| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 14፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ደ/ብርሃን ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በፓኬጅ ቁጥር በከተማ አስተዳደሩ በጀት
- 1ኛ የዳው ዳምትራክ እና ሚስትቡሽ ገልባጭ መኪና
- 2ኛ ሚስትቡሽ ደብል ጋቢና መኪና እና ቶዮታ ደብል ጋቢና መኪና
- 3ኛ የሎደር ማሽን
- 4ኛ የተለያዩ ትራክተሮች
- 5ኛ የእሳት አደጋ መኪና የመለዋወጫ እቃዎች
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በ2013 በጀት ዓመት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ከብር 200000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆኑ የተጫራች እሴት ታከስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሰትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በሎት በጥቅል ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን በአንድ ሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች በከፊል ወይም ቀንሶ መጫረት አይቻልም
- ለእያንዳንዱ እቃ የእስፔስፊኬሽን መግለጫ መሞላት አለበት፤ ነገር ግን የእስፔስፊኬሽን መግለጫው ያልተሞላበት እቃ ቢኖር ተጫራቹ ጽ/ቤቱ የሚፈልገውን ጥራት ያለው እቃ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዓይነት ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፣
- በጨረታው ሰነድ ላይ ማረጋገጫ ያልተቀመጠለት ስርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት አሻሚ የሆነ ፅሁፍ መኖር የለበትም
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/ በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ተው መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለ30 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 1% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/ጋራንት/ በስማቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በሚል አድራሻ በስማቸው ከኦርጅናል ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አብሮ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ አንድ ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታውቂያው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/ አገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 29 በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል :: ዕለቱ ቅዳሜ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቶች በራሳቸው ምከንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ ተሟልቶ ከተገኘ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል ፣
- አሸናፊው ተጫራች ውጤት ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በአሉት 5 የስራ ቀን በኋላ በአሉት 5 ተከታታይ ቀን ውስጥ መዋዋልና በውሉ መሰረት እቃውን የማጓጓዣ ወጭን ችሎ በደ/ብ/ከ/አስ/ግ/ፋ/ንአስ/ደ/ስራ ሂደት ንብረት ከፍል ድረስ ማቅረብ አለበት ።
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፋቸውን የመለዋወጫ እቃዎች ሲያስረክብ በባለሙያ ሲረጋገጥ ተቀባይነት ሳያገኝjትከክል ባይሆን/ ተመላሽ አድርጎ ትከከለኛውን እቃ ማቅረብ አለበት፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የሚያስይዙት ዋስትና ጊዜ እቃው ተጠናቆ ርክክብ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ቢያንስ ለ1 ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
- መ/ቤቱ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ ሙግዛት ይችላል ::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው ፣
- በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 01118906580/011 681 2717/ 28 57 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት