The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

G+5 የቢሮ ህንፃ የዲዛይን ንድፍ ስራ

Published on:Be’kur ( ጳጉሜ 2፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:ባህርዳር

Remaining Time for Bid Submission

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013

የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት በደሴ ከተማ ለሚያሰራው G+5 የቢሮ ህንፃ የዲዛይን ንድፍ ስራውን የሚያዘጋጅ ደረጃ ሁለት (2) እና ከዚያ በላይ የሆኑ አማካሪ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረ ዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በስራ ዘርፍ የተመዘገባችሁ ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳ ተፉ ይጋብዛል፡፡

  1.  የስራ ፈቃድ ደረጃቸው 2 እና ከዚህ በላይ የሆነ፣
  2. ተጫራቾች በመስኩ የተሰማሩ ሆኖ የታደሰ እና ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገበበትን የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬትን ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ባህር ዳር ከተማ ከፖሊስ ኮሚሽን ጎን ከሚገኘው ዋና ኦዲተር መ/ቤት የገንዘብ ያዥ ክፍል(ቢሮ)ቁጥ ር09 የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን በማስፈር ፋይናንሻል እና ቴክኒካል በሚል በ2 ፖስታ ተለይቶ ለየብቻው አንድ ኦርጅናል እና አንድ ፎቶ ኮፒ በተዘጋጀ ፖስታ በማድረግ በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የዲዛይን ንድፍ ስራውን ብቻ ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅበታል፡፡
  6. የጨረታው ሳጥኑ የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ22ኛው ቀን 4፡00 ላይ ተዘግቶ በእለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
  7. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 058-220-1992 (058-226-2719 ባህር ዳር ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ /በተፈቀደላቸው ባንኮች ሲፒኦ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና(bid bond) /ጥሬ ገንዘብ በሞሉት ጠቅላላ ድምር ቫትን ጨምሮ 2 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነድ ላይ ለማግኘት በሀርድ ኮፒ ወይም በሶፍት ኮፒ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሸለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት

ባህርዳር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page