Published on: Addis Zemen ( ነሐሴ 29፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡- ECWCT/NCB/PW/06/2013
- የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን Design-Build of Soil Protection (Shoring), Excavation and Earth Works for 4B+G+21 Office Building ለፌዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ፕሮጀክት ግዥ ለመፈፀም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ብቁ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ነገር ግን በአቅራቢዎች ዝርዝር ያልተመዘገቡ ተጫራቾች ለሚመለከተው “የመንግስት መ/ቤት በማመልከት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ከጠቅላላው ኮንትራት ዋጋ 1% (አንድ በመቶ) ነገር ግን ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የማይበልጥ በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና (unconditional Bank guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
- በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፣ ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር ተዛማጅ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት እና በጨረታው ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢዎች ቢሮ ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማሰረጃ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6፡30 በግዥ መምሪያ (የህንፃ ዕቃዎች ግዥ ቡድን) በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሠረት ሲሆን ጨረታው ለማንኛውም አቅራቢ ክፍት ነው፡፡ የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ በሚገኘው የግዥ መምሪያ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ከመገናኛ ወደ ሀያት በሚወስደው መንገድ በግራ በኩል ጉርድ ሾላ ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ህንፃ 200 ሜትር ገባ ብሎ አንድነት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡+251-118 72 30 86
ፋክስ፡- +251-16 67 6090 ፖስታ ሳጥን ቁጥር፡ -21952/1000
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን