| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 13፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 12/2013
የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ፅ/ቤት ለክፍለ ከተማው ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራ የሚሠሩ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ኃይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውስድ ይችላሉ፡፡
| ተ.ቁ | የስራው ዓይነት | የሚሰሩበት ወረዳ | ደረጃ | የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን | የጨረታ ማስገቢያ ቀን | የጨረታ መክፈቻ ቀን |
| 1 | የወረዳ 03 ወጣት ማዕከል እድሳት ስራ | ወረዳ 3 | GC 5/BC 5 እና ከዚያ በላይ | በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን 10፡00 ሰዓት | በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት | በጋዜጣ በወጣበት 16ኛው ቀን የስራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ጀምሮ |
| 2 | የወረዳ 08 ወጣት ማዕከል እድሳት ስራ | ወረዳ 8 | GC 5/BC 5 እና ከዚያ በላይ | በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን 10፡00 ሰዓት | በጋዜጣ ከወጣበትቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት | በጋዜጣ በወጣበት 16ኛው ቀን የስራ ቀን ጠዋት 4፡30 ሰዓት ጀምሮ |
- በዘርፉ 2013 የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ሆነ አማካሪ ከመስተዳድሩ ኮንስትራክሽን ቢሮ ተመዝግቦ የብቃት ማረጋገጫ ወይም የአጭር ምዝገባ ሰርተፊኬት ሳይዝ በሴክተሩ መሳተፍ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት 3ተኛ ፎቅ ቀርበው በስራ ሰዓት መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በእለቱ ባለቤቱና ተወዳዳሪዎች ወይንም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በጽ/ቤቱ ጠዋት 4፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond 70,000.00 ብር ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ለ90 ቀናት የሚያገለግል ሆኖ ከኦሪጅናል ቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- በተጨማሪነት ስራውን በምን ያህል ጊዜ እንደሚጠናቅቁ የሚገልጽ የስራ መርሃ ግብር /ወርከ ስኬጁል/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱንና የተወዳደሩበት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተቋራጮች የስራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፕን በሰም በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ16ኛው ቀን በአራዳ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት፡፡ ይህም ከሆነ ተጫራቾች ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል ።
- በኮንስትራከሽን ጽ/ቤት በወጡና በሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች ላይ ተቋራጭ ከአንድ በላይ ጨረታ መሳተፍ አይቻልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማሰታወቂያው በወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ /ክ/ከ/ኮ/ጽ/ቤት መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት
የግዥ ቡድን