| Published on:Reporter ( ኅዳር 23፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:Addis Ababa |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በቀድሞ ብሔራዊ ሆቴል ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘውን በቂርቆስ ክ/ከ ወረዳ 18 በቀድሞው ቀበሌ 06 በአዲሱ ወረዳ 09 የሚገኘውን በአሁኑ ጊዜ ፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ተከራይቶ የሚጠቀሙበትን ቢሮ ለማስጠገን ስለፈለግን፡
በዚሁ መሠረት፡
- በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ፧ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
- ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው ፤
- ተጫራቾች ጨረታውን ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ጉርድ ሾላ በሚገኘው በድርጅቱ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይቻላሉ ፤
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውንና ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 2 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላው ዋጋ 5% CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስረኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 8፡30 ሰዓት በፌዴሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 5 (መሰብሰቢያ አዳራሽ) ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- አድራሻ፡- ጉርድ ሾላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 6
- ለበለጠ መረጃ፡- 0116-47-07-94/ 0116-47-95-78 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ፋክስ 0116-45-08-79
- ፖ ሳ.ቁ 13336
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን