| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 8፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (ኢኢግልድ) ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለያዩ የአይቲ ዕቃዎች እና የሰርቨር ክፍል ዕድሳት የአገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1. ዩፒኤስ ባትሪ (UPS 12kw)
- ሎት 2 ቴሌቪዥን ከነሙሉ ዕቃው /Led Television 427 እና ሪሲቨር
- ሎት 3. የውሃ ማጣሪያ እና
- ሎት 4. የሰርቨር ክፍል እድሳት /Renovation/
ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዝርዝር የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀትና ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በጨረታ እንዲሳተፍ የተፃፈላቸው የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ ቡድን በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በሁሉም ወይም በተወሰኑት ሎት መጫረት የሚቻል ሲሆን፣የሚወዳደሩባቸውን የተለያዩ የአይቲ ዕቃዎች እና የሰርቨር ክፍል ዕድሳት የአገልግሎት ግዥ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዳቸው በተለያዩ ፖስታዎች በማድረግ እንዲያቀርቡ እያሳሰብን፣ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በማግስቱ በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢኢግልድ ዋና መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎት ለጨረታ ማስከበሪያ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት (Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise) ስም በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፖስታ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አዲስ አበባ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ አካባቢ በስተሰሜን አቅጣጫ የባቡር ሃዲዱን ተሻግሮ ወደ ዮሃንስ በሚወስደው መንገድ ጣሊያን ሰፈር (የቀድሞ ጅንአድ መ/ቤት)፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ:- በስልክ ቁጥር 01-13-69-20-36 /0113-69-27-11 በመደወል ወይም በድረ ገጽ www.mewit.com.et ወይም www.eiide.com.et በመጎብኘት ማግኘት ይችላሉ
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት