The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የግድብ መሰረት ግራውንቲንግ (Dam Foundation Grouting) ስራን በንዑስ ተቋራጭ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ባህር ዳር 
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

አገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር NCB AWWCE 04/2013 ዓ.ም

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባው ለአጅማ ጫጫ መስኖ ፕሮጀክት ግድብ አገልግሎት የሚውል የግድብ መሰረት ግራውንቲንግ (Dam Foundation Grouting) ስራን በንዑስ ተቋራጭ ለማሰራት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊው ለመስጠት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1.  የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና ተያያዥ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም አርፎበት በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቶች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ቢያንስ ለ90 ቀን እና ፀንቶ የሚቆይ 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር) በድርጅታችን ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡ አሸናፊ ከተለየ እና ከአሸናፊው ጋር ውል ከተያዘ በኋላ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቶች ስራውን ሰርተው የሚያጠናቅቁበት ጊዜ | Construction time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ ስራውን ሰርቶ የሚያጠናቅቅበትን ጊዜ ገደብ በግልፅ በሰነዱ ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (ኢውስኮድ) ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ 21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ይከፈታል፡፡ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መከፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ባይገኙም ጨረታው በግዥ ኮሚቴ አማካኝነት ስለሚከፈት ተጫራቾች ከውድድሩ አይታገዱም፡፡ ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ለሚወሰዱ ማንኛውም ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ ወይም የድርጅቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ሲፒኦ ወይም አንኮንዲሽናል ባንከ ቢድ ጋራንቲ በማሰራት ማስያዝ እና በአካል ቀርቦ ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መያዝ አለበት፡፡ ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው:: የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮአችን 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻበመክፈል መግዛት ይችላሉ:: የሚሰሩ ዝርዝር የግድብ መሰረት ግራውንቲንግ (Dam Foundation Grouting) ስራን አይነት በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል፤ ለወደፊቱም ድርጅታችን በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
  9. የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡ ከተጠቀሰው ቀናት በታች የሰጠ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
  11. ተጫራቶች ተወዳድረው ያሸነፉበትን የስራ ዝርዝር ሰነድ አቅርበው እና በአማካሪው ተቀባይነት ሲያገኝ ወደ ስራው እንዲገቡ ይደረጋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 058 222 14 79 መደወል ይችላሉ::

አድራሻ ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት

አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን

ድርጅት (ኢው.ስ.ኮ.ድ.)

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page