| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 5፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢው መለያ ቁጥር፡ አአከመባ/ግንባታ/ቡ-2/006-02/13
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን የቢሮ ግንባታ አገልግሎት የአልሙኒየም የበር እና መስኮት አቅርቦት ገጠማን ጨምሮ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር መግዛት ይፈልጋል ፡፡
| ተ.ቁ | የዕቃው መግለጫ | ብዛት በካሬ ሜትር | ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው | የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት | የጨረታ ማስከበሪያ በብር |
| ሎት -1-ቦሌ ሚካኤል | አልሙኒየም በር ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማን ጨምሮ ግሪል ያለው | 136.53 | 60 ቀን | 16/04/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት | 16/04/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት | 19,000.00 |
| አልሙኒየም በር ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማን ጨምሮ ግሪል የሌለው | 12.88 | |||||
| አልሙኒም ፍሬንች ዶር ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማን ጨምሮ ግሪል ያለው | 37.75 | |||||
| አልሙኒም ዊንዶው ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማን ጨምሮ ግሪል የሌለው | 29.31 | |||||
| አልሙኒየም ዊንዶው ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማ ጨምሮ ግሪል ያለው | 169.78 | |||||
| አልሙኒም ዊንዶው ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማን ጨምሮ | 136.18 | |||||
| ሎት-2 ገርጂ | አልሙኒም በር ከነሙሉ ዕቃው እና ገጠማን ጨምሮ | 65.94 | 10,000.00 |
ስለዚህ፡– :
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ በመስኩ የተሰማሩበት የንግድ ስራ ፍቃድ፣ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ ስለመመዝገቡ ማስረጃ ሊሆን የሚችል ሰርተፊኬት (online PPA supplier list registration certificate) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሠንጠረዥ በተገለፀው መሠረት ሲሆን ለሁለቱም ሎት የሚሳተፉ በድምሩ ብር 29,000.00/ሃያ ዘጠኝ ሺ ብር/ ማቅረብ አለበት። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
ስልክ ቁጥር፡- 011-37 41-03/ 011-3-72-28-15/011-3-72-28-25
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን