Published on: Reporter ( መስከረም 17፣ 2013 ) /Place of Bid Competitions:Addis Ababa or Bahirdar
Remaining Time for Bid Submission
የህንፃ ማጠናቀቂያ ግንባታ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡-BIB/009/2020
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አማ በባህር ዳር ከተማ ፤ ቀበሌ 16 ፤ ጣና ክፍለ ከተማ ለሚገኘው ባለ ሶስት ወለል (G+3) ህንፃ ቀሪ ግንባታዎችን እና የማጠናቀቂያ ሥራዎችን ለማከናዎን G.6 እና በላይ የስራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የማጠናቀቂያ ግንባታ ሥራውን ለማስጨረስ ይፈልጋል::
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ የስራ ተቋራጮች በጨረታው መሳተፋ ይችላሉ።
- GC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ከዚህ በፊት የግንባታ ሥራ መስራታቸውን ወይም እየሰሩ መሆኑን የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ መንግስታዊ ከሆነ ድርጅት አሊያም ከግል ድርጅት ፤ ማህበር ወይም ተቋም አንዲሁም የመልካም ሥራ አፈጻፀም ማምጣት የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለ2013 ወይም ለ2012 የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፤ የግብር መክፈያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN NUMBER ፤ የቫት መክፈያ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት NAT REGISTRATION CERTIFICATE/ እና ከክልሉ ከተማ ልማት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም ከፌደራል ስራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ለ2012 ዓ.ም የታደሰ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- ተጫራቾች ከመስከረም 18 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በቡና ኢንተርናሽል ኢማ ሂሳብ ቁጥር 1019601000609 በማንኛውም የባንኩ ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ ቦሌ ሩዋንዳ አከባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ ከንብረትና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ወይም ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አማ ባህርዳር ዲስትሪክት መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) እውቅና ካለው የፋይናንሽያል ተቋም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም ሲፒኦ በተናጠል በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በመሙላት ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒውን በመለየት ፤ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያየ ፖስታ በማሽግ ፤ ትክክለኛ የራሳቸውን እና የሰሪውን ድርጅት አድራሻ በመጻፍ በፖስታ አሽጎ እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ የጨረታ መክፈቻ አደራሽ እንዲሁም ባህር ዳር ከተማ በሚገኘው የዲስትሪክት ቢሮ ይከፈታል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
ቡና ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ የባለራዕዮች ባንክ!!
ስልክ ቁጥር 011-158-0869
0912-00-64-58