| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 27፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በሀድያ ዞን ሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
በሀድያ ዞን የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዲሞኔስስትሬሽን ክፍል ቀሪ ስራዎችና የግቢ ማስዋብ ሥራ ለማሰራት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- ደረጃቸው BC/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letterከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በስም አሽጐና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝናበፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጂናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ተሞልቶ ተፈርሞና ታሽጐ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- ጨረታው በ21ኛው በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 21ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- አዲሱ የተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት የግዥ መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል ።
በዞኑ ውስጥ ሶስትና ከዚያ በላይ ስራ ያላቸው ተቋራጮች መሳተፍ አይችሉም ::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046-555-3988 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በሀድያ ዞን ሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ሆሣዕናCompany Info