| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 3፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ቁጥር 01/2013
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት በከፍለ ከተማው ለተለያዩ ሴክተሮች ለሚያስገነባቸው የግንባታ ስራዎች ደረጃቸው GC/BC 5፣ 8 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ተቋራጮች እና በደረጃ አንድ እና ሁለት በልዩ ጀማሪ አማካሪ ኢንተርፕራይዝ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል ::
የሥራዎቹ ዓይነት እንደሚከተሉት ነው፡፡
| ተ.ቁ | ወረዳ | የስራው አይነት | የተቋራጮች ደረጃቸው |
| 1 | ወረዳ 8 እና ወረዳ 13 | ፖሊስ መምሪያ መጸዳጃ ቤት | GC/BC 8 እና ከዚያ በላይ |
| 2 | ወረዳ 14 | ቃሌ ት/ቤት ስፖርት ሜዳ ተጨማሪ ስራ | GC/BC 5 እና ከዚያ በላይ |
| 3 | ወረዳ 7 እና 4 | ወረዳ 7 አስተዳደር ጊቢ እስቶር እናወረዳ 4 አስተዳደር ቢሮ እስቶር ግንባታ ስራ እና መጸዳጃ ቤት | በደረጃ 1 እና 2 በልዩ ጀማሪ አማካሪ |
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በመስኩ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ከሚመለከታቸው አካላት ሕጋዊ ማስረጃዎች ምስክር ወረቀት፣ ብቃት ማረጋገጫ፣ የግብር መለያ፣ ከመንግስት ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡበት ማስረጃ፣ ከገቢዎች እና ጉምሩከ የተሰጠ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው:: ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፣ ከኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ስራ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ Turn over Tax (TOT) ተመዝጋቢ የሆኑ መጫረት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን ጨረታ በኮ/ቀ/ክ/ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 204 ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ተቋራጮች የሚያቀርቡት ሰነድ ዋናውን እና ሶስት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ የፕሮጀክቱን ሥም እና አድራሻ በመጥቀስ በኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ለዚህ ሥራ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2013 ዓ.ም ከ2፡30 – 6፡00 ሰዓት ሰነዱ ተመላሽ ተደርጐ በዚህ ቀን ከሰዓት በኋላ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 204
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም ደብዳቤ ከተደራጁበት ክ/ከተማ ወይም ህጋዊነት ካለው ተቋም የጨረታ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 300 ብር ከፍለው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ለተጠቀሰው የማማከር እና የግንባታ አገልግሎት 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- ከአንድ ሰነድ በላይ መወዳደር ከተወዳዳሪነት ሁሉም ላይ ያሰርዛል በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ እና ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለጎት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 204 በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
- አማካሪው ድርጅት የዲዛይን፣ የስራ ዝርዝር፣ የግንባታ ክትትል እና የውል ማስተዳደር ስራ ይሰራል፡፡
- ተጫራቾች በእጃቸው ላይ ያለ ፕሮጀከት 75% እና ከዚያ በላይ መሆኑን የሚያሳይ ወይም በከፍለ ከተማው ላይ ምንም አይነት ስራ እንደሌላቸው የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የCOC ምዘና ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት