| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 28፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check It!
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ዲዲ/02/2013
መ/ቤታችን በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን የዳዬ ዲስትሪክት ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገነቡ መንገድ ሥራ ፕሮጀክቶችና ድልድዮች እንዲሁም ለሚጠገኑ መንገድ ጥገና መስመሮች አገልግሎት የሚውሉ አይሱዙ፣ ሚኒባስ፣ ደብል ጋቢና ፒክ አፕ እና ውሃ ቦቴ መኪናዎችን ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችለውን የዘመኑን ግብር የተከፈለበትን፣ ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ የፋይናንሻል ፕሮፖዛሉን በተለያየ ፖስታ ከማድረግ አንድ ዋና እና አንድ ኮፒ “ኦሪጂናል” እና ኮፒ በማለት እና የጨረታ ማስከበሪያውንም በተለየ ፖስታ ለብቻው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00/ ሃምሳ ብር በመክፈል ከዲስትሪክቱ የቢሮ ቁጥር 01 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ዜግነትን ሳይመለከት ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው::
- አቅራቢዎች ጨረታውን በዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉበት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 6.00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታውን ማቅረብ አለባቸው:: ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም::
- ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ::
የዳዬ መንገድ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፋይናንስና ሎጂስቲክ አስተዳደር
የስልክ ቁጥር 0912863927
ዳዬ ኢትዮጵያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መንገዶች ባለሥልጣን
የዳይ ዲስትሪክት ጽ/ቤት