| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 11፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደሴ ከተማ |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2013
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውል 1ኛ በከተማው ውስጥ ለሚያሰራው
- የመንገድ ስራዎች ኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ኪራይ የኦፕሬተር አበል ወጭ ፣ የነዳጅ ወጭ ፣ የቅባትና ዘይት ወጭ ፣ እንዲሁም ሌሎች ወጭዎችን አከራዩ ችሎ በሰዓት ተከራይቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- 2ኛ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ፣
- የህንጻ መሳሪያ ፣
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ፣
- አላቂ እቃ /የጽህፈት መሳሪያ/ ፣
- የቢሮ ቋሚ እቃ፣
- የጽዳት እቃ ፣
- የግንባታ ድንጋይ በሜትር ኩብ የተፈጨ ጠጠር በሜ/ኩብ እና አሸዋ በሜትር ኩብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- 2ኛ የሰራተኞችን ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ በእጅ ዋጋ ማሰፋት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን መወዳደር የሚችሉ መሆኑን
- ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ/ የ2013 ዓ.ም/ የታደሠ የንግድ ወይም የስራ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾችን በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የኤክስካቫተር ማሽን ባለ ጎማ ፣የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ፣ የህንጻ መሳሪያ፣ የሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ ፣ አላቂ /የጽህፈት መሳሪያ/፣ የቢሮ ቋሚ እቃ ፣የጽዳት እቃ፣ የግንባታ ድንጋይ ፣ አሸዋ ፣ የተፈጨ ጠጠር ፣ የሰራተኞችን ደንብ ልብስ የእጅ ዋጋ ማሰፋት አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% ከነቫቱ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያትዕዛዝ (ሲፒአ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው
- ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
- የመጫረቻ ሰነዱ /የጨረታ ሰነዱ/ ጨረታው ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን አርባ ቀን/ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- ተጫራች ለእያንዳንዱ የጨረታሠነድ ማለትም ለኤክስካቫተር ማሸን ባለ ማ ኪራይ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ለተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫ እና ጎማ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ ለህንጻ መሳሪያ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ለሰራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/አላቂ እቃ / የጽህፈት መሳሪያ /፣የቢሮ ቋሚ እቃ፣ የጽዳት እቃ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር፣ ለግንባታ ድንጋይ ፣ ለተፈጨ ጠጠር እና አሸዋ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ የሰራተኞችን ደንብ ልብስ የእጅ ዋጋ ማሰፋት የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል ደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን ግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሣቡን በአንድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ደሴ ከተማ አስ/መንገድ ባለስልጣን ከግዥና ፋ/ንብ/አስ/የስ/ሂደት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሁሉም ጨረታዎች ለተከታታይ 15 ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል በዚሁ ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ለሁሉም እቃዎች የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደሴ ከተማ አስ/መንገዶች ባለስልጣን መ/ቤት 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት ይከፈታል የሚከፈትበት ቀን የበአላት ቀን ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ደሴ ከተማ አስ/ መንገድ ባለስልጣን መ/ቤት ድረስ በራሱ ማጓጓዣ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉና ስለጨረታው በዝርዝር መረጃ ከፈለጉ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር
033 312 91 73/ 033 311 10 41/10 48/ 10 59 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አደራጃ፦ካሪጉቱ መስጅድ ፊት ለፊት
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለደሴ
ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን