| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 23፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:የቤንች ሸኮ ዞን የጊዲ ቤንች ወረዳ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
የጨረታ ማስታወቂያ
የቤንች ሸኮ ዞን የጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት በ2013 የበጀት ዘመን በዲዙ ከተማ ሊያሰራ ላቀደው የችሎት አዳራሽ እና የቢሮዎች ግንባታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- የደረጃ ቢሲ/ጂሲ (BC/GC6 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የብቃት ማረጋገጫ፤ የንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት በማቅረብ በጊዲ ቤንች ወረዳ በሚገኘው ግዥ እና ከፍያ ክፍል የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 300 ብር በመክፈል መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ በተገቢው ሁኔታ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 130,000 (አንድ መቶ ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች አንድኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ እያንዳንዱን ለየብቻ በሰም በማሸግ እና በጥቅል በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ፖስታ በሰም ታሽጎ ማህተም መምታት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ እና በመፈረም ኦርጅናልና ኮፒ የሚል ፅሁፍ በግልፅ በሚታይ ቦታ መፃፍ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የስራ ቦታ፤ የተጫራቹ አድራሻ እና የተወካዩ ስልክ ቁጥር በመግልዕ መፃፍ አለበት።
- ይህ ጨረታ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በማድረግ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚታሽገው በማስታ ወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በጊዳ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሽጋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ተኛው ቀን በቤንች ሽኮ ዞን በጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጊዲ ቤንች ወረዳ ፍ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የቤንች ሸኮ ዞን የጊዲ ቤንች
ወረዳ ፍ/ቤት