The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የአምቢሲ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክላስ ግንባታ…

Published on:Be’kur ( ጳጉሜ 2፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰከላ ወረዳ

Remaining Time for Bid Submission

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ መምሪያ የሰከላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ለሰከላ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከአልማ በተገኘ የበጀት ድጋፍ አማካኝነት

  • ሎት1 የከበሳ ሃይስኩል የቢሮ አስተዳዳር ግንባታ ለማስጨረስ
  • ሎት2 የአባግስ ሃይስኩል የቢሮ አስተዳዳር ግንባታ ለማስጨረስ
  • ሎት3 የአምቢሲ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክላስ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል ፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
  4. ተጫራቾች ደረጃ 9 እና በላይ መሆን አለባቸዉ
  5. የግዥው መጠን ከብር 200 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. የሚገነቡ የሰራ ዝርዝሮችን መግለጫ /ስፔስፊኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50/አምሳ ብር ብቻ / በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ከጳጉሜ 02/2012 እስከ መስከረም 17/2013 ዓ/ም 11፡30 ድረስ ብቻ ቢሮ ቁጥር 04 መግዛት ይችላሉ
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት(የሞሉትን) ዋጋ 1.5 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ እና በኢ/ዝ የተደራጁ ከሆነ በጨረታ በወጣበት ጊዜ ዉስጥ የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸው ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰከላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳድር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ መስከረም 18/ 2013 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 04 መስከረም 18/ 2013 ዓ/ም በ4፡10 ይከፈታል
  11. አሸናፊ የሚለየዉ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ሆኖ የስራ ዝራዝሩን አስተካክሎ መሙላትና የሁሉንም የነጠላ ዋጋ ያልሞላ በጫራታዉ ወድቅ ይሆናል፡፡
  12. አሸናፊ በተገለጸ ከአምስት(5) ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት(5) ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፉበትን የጨረታ ማስከበሪያ 10 በመቶ በሰከላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ስም በባንክ በተረጋገጠ ስፒኦ በማሲያዝ ዉል መዉሰድ አለባቸዉ በተባለዉ ቀን የማይመጣ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የምንወረስ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  14. በጨረታ ማስታወቂያዉ ያልተካተተ በግዥ መመሪያ የምንገዛ ይሆናል
  15. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0582590442 በመላክ ወይም በስልክ 0582590009/6 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡

የሰከላ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page