| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 5፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በሰሜን ወሎ ፕሮግራም ጽ/ቤት በጉባላፍቶ ወረዳ ዘውር ጎተራ ቀበሌ |
Remaining Time for Bid Submission
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ውመን ኢምፓወርመንት – አክሽን (Women Empowerment –Action) በሰሜን ወሎ ፕሮግራም ጽ/ቤት በጉባላፍቶ ወረዳ ዘውር ጎተራ ቀበሌ አንድ የመስኖ አውታር ለመገንባት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉና ከታች የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ በጠቅላላ የስራ ተቋራጭ ወይም በውሃ ስራ ዘርፍ ላይ የተሰማራችሁ በጨረታው እንድትሳተፉ እናሳውቃለን፣
- የቲን ምዝገባ ማስረጃና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ከዚህ በፊት በተለይም በ2011 እና በ2012 ዓ.ም ተመሳሳይ ስራዎችንመስራታቸውንና በብቃት ማከናወናቸውን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከአሰሪ መስሪያ ቤት ማቅረብ የሚችሉ፣
- በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በጠቅላላ የስራ ተቋራጭ ወይም በውሃ ስራ ዘርፍ ደረጃ 9 እና ከዚህ በላይ ፍቃድ ያላቸው ሲሆኑ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታው ዝርዝር ዋጋ የተሞላበት ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በአካል መቅረብ ይኖርበታል፣
- ሰነዱ ላይ የእጩ ተወዳዳሪው ስም ፊርማና ማህተም መመታት ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ 2% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝር መሙያ ፎርም ከድርጅቱ መውሰድ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናትና በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ድረስ ብቻ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፣
- ተጫራቾች የሚያስገቡበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሁሉንም አይነት ግብር ያካተተመሆን አለበት፣
- አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባሉት አምስት የስራ ቀናቶች ውል መፈፀምና ወደ ስራ መግባት ይኖርበታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡- ውመን ኢምፓወርመንት – አከሽን (Women Empowerment Action) ሰሜን ወሎ ፕሮግራም ጽ/ቤት መርሳ ከተማ፡፡
ስልክ ቁጥር፡ 033-333-04-91
ውመን ኢምፓወርመንት – አክሽን
ዋና መስሪያ ቤት