| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 10፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addsis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግንባታ ዲዛይን፣ ቁጥጥር እና የማማከር አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ብግጨ- 007/13
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በ2013 በጀት ዓመት የድሬዳዋ ኤርፖርት ወደ ቢከን መስሪያ ቤት የሚወስደው ድልድይ የዲዛይንና ቁጥጥር የማማከር አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የመንገድና ድልድይ አማካሪ ከሆኑና የታደሰ ፈቃድ ካላቸው፣ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳይት በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ ከተመዘገቡ እና ወቅታዊ የመንግስት ግብር የከፈሉበትን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ከሚችሉ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- ስለጨረታው አፈጻጸም የሚገልፅ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በCP0. ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ዋስትና ማቅረብ ደመቻል አለባቸው:: የባንክ ዋስትና ከሆነ ቢያንስ ለ90 ቀናት የፀና መሆን አለበት፡፡
- ጨረታው ታህሳስ 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለሥልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 18 ውስጥ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾችቅድሚያ ክፍያ የሚፈልጉ ከሆነ ለሚሰጣቸው ክፍያ አስቀድሞ ተመጣጣኝ የባንክ ዋስትና ወይም CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ላለማጭበርበር ቃል የሚገቡበትን ፎርም ሞልተው ከመወዳደሪያ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ፎርሙ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
- ባለሥልጣን መ/ቤቱ ለጨረታው አፈጻጸም የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አድራሻ፡- ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አካባቢ፣ ከኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና መ/ቤት ፊት ለፊት ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡- የስልክ ቁጥር 0116 65 02 27 ወይም 0116 65 02 00 የውስጥ መስመር 116 ወይም 209 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን