The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

አጥር ማሳጠር ግንባታ ስራ

Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 10፣ 2013 )Place of Bid Competitions:Addis Ababa
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር MOR BG-03/2013

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር በ2013 በጀት ዓመት ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ ቀጥሎ የተገለፀውን የግንባታ አገልግሎት ስራ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስራዎቹን የሚያመላክተው የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ ተመልክቷል፡፡

በተ.ቁየስራው አይነትየጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን
1የአጥር ማሳጠር ግንባታ ስራ ግዥ30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ)

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ፡፡
  3. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ፡፡
  4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት
  5. የደረጃ ስድስት (6) እና ከዚያ በላይ የስራ ተቋራጭ BC/GC መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረስት ቼክ (cp.) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር አንድ መቶ (100.00) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ መገናኛ አካባቢ ከሚገኘው የባለሥልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት የግዥ ቡድን ህንፃ መ ቢሮ ቁጥር 301 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከጥር 05 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በፊት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታውም በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረስትቼክ (c.p.o) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ስማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • ስልክ ቁጥር 0116-67-39-28

የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page