| Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 19፣ 2013 ) | Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ |
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በጨረታው ሰነዱ ውስጥ ይገለጻል፣
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁ/ት/ባ 05/2013
የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘውን የላምበረት መናኸሪያ የአጥርና የቢሮ ጥገና እና ሌሎች የጥገና ስራዎች ለማሰራት ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና ብቃት ማረጋገጫ የ2013 ዓ.ም ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣(BC-5 Or GC-6) ደረጃ እና ከተጠቀሰው በላይ
- በግዢ ኤጀንሲው ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በጨረታ ለመሳተፍ የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/በመከፈል ከባለስልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 305 መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጥቅል 200,000.00 ብር (ሁለት መቶ ሺ ብር) እውቅና ካለው ባንክ ሲፒኦ በትራንስፖርት ባለስልጣን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፣
- ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ በመመስረት የሚያቀርበው ዋጋ ተቀባይነት የለውም፣
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በጨረታው ሰነዱ ውስጥ ይገለጻል፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋና የቴክኒክ ግምገማ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አድራሻ፡-እስታዲየም አካባቢ የሚገኘው የዋናው መ/ቤት ህንፃ
- በተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0115-5102-44 የውስጥ መስመር 231 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፌደራል ትራንስፖርት ባስስልጣን