| Published on: | Place of Bid Competitions:በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ጎ/ዞን የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለአ/ዘመን ከተማ አስተዳደር አገልግሎት ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት ለመሰረተ ልማት አገልግሎት የሚውሉ
- ሮሎ፣ ግሬደር፣
- ዶዘር፣ ሎደር፣
- ሻውል ትራክ እና ገልባጭ መኪና የማሽን ኪራይ ግዥ ለመንገድ ጥገና በጥቅል ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለው የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ናምበር/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከ200000.00/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በድርጅታቸው ስም የተቀረፀ ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
- የሚገዙ የእቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፍኬሽን/ የማይመለስ 100 ብር ብቻ በመክፈል አ/ዘመን/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የአቅርቦት ዘርፍ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 17000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒኦ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አ/ከ/አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ከቀን 9/2/2013 እስከ 29/2/2013 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ የጨረታ ሰነድ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን እንዲሁም ጨረታው ከቀን 30/2/2013 ዓ.ም ድረስ እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ፖስታ /የጨረታ ሰነዱን/ ማስገባ የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 30/2/2013 ዓ.ም 3፡30 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙበት በ4፡00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ሙሉ መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058444 03 43/985 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ከቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ የስራ ቀን ከ2፡30 እስከ 11፡30 አሸናፊው ውል በፍትህ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሎትም ሆነ በተናጥል የማየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ቢሆንም እያንዳንዱ የእቃ ዝርዝር መሞላት አለበት፡፡
- የማሽን ነዳጅ፣ ዘይት እና የሎቪድ መጫኛ እንዲሁም ልዮ ልዮ ወጭዎችን በተጫራቹ /በባለሀብቱ/ የሚሸፈን ይሆናል/ተቋሙ የማይሸፈን/መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የሚጫረቱበትን የማሽን ሊብሬና ቦሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ 20 በመቶ ከፍ 20 በመቶ ዝቅ አድርጎ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ያሸነፋቸውን ማሽኖች በራሱ /በተጫራቹ/ ትራንስፖርት ወጭ እስከሚፈለገው ቦታ ድረስ የሚያቀርብ መሆን አለበት፡፡
የአዲስ ዘመን ከተማ አስ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት