The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

የምርት መሣሪያዎችን ማሳያ ክፍል ግንባታ

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 20፣ 2013 )Place of Bid Competitions:ወላይታ ሶዶ
Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!)

Please Check the Countdown!

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የሶዶ ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት ለሚያመርታቸው ምርቶች የሚውል፡-

  • በሎት 1. የተለያዩ የምርምርና የልማት አላቂ ዕቃዎችንና የማሽን መለዋወጫዎችን፣
  • በሎት 2. የሠራተኛ ደንብ ልብስን፣ 
  • በሎት 3. የምርት መሣሪያዎችን ማሳያ ክፍል ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በመስኩ በአቅራቢነት የተሰማሩ፣ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋብ የሆኑ ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘውን ሠነድ የማይመለስ ብር ለሎት 1. 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ፣ ለሎት 2. 50.00 /ሃምሳ ብር/ብቻ፣ ለሎት 3. የግንባታ ፈቃድ G9 እና ከዚያ በላይ ያላቸው ሆኖ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ከማዕከሉ ግ/ክ/ን/አ ሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 16,863.66/ አስራ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከስልሳ ስድስት ሣንቲም /ብቻ፣ ለሎት 2. ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር ብቻ፣ ለሎት 3 ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ብቻ ስባንክ ከተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ጋር በማድረግ በሰም በታሸገ ፖስታ ለሎት 1 እና 2 እስከ 06/04/2013 ዓ/ም ለሎት3 እስከ 14/04/2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታዉ ሣጥን ለሎት 1 እና 2. በ09/04/2013 ዓ/ም፣ ለሎት 3. በ19/04/2013 ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ላይ በማዕከሉ ግ/ፋ/ን/አ/ሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፡፡
  5. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ተጫራቾች የዕቃዎችን ዋጋ ከመ/ቤቱ በሚሰጠው ሰነድ ላይ መሙላት አለባቸው፡፡
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-551-2236/37 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የሶዶ ገጠር ቴክኖሎጂ

ማስፋፊያ ማዕከል

ወላይታ ሶዶ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page