The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

G+3 የንግድ ህንፃ ግንባታ…

Published on:Be’kur ( መስከረም 4፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:ደሴ

Remaining Time for Bid Submission

ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ የግንባታ የጨረታ ማስታወቂያ

የወል ኀ/የተ/ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን በጃማ ወረዳ ደጎሎ ከተማ ውስጥ ማስገንባት ለፈለገው G+3 የንግድ ህንፃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ለህንፃ ግንባታው የሚያስፈልገውን

ማቴሪያል አቅርበው የሚሰሩ ሲሆን ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የም ታሟሉ ከደረጃ G C/BC 5 እና ከዚያ በላይ ያሉ ስራ ተቋራጮችን ለጨረታ ይጋብዛል ፡፡

  1. ተጫራቾች ለ2012/2013 ዓ/ም የሚያገለግል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ በመያዝ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ማንኛውም ተጫራች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ያላቸው፣
  3. የተጫራች እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ከላይ የተገለፀውን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው ለተወዳዳሪ ክፍት ሆኖ የሚቆየው በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ጨረታውን የሚዘጋበትን ቀን ደግሞ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሲሆን እንዲሁም በተመሣሣይ ሰዓት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰነዱን ከገዙበት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለመጫረት የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለአንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 በመክፈል በደሴ ከተማ ደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ግቢ ውስጥ በደቡብ ወሎ ዞን ህብረት ስራ ማህበራት ማስፋፊያተጠሪ ጽ/ቤት የማደራጃና ግብይት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን የፋይናንሽያልና የቴክኒካል ፕፖዛል ዋናና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው ታሽጐ በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱ በጨረታ ሰነዱ የሰጠው ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም፡፡
  11. አሸናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች ከአሁን ቀደም በያዛቸው ፕሮጀክቶች ላይ አሰሪው መስሪያ ቤትም ሆነ ከስራና ልማት ቢሮ/መምሪያ/ ማስጠንቀቂያ ያልቀረበባቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  13. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ መኖር አለበት፡፡
  14. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም ለመለየት አሻሚ የሆኑ ነገሮች መኖር የለባቸውም፡፡
  15. አሸናፊው ተቋራጭ አሸናፊነቱ ከተገለፀበት በ10 ቀናት ውስጥ የሚጠየቀውን የመልካም አፈፃፀም ዋስትና/ኢንሹራንስ/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  16. አሸናፊው ተቋራጭ የስራ መርሃ ግብር፣ የሰው ሃይል አጠቃቀም የማቴሪያልና ፋይናንስ ፍሰት አጠቃላይ መርሃ ግብር እንዲሁም የክፍያ አጠቃቀም የሚያሣይ መርሃ ግብር በማቅረብ ከጽ/ቤቱ ጋር ውለታ መውሰድ ይጠበቅበታል፡፡
  17. መስሪያ ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ብዛት እና አይነት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
  18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0931623651 ወይም 0912855990 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የወል ኀ/የተ/ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማህበራት ዩኒየን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page