| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 19፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ጅጅጋ ሶማሌ ክልል |
Remaining Time for Bid Submission (Check it!)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር SRS-IBDB/FDW/17/2013
የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ የፈትወሊ ቀበሌ ኤረር ወረዳ ዳይበርሽን ሥራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታው እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ጅጅጋ ከሚገኘው የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ ልማት ቢሮ በመገኘት የስራውን ዝርዝርና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ) በመከፈል መግዛት ይቻላሉ፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ ስራ ላይ የሰሩ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣበት በሰባተኛው የስራ ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት መስሪያ ቤቱ በሚገኝበት ጅጅጋ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር +251 25 77 53 595/96
ፋክስ ቁጥር፡- +251 25 77 53 598
ጅጅጋ ሶማሌ ክልል
የሶማሌ ክልል መስኖ እና ተፋሰስ
ልማት ቢሮ