| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 3፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አምቦ |
Remaining Time for Bid Submission
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2013
የአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለመንገድ ሥራ የሚያገለግል ጋረጋንት የሚያመርት ዶዘር (D8R Bulldzer CAT) የፈረስ ጉልበቱ 305 (ሶስት መቶ አምስት) የሆነ በሰዓት አወዳድሮ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል፤
ስለዚህ፡
- ከተጠየቀው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ ፣ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር/Supplier List/ የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል የማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 2% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
- ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነፃ የሆነ የሀገሪቱንና የክልሉን ሕግ የሚያከብር፤
- ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት ስም CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፣
- ከአሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል ፤
- በጨረታ ሠነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል/የድርጅቱ ባለቤት/ ሥም ፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፤የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መገለፅ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ኦሪጅናል ከኮፒው ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ በ18/02/2013 በ4:30 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል:: ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመከፈት አያስቀርም:: ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100/ መቶ ብር/ በመክፈል በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በባንክ ሂሳብ ቁጥር GOV 1412 ወይም 1000015202018 በማስገባት ባንኩ የሚሰጠውን ደረሰኝ/sleep/ በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ገቢ በማድረግ ሰነዱን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 መውሰድ ይቻላል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን በደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ 7(ሰባት) ባልበለጠ ቀናት ውስጥ መ/ቤታችን በአካል ቀርቦ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈረም አለበት::
- ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊቱ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011260-94-48/01123644-62
አድራሻ፡- አምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር
አምቦ ከተማ አስተዳደር አምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት