The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የተለያዩ ፕሮጀክቶች የክትትልና ቁጥጥር፣ ኮንትራት አስተዳደርና ዲዛይን ማስተካከያ (Design Modification) ሥራዎች

Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 16፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/ከ/ክ/ከ/ኮ/ጽ/ቤት/ ም/ቡ/013/2013

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የተለያዩ ፕሮጀክቶች የክትትልና ቁጥጥር፣ ኮንትራት አስተዳደርና ዲዛይን ማስተካከያ (Design Modification) ሥራዎችን የሚሰሩ አማካሪዎችን እወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

  1. ተጫራቾች ለሥራው ህጋዊ ፈቃድ ኖራቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፣ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ የምሥክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምሥክር ወረቀት ያላቸው፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ አጭር ምዝገባ ያደረጉና የ2013 ዓ.ም ያሳደሱ አማካሪ ድርጅቶች መሆን ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የጫካ ሜዳ ድግፍ ግንብና አጥር ግንባታ ሥራ፣ ቢላል መስጅድ አካባቢ የድሬኔጅ ሥራ፣ ቀስተ ደመና ት/ቤት አካባቢ ድሬኔጅ ግንባታ ሥራና ኢትዬ ጠቢብ ሆስፒታል ፊት ለፊት አካባቢ የድሬኔጅ ግንባታ ሥራ፣ ወረዳ 4 ፖሊስ ካምፕ ውስጥ መፀዳጃ ቤት ግንባታ፣ አጥር ግንባታ፣ ካፌ፣ ማዕድ ቤትና የጥበቃ ማማ ግንባታ ሥራ
  3. ከላይ በተጠቀሰው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግንባታ አማካሪ ደረጃ ሦስትና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርባቸዋል::
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በአዲሰ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ 4ተኛ ፎቅ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን ስልክ ቀጥር 0118-27-89-97 ድረስ በመምጣት ከታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም 11፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ 300 (ሦስት መቶ) ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::
  5.  ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በመሙላትና በሰም በማሸግ የጨረታ መመሪያ በሚያዘው መሠረት ከዋናው ሠነድ በተጨማሪ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሠነድ ሁለት ሁለት ኮፒ እንዲኖረው በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ 4ተኛ ፎቅ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሣጥን ታህሳስ 27 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሠነዱን ቴክኒካል ሠነድ/technical proposal/ እና ፋይናንሻል ሠነድ /financial proposal/ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ ቀን ታህሳስ 27/2013 ዓ.ም ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት / technicalproposal /በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሕንፃ 4ተኛ ፎቅ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዥ ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) የጨረታ ዋጋ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ ትዕዛዝ (CPO) ወይም LNCONDITIONAL BANK GUARANTEE በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ሥም ማስያዝ አለባቸው።
  8.  በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሠነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የሥራ ዝርዝር ዋጋ Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ሥርዝ ድልዝ ካለ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላለት የሥራ ዝርዝር እንዲሁም የሥራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሠርዛል።
  9. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በክፍለ ከተማው ኮንስትራክሽን ት/ቤት የምህንድስና ግዥ ቡድን በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል።
  10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- መድሃኒያለም መሰናዶ ት/ቤት አካባቢ ራስ ኃይሉ ስፖርት ማዕከል ጎን በሚገኘው የክፍለ ከተማው ሕንፃ 4ኛ ፎቅ ላይ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page