The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

Ethiopia

ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ የውሃ ቦቴ፣ ዋገን ድሪል፣ ሎቤድ እና ሰርቪስ መኪና በጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 12፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ባህር ዳር
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የማሽነሪ ኪራይ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ

የኣማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ገልባጭ መኪና በሜ.ኩብ፣ ገልባጭ መኪና በሰዓት፣ የውሃ ቦቴ፣ ዋገን ድሪል፣ ሎቤድ እና ሰርቪስ መኪና በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች የሚያገለግሉ  የተለያዩ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን በጨረታ አወዳድሮ መከራየት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መመሪያዎች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የጸና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) እና በላይ የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤(ሰርቪስ መኪና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ያልሆኑ መወዳደር ይችላሉ።)
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ::
  5. የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች በሙሉ የፈረስ ጉልበታቸው፣ የስሪት ዘመናቸውና ሌሎች ከጨረታ ሰነዱ የተገለፁት መስፈርቶች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው፡፡
  6. የኪሎ ሜትር እና የነዳጅ ቆጣሪው በትክክል የሚሰራ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% ለማሽነሪ ሆኖ ለውሃ ቦቴ፣ ለሎቬድ፣ ለገልባጭ መኪና በሰዓት፣ ለገልባጭ መኪና ሜ.ኩብ እና ለሰርቪስ መኪና ለአንድ ተሽከርካሪ የሚያስይዙት ብር 10,000.00 (አስር ሽህ) በባንክ በተረጋገጠ ፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም ጨረታ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60(ስልሳ ቀናት የሚቆይ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብሄራዊ ባንክ እወቅና ከሰጣቸው ባንኮች ብቻ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከገንዘብ ዥ ቢሮ ቁጥር 02 ይህ ማስታወቂያ ኣየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ12/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/02/2013 ዓ.ም መግዛት ይችላሉ፡፡
  9.  ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን ፋይናንሻልንና ቴክኒካሉን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ ከግዥ አፉሰሮች ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 27/02/2013 ዓ.ም 8.00 ስዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንስትራከሽን ኤጄንሲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ27/02/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  12. የጨረታ ሰነዱን ለኤጀንሲው ድረ-ገጽ WWWarrca.gov.et በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፡፡
  13. በጨረታው ለመሳተፍ ያሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ

ከፈለጉ በፋክስ ቁጥር 058-222-1100

በስልክ ቁጥር 058-220-51-55 ወይም 058-222-11-07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::

የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ

ባህር ዳር

ሮሎ፣ ግሬደር፣ዶዘር፣ ሎደር፣ሻውል ትራክ እና ገልባጭ መኪና

Published on:Place of Bid Competitions:በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር 
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለመሰረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ

  • ሮሎ፣ ግሬደር፣
  • ዶዘር፣ ሎደር፣
  • ሻውል ትራክ እና ገልባጭ መኪና የማሽን ኪራይ ግዥ ለመንገድ ጥገና በጥቅል ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
  1. በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው
  4. የግዥ መጠኑ ከ200000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
  7. የሚገዙ የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ የማይመለስ 100 ብር ብቻ በመክፈል አ/ዘመን/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ዘርፍ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 17000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቀን 9/2/2013 እስከ 29/2/2013 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም ጨረታው ከቀን 30/2/2013 ዓ.ም ድረስ እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ፖስታ /የጨረታ ሰነዱን/ ማስገባ የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 30/2/2013 ዓ.ም 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙበት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ሙሉ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058444 03 43/985 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
  12. ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ የስራ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡30 አሸናፊው ውል በፍትህ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጥል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡
  14. የማሽን ነዳጅ፣ ዘይት እና የሎቪድ መጫኛ እንዲሁም ልዮ ልዮ ወጭዎችን በተጫራቹ /በባለሀብቱ/ የሚሸፈን ይሆናል/ተቋሙ የማይሸፈን/መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  15. የሚጫረቱበትን የማሽን ሊብሬና ቦሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  • ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ 20 በመቶ ከፍ 20 በመቶ ዝቅ አድርጎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አሸናፊው ያሸነፋቸውን ማሽኖች በራሱ /በተጫራቹ/ ትራንስፖርት ወጭ እስከሚፈለገው ቦታ ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡

የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት

ሞተር ግሬደር : ዶዘር :ሮለር : ሎደር : ቼን ኤክስካቫተር : የውሃ ቦቴ : ገልባጭ

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 10፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ጋምቤላ 
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)

ለመንገድ ግንባታ የሚውሉ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2013

የጋምቤላ ክልል ገጠር መንገዶች ባለስልጣን የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች፣ ገልባጭ መኪናዎችና ቀላል ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁየተሽከርካሪው /የማሽነሪው አይነትብዛት
1ሞተር ግሬደር 180 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ጉልበት ያለው3
2ዶዘር 300 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ ጉልበት ያለው2
3ሮለር 14 ቶን ክብደት እና ከዚያ በላይ ክብደት ያለው3
4ሎደር 3 ሜትር ኪዩብ የሚጭን እና ከዚያ በላይ የሚጭን2
5ቼን ኤክስካቫተር 200 የፈረስ ጉልበት እና ከዚያ በላይ1
6የውሃ ቦቴ 13,000 ሊትር እና ከዚያ በላይ መጫን የሚችል3
7ገልባጭ መኪና 14 ሜትር ኪዩብ የሚጭን እና ከዚያ በላይ የሚጭን15
8ሰርቪስ መኪና ሎንግ ቤዝ ሾፌሩን ጨምሮ 10 ሰው መጫን የሚችል4
9ሰርቪስ መኪና ፒክ አፕ ደብል ገቢና ሾፌሩን ጨምሮ 5 ሰው መጫን የሚችል2
10ሰርቪስ መኪና ሲንግል ካፕ ገቢና ሾፌሩን ጨምሮ 2 ሰው መጫን የሚችል3

በዝርዝር ከላይ የተመለከቱትን ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ሙሉ በሙሉ ለማከራየት የምትፈልጉ ተጫራቾች በጋምቤላ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብርብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ዘውትር በስራ ሰዓት በመግዛት ረቡዕ 2/3/2013 ዓ.ም ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በዚሁ ቀንም ጨረታው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋምቤላ ገጠር መንገዶች ባለሥልጣን የግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 6 ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተከፍቶ 430 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ካስገቡ በኋላ በዕለቱ ጨረታው ይከፈታል፡፡

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑ ግብር የከፈሉበት፣ ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር ተዛማች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የአገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ብቻ ሲሆን ጨረታው ለማንኛውም ብሔራዊ አቅራቢ ድርጅት ክፍት ነው፡፡ የጨረታ ሰነዱ የተዘጋጀው በአማርኛ ቋንቋ ነው፡፡
  3. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዓይነት የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብርየጨረታ ማስከበሪ በባንክ በተረጋገጠ CPO ለብቻው በማሸግ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ የተደረገበት ሞዴል / አብሮ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጪ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም፡፡
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ረቡዕ 2/3/2013 . ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ዕለት ሲሆን በዕለቱ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ይከፈት እና 430 ሰዓት ይዘጋል፡፡ የጨረታው የመክፈቻው ቀን በሰንበት ወይም በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በማግስቱ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያው መሠረት ሙሉ የጨረታ ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7.  ለበለጠ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

የጋምቤላ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን

የስልክ ቁጥር 047-551-0835/047-551-1175/047-551-2376

ጋምቤላ

የጋምቤላ ክልል ገጠር መንገዶች ባለስልጣን

ገልባጭ: የውሃ ቦቴ: ቼን ኤክስካቫተር: ኤክስካቫተር ባለጃክሃመር: ባለጎማ ኤክስካቫተር

Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 5፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Remaining Time for Bid Submission: Not Fixed

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የኮንስትራክሽን

ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ

አገልግሎት ግዥ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ ቁጥር :- ማ/ኪ/አ/ግ 01/2013

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግንባታ ማሽነሪዎችንና ተሽከርካሪዎችን በቁርጥ ዋጋ ተከራይቶ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች በሚገኙ የመንገድ፣ የግድብና መስኖ፣ የህንጻ ፣ አውሮፕላን ማረፊያ ፣ የደረቅ ወደብ እና ሌሎች የመሰረት ልማት አውታር ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በኪራይ አሰማርቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ገልባጭዶዘር
ገልባጭ (ኳሪ/የድንጋይ መኪና)ግሪደር
የውሃ ቦቴሮለር
ቼን ኤክስካቫተርሎደር
ኤክስካቫተር ባለጃክሃመርየድንጋይ መሰርሰሪያ(ዋግንድሪል)
ባለጎማ ኤክስካቫተርሳንድ ሜከር ክሪሸር

በዚሁ መሠረት እንደ የፕሮጀክቱ ተጨባጭ ሁኔታ ተጠንቶ በተዘጋጀው የቁርጥ የኪራይ ዋጋ መሣሪያዎችን ለማከራየት የምትፈልጉ የመሣሪያ አከራዮች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ  በማንኛውም የሥራ ሰዓት(ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) ቃሊቲ በሚገኘው  የኮርፖሬሽኑ የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችና ማሽነሪ አስተዳደር ዘርፍ በአካል ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን  አከራዮች በምዝገባው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. አከራዮች በምዝገባው ለመሳተፍ የባለቤትነት ደብተር/ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉና በውክልና ከሆነ ህጋዊ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. አከራዮች ማቅረብ በሚችሉት የመሣሪያ ብዛት ያለገደብ በፈለጉት ፕሮጀክትና ዲስትሪክቶች መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  3. በምዝገባው መሣተፍ የሚችሉ አከራዮች መሣሪያዎቻቸውን እንዲያሰማሩ ትዕዛዝ በደረሳቸው በ 1(አንድ) ሣምንት ጊዜ ውስጥ በሥራ ቦታው ማድረስ የሚችሉ፡፡
  4.  በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ያልተመዘገቡ አከራዮች ለሚመለከተው የመንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፊኬት ማግኘት ሲችሉ ሰርተፊኬቱንም ሲመዘገቡ ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. በምዝገባው ለመካፈል የሚፈልጉ አከራዮች ከላይ ከተጠቀሱት  መስፈርቶች በተጨማሪ የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈልገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የተጨማሪ  እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  • የማሽነሪዎችንና ተሸከርካሪ ዝርዝር መረጃ፣ የኪራይ ዋጋቸውን እንዲሁም የፕሮጀክቶቹን ዝርዝር በምዝገባው ወቅት በአካል ማየት ይቻላል
  • ምዝገባው የሚካሄደው ቃሊቲ በሚገኘው የኪራይ መሳሪያ አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሲሆን መ/ቤቱ የሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከተሽከርካሪዎች ማሰልጠኛው ወረድ ብሎ ወረዳ 05 አስተዳደር  ጽ/ቤት ጎን ነው::
  • በአንድ መሣሪያ መመዝገብ የሚቻለው ለአንድ ፕሮጀክት ነው፡፡
  • ለገልባጭ መኪኖች የመጫን አቅም ከ 12 ሜ/ኩብ እና በላይ መሆን አለበት፡፡
  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች/ማስረጃዎች አሟልቶ ለመመዝገብ የቀረቡ አከራይ ድርጅቶች የመሣሪያ/የተሽከርካሪ ፍላጎት ባልተሟላላቸው ፕሮጀክቶች  ምደባ በቀጥታ የሚሰጠው ሲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ቅድሚያ ለተመዘገቡ አከራይ ድርጅቶች ይሆናል፡፡ ምዝገባው የማሽነሪ ፍላጎቱ እስኪሟላ ድረስ ክፍት ሆኖ ያለጊዜ ገደብ ይቆያል፡፡
  • አከራዮች ለመመዝገባቸው ሰነዱ ላይ በስማቸው አንጻር መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ የአገልግሎት ግዥውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 ለበለጠ መረጃ ተመዝጋቢዎች የሚከተለውን አድራሻመጠቀም ይችላሉ።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የኪራይ መሳሪያ አስተዳደር ቡድን ቢሮ

የስልክ ቁጥር ፡-0118694016/0989815730

የኋላውን እያደስን የወደፊቱን እንገነባለን!!

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

Excavater (chain),Grader 140H),Dum Truck(16m3) ብዛት 5(five),Roller(8 ton) and Shower truck

Publish Date:Addis Zemen ( ጥቅምት 2፣ 2013 )
Submission Date:13/2/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 7፡30 ሰዓት
Competition place:በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሸዋ ዞን የሜታ ወልቂጤ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሜታ ወልቂጤ ወረዳ ለመንገዶች ባለሥልጣን ለመንገድ ሥራ አገልግሎት የሚውል

  1. Excavater (chain)
  2. Grader 140H)
  3. Dum Truck(16m3) ብዛት 5(five)
  4. Roller(8 ton) 
  5. Shower truck በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡

  1. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት የአገልግሎት አይነት ህጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፤ መለያ ቁጥር(Tin No) ፤ VAT ያላቸው የአቅራብነት ምስክር ወረቀት ያላቸው ናማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ብር ከጠቅላላ ዋጋ 1% በCPO የጨረታ ዋስትና ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3.  አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና ካሸነፈባቸው ጠቅላላ ዋጋ 10% ብር በCPOማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከወረዳው ገቢዎች ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻያል ሰነዶች ኦርጅናል እና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 2/2/2013 ዓ.ም ቀን ጀምሮ እስከ 13/2/2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 7፡30 ሰዓት ሜታ ወልቅጤ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  6. ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል፡፡
  7. ተጫራቾች ያሸነፉትን የማሽነሪዎች መጓጓዣ በራሳቸው ወጪ የሚሸፈን ጀሆናል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ሳሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ ሜታ ወልቂጤ

ስልክ ቁጥር፡-0919790098/0913472622

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሸዋ ዞን

የሜታ ወልቂጤ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

ገልባጭ

Published on: Addis Zemen ( መስከረም 30፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን

Remaining Time for Bid Submission

1ኛ ግዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ  ማስታወቂያ 



በኦሮሚያ ክልዕ በባሌ ዞን የጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት በ2013 ዓም በጀት 1ኛ ዙር ለጎባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አሽዋ ለማምረት እስካቫተር ማሽን ኪራይ እና በጎባ ከተማ ወስጥ ለውስጥ መንገድ

  • በተለያዩ ቦታዎች አሽዋ ለማስደፋት በኪራይ መልክ ባለ 16 M3 ሜትር  ኪዩብ በላይ (M3) የሚጭን ገልባጭ ዳምትራክ በመከራየት አሸዋ ለማምረትና ለማስደፋት በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዘርፉ ባገልግሎት ሰጪነት የተሰማሩ በውድድሩ ላይ እንዲካፈሉ እየጋበዝን በውድድሩ ላይ ለመካፈልቀጥሎ የቀረቡትን መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ 

  1. ቲን ነምበር ተዘጋቢ መሆኑንና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸወና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል ፡፡ 
  2. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል። 
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮው ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ  ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመግዛት ከጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
  4. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6:30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 እስከ 11፡30  ሲሆን 100 (አንድ መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Acc.No 1000028126712 በማስገባት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡ 
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሠድ ዋናውን እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  6.  የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት 16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 (ሶስት ሰዓት ከሰላሳ )የጨረታው ሠነድ  በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚሁ ዕለት በ4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ 
  7. ተጫራቾች የእስከቨተር ማሽን እና የገልባጭ ዳም ትራክ ሙሉ ወጭውን በመቻል ባከራዩ እንደሚሸፈን  አወቀው  መወዳደር ይኖርባቸዋል፡፡ 
  8. የኪራዩን ዋጋ መ/ቤቱ የሚከፍለውኑ በውሉ መሰረት ሙሉ በመሉ  ሥራውን በጥያቄው መሠረት ማለቁ ሲረጋገጥ ብቻ ነው:: 
  9. ተጫራቾች በቀረበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን  በደብዳቤ ከተገለጸላቸ ው ቀን በኋላ መስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል በተጨማሪም ውል ከገቡ በኃላ ሥራውን በውሉ መሰረት ሰርተው መጨረስ አለባቸው:: 
  10. የግልባጭ ዳም ትራክ ኪራይ እና አሸዋ ለማምረት ኤስከቨተር ማሸን 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ / ብቻ CPO /ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  11.  አሸናፊው ተጫራች የግልባጭ ዳም ትሪክ ኪራይ እና አሸዋ ለማምረት ኤስካቨተር ማሽን የውል ማስከበሪያ የሥራውን ሙሉ ዋጋ 10% (ፐርሰንት) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  13. ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ገ/ኢ/ት/ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 0226612764  መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 



በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን የጎባ ከተማ 

ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት 

You cannot copy content of this page