The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ለሀብሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት የመርኮታ ጤና ኬላ መጸዳጃ ቤት እና ለመርሳ ጤና ጣቢያ ኢንስነሬተር

Published on: Addis Zemen ( ነሐሴ 26፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:በአ/ብ/ክ/መ/በሰሜን ወሎ ዞን

Remaining Time for Bid Submission

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር 01/2012 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ውሀ ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት

  • የግንባታ ማተሪያሎች፤
  • የውሃ ዕቃዎች እና፤
  • በተለያዩ ቀበሌዎች የውሃ ግንባታ በደረጃ 9 እና ከዚያ በላይ) WC/ እና አርቲዥያኖችን ጨምሮ በእጅ ዋጋ፤
  • ለሀብሩ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በአልማ በጀት ለአሊመንታ ትምህርት ቤት ግንባታ እና ለሀብሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ለአቢዎት ፍሬ ጤና ኬላ ግንባታ ከደረጃ 9 በላይ BC እና GC ተቋራጮች በሙሉ ዋጋ፤
  • ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃ፤ የመኪና ጎማ ግዥ፤
  • ለሀብሩ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በዋን ዋሽ በጀት የመርኮታ ጤና ኬላ መጸዳጃ ቤት እና ለመርሳ ጤና ጣቢያ ኢንስነሬተር በደረጃ 3 እና በላይ BC እና GC ተቋራጮች በሙሉ የእጅ ዋጋ በዘርፉ በተሰማሩበት የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውን አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡ 
  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው በተጠየቁት የግዥ አይነትና ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው 
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200.000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል:: 
  4. በውሉ መሠረት ያሸነፈበትን እቃ ግዢ ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ የሚችል:: 
  5. ማስታወቂያ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃ፤ የመኪና ጎማ ግዥ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአልማ በጀት ግንባታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን እና በዋን ዋሽ በጀት ግንባታና ዕቃ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት እስከ 11፡30 የስራ ቀን ድረስ ብቻ ነው፡፡ 
  6. ጨረታውን ማስከበሪያ 1% በCPO ያስይዛሉ ወይም ገንዘቡን አስቀድሞ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ያቀርባሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና መመሪያ ለእያንዳንዱ ለተጠየቀ ግዥ ሰነድ በማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ዝርዝር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰአት ጨረታው አየር ላይ ከሚቆይበት እስከ ሚቆይበት መጨረሻ ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 12 በመገኘት መግዛት ይችላሉ፡፡ 
  8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃ፤ የመኪና ጎማ ግዥ በ16ኛው ቀን እና ለአልማ ግንባታ በ21ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዋን ዋሽ ግንባታ እና እቃ በ31ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
  9. ጨረታው ለዋን ዋሽ በጀት እቃና ግንባታ በ31ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ በመደበኛ በጀት የጽህፈት መሳሪያ፤ የጽዳት እቃ ፤የመኪና ጎማ ግዥ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፤ ለአልማ በጀት ግንባታ በ21ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ፖስታውን ከፍተን የምናወዳድር መሆኑን ይታወቅ፡፡ 
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡ 
  11. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሙሉ አድራሻ፣ ማህተም፣ ፊርማ እና ሌሎች መረጃዎች አሟልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  13. በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10% የውል ማስከበሪያ CPO ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  14. በጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0333330585 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

በአ/ብ/ክ/መ/በሰሜን ወሎ ዞን 

የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ 

ትብብር ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page