ግንባታ እና የጥገና ሥራዎች
Published on: Addis Zemen ( ነሐሴ 28፣ 2012 ) /Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ
Remaining Time for Bid Submission
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ./ብግጨ/01/2013 ከዚህ በታች የተገለፁትን የግንባታ እና የጥገና ሥራዎች ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
| ተ.ቁ. | አሠሪው መ/ቤት | ምድብ | የሥራ ደረጃ | መሸጫ ዋጋ | የጨረታ መክፈቻ ቀን |
| 1 | ዋናው መ/ቤት | ሎት 1 | ቢሲ/ጂሲ6 እና ከዚያ በላይ | ብር 500 | መስከረም 21ቀን 2013 ዓ.ም |
| 2 | የተ/ጥገና አስተዳደር ዘርፍ | ሎት 2 | ቢሲ/ጂሲ7 እና ከዚያ በላይ | ብር 300 | መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም. |
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ሆነው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የ2012 ዓ.ም. የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ ምስክር ሠርተፊኬት ያለው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሁም ከገቢዎች ሚኒስቴር ክሊራንስ (የምስክር ወረቀት) ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዋናው መ/ቤት ኮርፖሬት ግዢና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 110 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም የኢንሹራንስ ዋስትና ወይም (un conditional bank guaranty) በድርጅቱ ስም ማስያዝ አለባቸው። የጨረታ ዋስትናው ለብቻው በአንድ ፖስታ ውስጥ ተደርጎ እና አድራሻ ተፅፎበት የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት መቅረብ አለበት፡፡ ለጨረታው የተሰጠ ዋጋ ለ 60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው እንደተገለጸላቸው ከ 10 ቀናት በኋላ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (Performance bond) የጠቅላላ ዋጋውን 10% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም የኢንሹራንስ ዋስትና ወይም (un conditional bank guaranty) በማስያዝ ውል ይፈራረማሉ ::
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ መሰረት ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በተለያዩ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነዱ ዋና እና ኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለሎት 1 እስከ መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሎት 2 እስከ መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት በተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የሁለቱም ፕሮጀክቶች የሚከፈቱበት ቀን ከላይ በሰንጠረዡ ላይ በተመለከተው መሠረት ሆኖ ሰዓቱ በተመሳሳይ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ- ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
ስልክ ቀጥር : + 251-14423608 /+251-14420797/251-14708736
አዲስ አበባ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን