Published on: Addis Zemen ( መስከረም 9፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ሕ/ከ/መንግስት በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ እረሻ ተፈ/ሀ/ል/ጽ/ቤት 2013 በጀት ዓመት በወረዳ ማእከል ሊያሰራ ላሰበው የህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቢሮ ግንባታ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን ማሰራት ይፈልጋል።
- በኮንስትራክሽን ዘርፍ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 5/GC/BC እና ከዛ በላይ የሆኑ።
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የንግድ ፍቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፡- የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና ምስክር ወረቀት ዋናውን በማቅረብ በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።
- ጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ መቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል)ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ለእያንዳንዳቸው አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሰም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ የፋይናንሻል እና ቴከኒካል ዶክመንቱን በጥቅሉ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ በማህተም መመታት እና መፈረም አለበት።
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቶች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እና እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፤ የሎት ቁጥር፣ የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩ ስልከ ቁጥር በመግለጽ መፃፍ አለበት።
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ተኛው ቀን ወይም 16ተኛው ቀን የበአል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሰራቀን የሚውል ሆኖ በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ተኛው ወይም 16ተኛው ቀን የበዓል ወይም የዕረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚውል ሆኖ በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በምዕራብ ኦሞ ዞን የቤሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ ዋና ጽ/ቤት