The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

11 /የኮንቲነር ዕድሣት ሥራ/

Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 15፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

(በድጋሚ የወጣ)

የግዥ መለያቁጥር፡- ብሐሥ/ኢሕምኢ/የኮንቲነር ዕድሣት ግዥ/066/2013 ዓ.ም የኢትየጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በ2013 በጀት ዓመት 11 /የኮንቲነር ዕድሣት ሥራ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስራት ይፈልጋል መስፈርቱን የሚያሟሉና በየዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ተቋራጮቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በዚህ ጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ፡-

1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በጥሬ ገንዘብ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 5 ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ጠዋት ከ2፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -1፡00 ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡

  • ሀ. የግዥ ኤጀንሲ ሥራ ተቋራጭነት የተመዘገቡ፣
  • ሊ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  • ሐ. ታክስ ክሊራንስ (ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ) የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፊኬት (TN No.)፣

2 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3 ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ ፋይናንሺያል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል እንድ ኮፒ ሠነዶችን አስፈላጊ መረጃዎችን ሁሉ በማካተት እና በማሸግ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓም ድረስ ከኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት አለባቸው

4. የጨረታው አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የጨረታው ውጤት በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ በኢንስቲትዩቱ ግዥ ኬዝ ቲም በመቅረብ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ለመልካም አፈጻፀም ዋስትና በማስያዝ ውል መፈረም አለባቸው፡፡

5 የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች በፈረሙት ውል መሠረት በራሳቸው ትራንስፖርት አሸናፊ የሆኑባቸውን የኮንቲነር ዕድሣት ዕቃዎች ኢንስቲትዩቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የጨረታው አሽናፊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የጨረታ አሸናፊነት ተለይቶ የአሸናፊነት ደብዳቤ ከተሰጠው በኋላ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡

7. የጨረታው ሣጥን ታህሳስ 19/2010 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይዘጋል፡፡

8.የጨረታ ሣጥን ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ኦዲትና የሥነ ምግባር ባለሙያ በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9 ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

10. ኢንስቲትዩቱ በሙሉም ሆነ በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አርበኞች መንገድ ጳውሎስ ሆስፒታል አጠገብ

ስልክ ቁጥር 0112771054/56

ፋክስ 0112758634

የመሣ.ቁ 1242

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩቱ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page