Published on: Addis Zemen ( መስከረም 7፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ባሌ
Remaining Time for Bid Submission
በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ዞን በጎባ ከተማ የሚገኘው ተስፋ ቁጠባና ብድር ሃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበር በጎባ ከተማ ጨፌ ሆራ /03/ቀበሌ በሚገኘው በ 640 ሜ ላይ G+3 የገበያ ማዕከል ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ለህንጻው ግንባታ የሚያስፈልጉት ማቴሪያል በማህበሩ የሚቀርብ ሲሆን የ GC5 እና ከዚያ በላይ ተቋራጮችን በእጅ ዋጋ ብቻ እወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል :: ስለዚህም ከዚህ በታች ያሉትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችል ተቋራጭ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈለና የታደሰ ህጋዊ የGC5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- ተጫራቹ የ3 ዓመት እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/CPO/ በባንክ የተረጋገጠ 5% (አምስት ፐርሰንት) በማህበሩ ስም አዘጋጅቶ ማስያዝ አለበት፡፡
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) ከምስራቅ ጎባ ቀበሌ ውስጥ ከሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናው እና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተጫራቹ ፋይናንሻል ጨረታ ሲሞላ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ሰአት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰአትተዘግቶ በዚያው እለትከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በማህበሩ ጽ/ቤት ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ውክልና ባለው አካል ባሉበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰአት ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- አሸናፊው ተቋራጭ ማሸነፉ ስማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ3ኛው ቀን በማህበሩ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል የመፈፀም ግዴታ አለበት። በተጠቀሰው ቀን ቀርቦ ውል የማይፈፅም አካል ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ/ PO/ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ሌላው ዝርዝር ሁኔታዎች በጨረታ መመርያ ላይ በወጣው ደንብ መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ህጋዊ መብት አለው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በጽ/ቤቱ የስልክ ቁጥር 0226611839/0919839094 ደውሎ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ተስፋ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ
የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበር