- . የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- . የግንባታው አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት የሚቻል ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ይሆናል፡፡
- ተጫቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ሠነዱን መግዛት የሚፈልጉ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከ28/03/2013 ዓ/ም እስከ 18/04/2013 ዓ/ም ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 18/04/2013 ዓ/ም 11፡30 ድረስ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- . ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት 19/04/2013 ዓ/ም 3፡30 ተዘግቶ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በዚህ ቀን በ4፡00 ይከፈታል
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟለት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ የጨረታዉን ፖስታ የመክፍት ስልጣን አለዉ፡፡
- . በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የውል ማስከበሪያ በባንክ ጋራቲ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- . ማንኛዉም ተጫራቾች /ተወዳዳሪ/ አሸናፊነቱ ተገልጾለት ዉል ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ በውሉ መሠረት የግንባታውን ቦታ ርክክብ በመፈፀም ግንባታውን መስራት ይኖርበታል፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918739006/0583350601 በመደወል ማግኘት ይችላሉ
- ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለከትም
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት