| Published on:Addis Zemen ( ጥቅምት 5፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:በአማራ ብሄራዊ..የአንኮበር ወረዳ |
Remaining Time for Bid Submission
በድጋሚ የወጣ የግንባታ ሥራ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብናኢኮኖሚ ትብብር ጽ ቤት የጎረቤላ ከተማ 01 አስተዳደር ጽ/ቤትበሰጠው ውክልና መሰረት በጎረቤላ ከተማ ላይ ለሚያሰራው G+2 የንግድ የገበያ አዳራሽ/ የህንፃ ግንባታ ካሁን በፊት ስራው ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች የቆመ ሲሆን ባሁኑ ደረጃ 15% ተሰርቶ ቀሪ85% ስራውን ለማስገንባት እንዲቻል ህጋዊ ድርጅቶችን በግልፅጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት:
- በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊንግድፍቃድያላቸው ደረጃ 7GC/BC ከዚያ በላይ የሆኑ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬትያላቸው እንዲሁም በመልካም የስራ አፈፃፀማቸው የታወቁለዚህም መረጃውን ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN / ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ MAT/ ከፋይነት የተመዘገቡመሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብየሚችሉ፣
- ለስራው የሚያስፈልጉ ሚክሰር፣ ቫይብሬተር ያለውያላት መሆን አለባቸው፤
- የኮንስትራክሽን ስኬጁል ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘውማስገባት የሚችሉ፤
- በማንኛውም ቦታ ከአንድ በላይ ስራ ያልያዘና ለዚሁም ስራውበምክንያትነት ያልቆመ ያላቋረጠ ለመሆኑ ማስረጃ ያለው፣
- ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥርከ1-7 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንኮበር ወረዳ ገንዘብናኢኮኖሚ ትብብር ዋ/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስዘመን ጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ 21ኛው ቀን6፡30 ሰዓትድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቀደም ሲል በወጡ በመ/ቤቱ ጨረታዎች የገባውንግዴታ ሳያከብር በመቅረቱ ስልጣን ባለው አካል የታገደ ወይምጨረታውን ባወጣው መ/ቤት ቀደም ሲል በውሉ መሰረትጀምረው ያቋረጡ ከሆነ በጨረታው ላይ አይሳተፉም::እንዲሁም ጨረታውን ባለማከናወናቸው በድርድር ላይ ያለተጫራቶችም አይሳተፉም .
- የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ከ1% የማያንስ በጥሬ ገንዘብወይም በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ወይም በባንክ በተረጋጋጠቼክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ስፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋርታሽጎ ማቅረብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሲፒኦ የሚያቀርብ ከሆነለአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ተብሎካልመጣ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት የለውም::
- የጨረታ ሰነድ የሚገባው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የካላንደር ቀናትየሚወዳደሩ ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረውዋና እና ኮፒ በመለየት በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉአድራሻ በመግለፅ አንኮበር ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት ለዚሁስራ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት አለባቸው፣
- . የጨረታው የመጨረሻ ማስገቢያ ቀን በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30ሰዓት ድረስ ነው
- ጨረታው የሚከፈተው በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ታሽጎወዲያውኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎችበተገኙበት ወይም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ 21ኛ ቀን በስራቀን ላይ የማይውል ከሆነ በቀጣይ በሚመጣው ስራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፣
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ በ5ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙ እና የውል ማስከበሪያካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢይሆናል፣
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያከጠቅላላ ዋጋው 10% ማስያዝ ይኖርበታል፣
- ቀሪ ዝርዝር ስራዎችን ከሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘትይችላሉ
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊልየመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0116230177/ 0116230137 ደውለው ይጠይቁ፣
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
የአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚትብብር ጽ/ቤት