| Published on:Reporter ( ታኅሣሥ 4፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
PT/06/2020
ኩባንያችን በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ገርጂ የሚገኘውን G+5 ህንፃ በጨረታ አወዳድሮ ለማስጠገን ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ደረጃቸው GC/BC 6 እና ከዛ በላይ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን፤ የንግድ ፍቃድ እና የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ በመያዝ በኩባንያው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከዋናው መስሪያ ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውስድና መወዳደር ይችላሉ::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO እና የባንክ ወይም የኢንሹራንስ ጋራንቲ በማስያዝ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሠነዱን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ እስከ ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 በሚገኘው ፕሮቴክሽን ሀውስ” በዋናው መ/ቤት መግቢያ ላይ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል:: የጨረታው መመዘኛ ሂደት 30% ቴክኒካል 70% ፋይናንሻል መሆኑን እናሳውቃለን::
ጨረታው ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በኩባንያው የሰራተኞች ክበብ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ኩባንያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ
ኒያላ ኢንሹራንስ አ.ማ
011-6-62-66-67 መጠየቅ ይችላሉ::
አዲስ አበባ