The Best Construction Tenders Advertiser in Ethiopia

Tenders

Contractor

Read more

 

Consultant

Read more

 

Machinery Rental

Read more

 

Direct Unit Price

Read more

 

ላምበረት መናኸሪያ የአጥርና የቢሮ ጥገና እና ሌሎች የጥገና ስራዎች

Published on:Addis Zemen ( ኅዳር 19፣ 2013 )Place of Bid Competitions:አዲስ አበባ 
  1. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በጨረታው ሰነዱ ውስጥ ይገለጻል፣

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁ/ት/ባ 05/2013

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘውን የላምበረት መናኸሪያ የአጥርና የቢሮ ጥገና እና ሌሎች የጥገና ስራዎች ለማሰራት ሥራ ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና ብቃት ማረጋገጫ የ2013 ዓ.ም ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣(BC-5 Or GC-6) ደረጃ እና ከተጠቀሰው በላይ
  2. በግዢ ኤጀንሲው ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በጨረታ ለመሳተፍ የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው፣
  4. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/በመከፈል ከባለስልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 305 መግዛት ይችላሉ፤
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጥቅል 200,000.00 ብር (ሁለት መቶ ሺ ብር) እውቅና ካለው ባንክ ሲፒኦ በትራንስፖርት ባለስልጣን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  6. የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው፣
  7. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ በመመስረት የሚያቀርበው ዋጋ ተቀባይነት የለውም፣
  8. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በጨረታው ሰነዱ ውስጥ ይገለጻል፣
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋና የቴክኒክ ግምገማ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  10. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • አድራሻ፡-እስታዲየም አካባቢ የሚገኘው የዋናው መ/ቤት ህንፃ
  • በተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0115-5102-44 የውስጥ መስመር 231 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የፌደራል ትራንስፖርት ባስስልጣን 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You cannot copy content of this page