ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የቋሪት/ወ/የገ/ማሪያም መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት የዉስጥ ለውስጥ መንገድ ጥገናና ከፈታ አገልግሎት የሚውል ዶዘር፣ ግሪደር ኤክስካቫተር፣ ሮለር፣ ሻወር ትራክ፣ ሎደር እና ገልባጭ መኪና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/ ያለው/ያላት
- ግዥው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾችየጨረታ ሰነዱን 100 ብር በመክፈል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው
- ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ይታሸግ እና በዚሁ ቀን ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በቋሪት/ወ/መሪ ማዘጋጃ ቤት በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በ4፡30 ይከፈታል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁጥር 0582620068 በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
- ጽ/ቤቱ ከሚገዛው እቃ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ ማሰራት ይፈልጋል::
- በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ፖራፍ መደረግ አለበት
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ጀምሮ ባሉት በ5 በስራ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማቅረብ ውል መያዝ ይኖርበታል::
- የውድድር ሁኔታ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሞልቶ ከቀረበው ድርጅት ሲሆን እንደ ሎት ከፋፍሎ መሙላት ወይም መጫረት ከውድድር ውጭ ያደርጋል::
- አሸናፊው ያሸነፈውን ስራ በቋሪት/ወ/በገ/ማርያም ከተማ የዉስጥ ለውስጥ የመንገድ ከፈታና ጥገኛ ይሆናል::
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ::
የቋሪት/ወ/የገ/ማሪያም መሪ ማዘጋጃ ቤት
Good Luck!