| Published on:Addis Zemen ( ታኅሣሥ 4፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የግንባታ ሥራ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ፣
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን
- ሎት 01 ቀበሌ 08 የስፖርት ሜዳ ግንባታ ሥራ በፓኬጅ ቁጥር D/Berhan/ CW-01/2020/21 በከተማ ከተመደበ በጀት በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ /GC/ ደረጃ 8 እና በላይ የሆኑ ስራ ተቋራጮችን
- ቀበሌ 07 ከመምህራን ኮሌጅ አጥርና የበሬሣ ወንዝ አጠገብ የችግኝ ጣቢያ ግንባታ ሥራ ፓኬጅ ቁጥር D/Berhan/ullDP/CW-O8/2020/21 በuiilDP በጀት በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ (Cር/ ወይም በህንፃ ሥራ ተቋራጭ /EC/ ደረጃ 8 እና በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው እና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የሚከተሉትን መሥፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታ መሳተፍ ይችላሉ፡፡
1.በ2013 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / yin Number/ ያላቸው
3 የግዥ መጠኑ ከብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
4 ተጫራቾች ከአማራ ክልል ወጭ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ከሆነ የታደሰ የፌዴራል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምሥር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5 ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀስ-ተን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ዋጋቸውን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡ የግንባታዎቹን የሥራ ዝርዝር መግለጫ Specification/እና መወዳደሪያ መሥፈርቶቹን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
7 በጨረታው ሰነድ ላይ ሥርዝ ድልዝ ወይንም ለመለየት እሻሚ የሆነ ዕሁፍ መኖር የለበትም፡፡
8 ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ጨረታ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
9 ተጫራቾች ለ30 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለተቁ1 ብር 15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ ለተ.ቁ2 ብር 10000 /አሥር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም ስሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና | ጋራንት/ በሥማቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራከሽን አገልግሎት ጽ/ቤት በሚል አድራሻ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደሩበት የግንባታ ጨረታ ህጋዊ ማስረጃዎቹን እና የጨረታ ሰነዱን በአንድ ላይ በማድረግ በጥንቃቄ ስታር ፖስታ በደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን አገልግሎት ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 29 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ በግልፅ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
11.ጨረታው በጋዜጣ ግልፅ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደ/ብ/ከ/ እስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 29 በ4፡ 00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። ዕለቱ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የህዝብ በዓላት ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምከንያት ባይገኙ የጨረታው ፖስታ ተሟልቶ ከተገኘ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።
12. አሸናፊው ተጫራች ውጤት ከተለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀን በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚፈለጉበትን ማስረጃዎች በማቅረብ ውለታ መፈፀም ይኖርበታል፡፡
13 በጨረታው አሸናፊ የሆነ የውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ /10%/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
14 መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ወይም አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብት አለው።
15 በማስታወቂያው ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
16. ተጫራች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ከሰኞ እስከ ዓርብ ባሉት ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 011 681 2717/28 57 ላይ በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የደ/ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶች ኮንስትራክሽንና አገልግሱት
ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን