| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 29፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/09/2013
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለተለያዩ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሠራተኞች የሚያገለግል የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ለማሰራት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ግዥውን መፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት በዋናው መ/ቤት ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ አዲሱ ኬኬር ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ካሼር ቢሮ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን አንደኛ ፎቅ ጀነሬሽን ኦፕሬሽን ግዥ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/GOP/NCB/09/2013 የሚል ምልክት በማድረግ 1(አንድ) ኦሪጂናል እና 2(ሁለት) ኮፒ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ/Bid Security/ የጠቅላላ ሥራውን ቫትን ሳይጨምር 150,000.00 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ) ለ90 ቀን የአገልግሎት ጊዜ የሚቆይ የባንክ ክፍያ ትእዛዝ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ታኅሣሥ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ታኅሣሥ 22 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል፡፡
- ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር፡- 011-5 57 42 95 / 011-5 58 17 25 መደወል ይችላሉ ::
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል