| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 15፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን ተርጫ ድስትሪክት ጽ/ቤት |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ለ2ተኛ ዙር የወጣ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
ተርጫ ዲስትሪክት 003/2013
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን የተርጫ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በስሩ ላሉ ፕሮጀክቶችና ጥገና መንገዶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 ለቢሮ ሠራተኞች ሚኒባስ ሰርቪስ መኪና ከ12 እስከ 15 የመጫን አቅም ያለው ሆኖ እ.አ.አ 2008 ስሪት ዘመንና ከዚያ ወዲህ የተመረተ ሞዴል፣ የመስክ ደብል ካፕ እ.ኤ.አ 2009 እና ከዚያ ወዲህ የተመረተ ሞዴል፣ ብቁ የውሃ ቦቴና ግንባታ ግብዓቶችን ማመላለሻ የሚውል አይሱዚዎች እ.አ.አ 2012 እና ከዚያ ወዲህ የተመረተ ሞዴል
- ሎት 2 የሰራተኛ ደንብ ልብስ ለመግዛት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ይህንን ጨረታ ማስታወቂያ አውጥተናል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ተሳታፊ የሚሆን፡
- ለውድድሩ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን ከሚወዳደረው ስራ የተዛመደ የንግድ ስራ ወይም አገልግሎት ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ምስክር ወርቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከድስትሪክቱ ከግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንቡና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡ የሚቀርበው ሰነድ ጥራቱ የተጠበቀ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በተወዳደሩባቸው በእያንዳንዱ በተወዳደሩበት የመሣሪያ ዓይነት የጠቅላላ ዋጋውን 1% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ ክፍያ ማዛዥ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የተሽከርካሪ ኪራይ ተወዳዳሪዎች በሚወዳደሩበት ሥራ ዘርፍ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ድጋፍ ደብዳቤ በ2011 ዓ.ም እና ከዚያ ወዲህ በዘርፉ ተሰማርቶ የሰራበትን መልካም የሥራ አፈፃፀም ድጋፍ ደብዳቤ ቢያቀርብ ይመረጣል። ይህ አዲስ ፍቃድ ያወጣውን አያካትትም፡፡ ይህም የሚያገለግለው ለመሣሪያ ኪራይ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያየ ፖስታ ለብቻው በማድረግ በተወዳደሩበት የመሳሪያ ዓይነት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በደ/መ/ባለሥ/ተርጫ ዲ/ጽ/ቤት ውስጥ ባለው ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የሚያስገቡበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያን ቀን ከቀኑ ማለትም በ15ተኛው ቀን በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ አከፋፈትን አያስተጓጉልም፡፡ በጨረታ ሠነዱ ውስጥ በተመለከተ መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው።
- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ድርጅት ከመ/ቤቱ ጋር ውል ከገባ በኋላ ተሽከርካሪዎችን በመስፈርቱ መሠረት በቴክኒክ ኮሚቴው ተፈትሾ እንዲገባ ይደረጋል፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ።
የስልክ ቁጥር: 0961244102፣0910005088፣0910063695፣0473450123፡
የደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን ተርጫ ድስትሪክት ጽ/ቤት