| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 3፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
Remaining Time for Bid Submission (check it)
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ እና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት የሚገኙ ከዚህ በታች የተገለጹትን ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| ሎት ቁጥር | የዕቃው አይነት |
| ሎት 2 | የተለያዩ ያገለገሉ አነስተኛ ተሽከርካሪዎች |
| ሎት 3 | የተለያዩ ያገለገሉ ከባድ ተሽከርካሪዎችና ተሳቢዎች |
| ሎት 4 | የተለያዩ ያገለገሉ የእርሻ እና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች |
| ሎት 5 | የተለያዩ ያገለገሉ የተሽከርካሪ፣ የእርሻና የኮንስትራክሽን መሳሪያ ሞተሮች(ኢንጅኖች)ና ኮምፖነንቶች |
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ::
ሀ) ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እቃዎቹ በሚገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ በተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ እና በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ማለትም ሞጆ፣ (ሀዋሳ (ሻሎ)፣ አሰላ ጎንዴ፣ ባህርዳር (ቁንዝላ)፣ ቻግኒ፣ አርዳይታ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 150.00(አንድ መቶ ሃምሳ ብር ) በመክፈል በተራ ፊደል ለከተገለፁት ቦታ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
ለ) የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሔደው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በዘርፉ ጽ/ቤት እና (በሀዋሳ፣ በአሰላ፣ በባህርዳር፣ በቻግኒ፣ በአርዳይታ እና ሞጆ) ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ክፍት ይሆናል:: ጨረታውም በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ የቅ/ጽ/ቤት ሰነዶች ተሰብስበው ከመጡ በኋላ
በ13ኛው የሥራ ቀን፡
- ሎት 2 ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- ሎት 3 ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
- ሎት 4 እና 5 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ አዲስ አበባ ይከፈታል::
ሐ) ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም፡
- ሎት 2፡- ለአነስተኛ ተሽከርካሪዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)
- ሎት 3፡- ለከባድ ተሽከርካሪዎችና ተሳቢዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ተሽከርካሪ ዋጋ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 4፡- ለእርሻ እና ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት መሳሪያ ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 5፡- ለተለያዩ የተሽከርካሪ፣የእርሻና የኮንስትራክሽን መሳሪያ ሞተሮች (ኢንጅኖች) እና ኮምፖነንቶች ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት፡
- ሎት 5.1 የተለያዩ ኮምፖነንቶች የመግዥያ ዋጋውን ብር 2% እና
- ሎት 5.2 ለየተለያዩ ሞተሮች ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን (የተሸከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ) ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
መ) ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ዕቃ የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ በፊት በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ላይ በዝርዝር በማመላከት ማቅረብ አለባቸው::
ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- የቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የቃሊቲ ባቡር የመጨረሻ ጣቢያ አዋሽ ባንክ ያለበት ህንፃ በስተጀርባ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ህንፃ ያለበት ግቢ የተሽከርካሪዎች አስተዳደርና ጥገና ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 312
ስልክ ቁጥር 0114-43-20-18፣ 011-470-84-70/ 0114-42-5637