| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 20፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:ወላይታ ሶዶ |
| Rough Estimation of Remaining Time for Bid Submission (don’t use it before check up!) |
Please Check the Countdown!
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ የሶዶ ገጠር ቴክኖሎጂ ማስፋፊያ ማዕከል በ2013 በጀት ዓመት ለሚያመርታቸው ምርቶች የሚውል፡-
- በሎት 1. የተለያዩ የምርምርና የልማት አላቂ ዕቃዎችንና የማሽን መለዋወጫዎችን፣
- በሎት 2. የሠራተኛ ደንብ ልብስን፣
- በሎት 3. የምርት መሣሪያዎችን ማሳያ ክፍል ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል:: በዚህም መሠረት በጨረታ ለመሣተፍ የሚፈልጉ
ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በመስኩ በአቅራቢነት የተሰማሩ፣ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቫት ተመዝጋብ የሆኑ ተጫራቾች የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘውን ሠነድ የማይመለስ ብር ለሎት 1. 100.00/ አንድ መቶ ብር/ ብቻ፣ ለሎት 2. 50.00 /ሃምሳ ብር/ብቻ፣ ለሎት 3. የግንባታ ፈቃድ G9 እና ከዚያ በላይ ያላቸው ሆኖ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ብቻ በመክፈል ከማዕከሉ ግ/ክ/ን/አ ሥራ ሂደት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 16,863.66/ አስራ ስድስት ሺህ ስምንት መቶ ስልሳ ሶስት ብር ከስልሳ ስድስት ሣንቲም /ብቻ፣ ለሎት 2. ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር ብቻ፣ ለሎት 3 ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ብቻ ስባንክ ከተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ጋር በማድረግ በሰም በታሸገ ፖስታ ለሎት 1 እና 2 እስከ 06/04/2013 ዓ/ም ለሎት3 እስከ 14/04/2013 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታዉ ሣጥን ለሎት 1 እና 2. በ09/04/2013 ዓ/ም፣ ለሎት 3. በ19/04/2013 ዓ/ም በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ8፡30 ላይ በማዕከሉ ግ/ፋ/ን/አ/ሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዋጋ ከመ/ቤቱ በሚሰጠው ሰነድ ላይ መሙላት አለባቸው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-551-2236/37 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሶዶ ገጠር ቴክኖሎጂ
ማስፋፊያ ማዕከል
ወላይታ ሶዶ