The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

G+4 የመማሪያ ህንጻ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 19፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት ስር ከሚያስገባቸው ውስጥ የመማሪያ ህንጻዎች ግንባታ ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ኃይልና ማሽነሪዎችን በማሟላት ከዚህ በታች ለተጠቀሰው ግንባታ የሚሰሩ ደረጃ 5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ በህንፃ ወይም ጠቅላላ ስራ ተቋራጮችን (Bር/GC-5) በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ሎትየፕሮጀከቱ ዓይነትየሚገነባበት ት/ቤትየሚሠራበት ወረዳ
ሎት 1G+4 የመማሪያ ህንጻጀሞ 101
ሎት 2G+4 የመማሪያ ህንጻጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ06

ከላይ በተጠቀሰው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራች ለሥራው የታደሠ የንግድ ፍቃድ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የብቃት ማረጋገጫ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 የሥራ ቀናት ብቻ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመከፈል የጨረታውን ሠነድ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን። ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ ፋይናንሽያል 2 ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ለየብቻው እንዲሁም ቴክኒካል 2 ኮፒ እና አንድ ኦርጅናል ለየብቻው በማሸግና CPO ኦርጅናል ቴክኒካል ሠነድ ወስጥ ብቻ ኣሽጎ በማስገባት እንዲሁም ለየብቻ የታሸጉትን የቴከኒካል ሠነዶች ሶስቱን አንድ ላይ በማሸግ፣ ለየብቻ ሶስቱን የታሸጉትን የፋይናንሺያል ሠነዶች አንድ ላይ በማሸግ በመጨረሻም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ መመሪያው በሚያዘው መሠረት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ እስከ 4፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ብቻ ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በዕለቱ ልክ በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) በክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በባንከ ጋራንቲ (unconditional Bank Guarantee) ጨረታው ከሚከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀን የሚቆይ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ማሳሰቢያ፡

  • ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዕዛዝ (CPO) ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  • ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሠነድ ላይ ትከክለኛ አድራሻቸውን የፕሮጀከት ባለቤቱን አድራሻ በመፃፍ እንዲሁም መፈረምና ህጋዊ ማህተማ ማድረግ አለባቸው።
  • በክ/ከተማው ስራ ያላቸው ተቋራጮች ስራውን ከ70% በላይ ስለማድረሳቸው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አያይዘው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  • ስርዝ ድልዝ መረጃና ዋጋ ማቅረብ ከጨረታው ያሠርዛል።
  • ተጫራቹ ከአንድ ሎት በላይ ከተጫረቱ ከጨረታው ያሠርዛል።
  • አሠሪ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡ ለቡ መብራት አደባባይ አጠገብ ሴፍዋይ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03

ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ

ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page