| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 24፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ፅ/ቤት በክፍለ ከተማው የሚያስገነባቸውን ግንባታዎች ለማሰራት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ የግንባታ ማህበራትን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል እና ማሽነሪዎችን በማቅረብ በሚቀመጠው ጊዜ ውስጥ ያለ ቅድመ ክፍያ ስራውን ማጠናቀቅ የሚችል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ።
| ተ.ቁ | የስራው አይነት | የጨረታ ቁጥር | ደረጃ | የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት | የጨረታ ማስገቢያ | የጨረታ መክፈቻ ቀን |
| 1 | የወረዳ 02 3በ1 ስፖርት ሜዳ ቀሪ ስራ ግንባታ | 012/13 | በኮ/ዘ/ጥ/አ/ኢንተርፕራይዞች አነስተኛ መብቃት እና ከዛ በላይ | በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ | በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ድረስ | በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡15 ሠዓት |
| 2 | የአጋዚያን ት/ቤት G+1 ቀሪ ስራ ግንባታ | 011/13 | በኮ/ዘ/ጥ/አ/ኢንተርፕራይዞች አነስተኛ መብቃት እና ከዛ በላይ |
- ለስራ ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ከአ/አ ኮንስትራክሽን ቢሮ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ፣ ባቅራቢነት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከወረዳ ደብዳቤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው::
- ሥራ ላላቸው ማህበራት የያዙት ሥራ 100% መሆኑን የሚገልጽ ወይም ሥራ እንደሌላቸው የሚገልጽ (ከተጻፈ 1 ወር ያልሞላው) ከፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል በተጨማሪም አሸናፊ ድርጅት የቅድመ ክፍያ ሳይወስድ ስራውን መስራት የሚችል መሆን ይኖርበታል ፡፡
- ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ እያንዳንዱ ገጽ ላይ የማህበሩ ማህተም ተደርጎ አንድ ወጥ ኦሪጅናልና 2(ሁለት) ኮፒው በተለያየ ፖስታ በማሸግ የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሠረት ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በምህድስና ግዢ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠር እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ሰነዱ በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን በዕረፍት ወይም በበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት በምህድስና ግዢ ቡድን 5ተኛ ፎቅ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው(Original) እና የማይመለስ 2 ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ ለማህበራት በነፃ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በዚሁ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በምህድስና ግዢ ቡድን ክፍለ ከተማው ህንፃ 5ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- ከአንድ ሰነድ በላይ መወዳደር ከተወዳዳሪነት ሁለም ላይ ያሰርዛል በተጨማሪም ተጫራቶች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገጾች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላለት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- ተጫራቾች ለስራ ዝርዝሮቹ ያቀረቡት ዋጋ ወቅታዊ ዋጋን ያላገናዘበ ከሆነ ተጫራቾቹን ከጨረታ ያሰርዛል፡፡
- የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማው በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
- አድራሻ:- ማሪዮት ሆቴል ጎን በስተምስራቅ በሚገኘው ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 5ተኛ ፎቅ በምህንድስና ግዢ ቡድን መሆኑን እንገጻለን
ስልክ ቁጥር፡- 011-869-78-10/118-54-60-15
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት