The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ህንጻ ለማስገንባት…

Published on: Addis Zemen ( ነሐሴ 26፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:ሀዲያ ዞን

Remaining Time for Bid Submission

የጨረታ ማስታወቂያ 

የሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ህንጻ ለማስገንባት የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC/GC 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከዞኑ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል። 
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በዞኑ ብልፅግና ቅ/ጽ/ቤት ስም ብር 220,000 (ሁለት መቶ ሀያ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee Letter) ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው። 
  3. ተጫራቾች ለፕሮጀከቱ አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጂናል፣ ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ እና የቴክኒካል ኘሮፖዛል አንድ ኦርጂናል፣ ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ(Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጐና ሁለቱንም አቃፊ ማለትም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል አቃፊ ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የኘሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 31ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) በየመጠይቁ ባዶ ቦታዎች ተሞልቶ፣ተፈርሞና ታሽጐ መመለስ አለበት፡፡ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ያለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ 
  4. ረታው በ31ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዞኑ ብልፅግና ፖርቲ ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስተዳደር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ 31ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል። አሰሪው መ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ማሳሰቢያ፡-ከዚህ በፊት በዞኑ ውስጥ ውል ገብተው የግንባታ ሥራ እየሠሩ በውል ጊዜ ያለበቂ ምክንያት ያላጠናቀቁ የሥራ ተቋራጮች ጨረታው ላይ መሳተፍ አይችሉም፡፡ 

  • ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ከገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ አሰሪው መ/ቤት ለሥራው ውል ለመግባት አይገደድም፡፡ 
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 046 555 290 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ 

የሀዲያ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሆሳዕና 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page