| Published on:Reporter ( ጥቅምት 11፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ጅማ በር አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የጨረታ ማስታወቂያ
ተስፋ ድርጅት ቸርችል ጐዳና የሚገኘው ዋና መስሪያ ቤት በመንገድ ማስፋፊያ ምክንያት የህንጻው ፊት ለፊት ግድግዳ በመፍረሱ፣ አስፈላጊውን እቃ፣ ማሽነሪ እና የሰው ኃይል አቅርበው መስራት የሚችሉ BC7/8 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት መጫረት ይችላሉ።
l. የህጋዊነት መመዘኛ መስፈርቶች
- ዋና ምዝገባ ሰርተፍኬት፣
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣
- የደረጃ BC -7/8 ወይም ከዛ በላይ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬት ፣
- የግብር መክፈያ (TIN Certificate) ፣
- የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን (Tax Clearance Certificate) ማቅረብ የሚችሉ :
II. የዋጋ መመዘኛ መስፈርት
- ተጫራቾች የሚሰራውን ሥራ ከቴዎድሮስ አደባባይ ወረድ ብሎ የድርጅቱ ጽ/ቤት የነበረውን፣ በአካል መጥተው በመጐብኘት የሚሰሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን አየር ጤና ከሚገኘው ቢሮአችን በሥራ ሰዓት በመምጣት ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ገዝቶ መውሰድ ይቻላል
ሙሉ አድራሻ፡ጅማ በር አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት
ፓሣ.ቁጥር 30153 /
ስልክ ቁጥር 0113-694249/0113- 693864
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነድ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በመጀመሪያ የህጋዊነት ሰነድ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን የህጋዊነት መመዘኛ መስፈርቶች የማያሟሉ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶቻቸው ሳይከፈቱ ተመላሽ ይሆናል፡፡ ነገር ግን የህጋዊነት መመዘኛ መስፈርቱን ካሟሉት ተጫራቾች መካከል ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ይሆናል። ጨረታው በቀን ጥቅምት 20፣ 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አየር ጤና ቅርንጫፍ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 8፡30 ይከፈታል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።